Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ቬንዙዌላ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

0 884

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 ኢትዮጵያና ቬንዙዌላ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ የአገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተስማሙ።

ዶክተር ወርቅነህ ገበየው የቬንዙዌላ አቻቸው ጆርጅ አሬያዛን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የሁለቱ አገራት ግንኙነት ለበርካታ ዓመታት የቆየ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታና የኢትዮጵያ የተወሰኑ ተማሪዎች ወደ ቬንዙዌላ ሄደው እንዲማሩም ነፃ የትምህርት ዕድል በመስጠት ድጋፍ ማድረጓን ገልጸዋል።

”እንዲያም ሆኖ አገራቱ ያላቸው ግንኙነት የሚጠበቀውን ያህል ጠንካራ አልሆነም” ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ በጋራ ሊሰሩባቸው በሚችሉበት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ቬንዙዌላ በደቡብ አሜሪካ ከፍተኛ ሚና የምትጫወትና የነዳጅ ኃብት ያላት አገር መሆኗም ለቀጣይ የትብብር ሥራዎች ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት መስማማቷን ዶክተር ወርቅነህ አንስተዋል።

በዚህም ግንኙነቱን አሁን ካለበት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆርጅ አሬያዛን በበኩላቸው አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አመልክተዋል።

በዚህም መሰረት በግብርና ፣ በኃይል ልማት ፣ በትምህርትና በአገልግሎት ዘርፍ ላይ በጋራ ለመሥራት እንደሚፈልጉ አረጋግጠዋል።

በትምህርት ዘርፍ ደግሞ በተለይም በሕክምናው ዘርፍ በርካታ ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ወደ ቬንዙዌላ ሄደው ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በአየር ትራንስፖርት ግንኙነት በመፍጠር አገራቱ ይበልጥ አጋርነታቸውን ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያና የቬንዙዌላ የሁለትዮሽ ግንኘነት በ1956 ዓ.ም መጀመሩን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy