Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የደቡብ ሱዳን ሰላም ስምምነትን መተግበር ብቸኛ አማራጭ ነው- ዶ/ር ወርቅነህ

0 296

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሁለተኛው ዙር የደቡብ ሱዳን የሠላም ሂደት ትግበራ ማሳለጫ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በስብሰባው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኢጋድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሠላም ለማምጣት የሠላም ስምምነቱን መተግበር ብቸኛው አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል።

ሁሉም የደቡብ ሱዳን ኃይሎች ቃል ከመግባት በዘለለ ለሠላም ስምምነቱ ትግበራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት ሊያሳዩ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

ኢጋድም ሆነ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ከአሁን በኋለ ስምምነቱን መጣስ የሚታገሱበት ምንም ምክያንት የላቸውም ብለዋል።

ሁለተኛው ዙር የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ማሳለጫ ለደቡብ ሱዳን ሠላም ብቻኛው አማራጭ መሆኑን ገልፀዋል።

የደቡብ ሱዳን ኃይሎች የሀገሪቱ ህዝቦች ሞት፣ ስደት ፣ስቃይና እንግልት ሊሠማቸው ይገባል ብለዋል።

ኢጋድ በአገሪቱ ሙሉ በሙሉ ሠላም እንዲሰፍን ጥረቱን ይቀጥላል ያሉት ዶክተር ወርቅነህ፥ ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰቡ የሠላም ሂደቱን እንድደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፥ የደቡብ ሱዳን ኃይሎች ለሠላም ስምምነቱ ተገዥ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ ከኢጋድ ጋር በመሆን የደቡብ ሱዳንን የሠላም ሂደት መደገፉን ይቀጥላል ብለዋል።

ሁለተኛው ዙር የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር ዋና ዋና አጀንዳዎች በመንግስት አወቃቀርና አስተዳደር፣ ዘላቂ የተኩስ ማቆም፣ የሽግግር ጊዜ የሰላም ሁኔታ ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ናቸው።

በመድረኩ የሀገሪቱ መንግስት እና ዋና ተቃዋሚው ሃይል ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የታጠቁ እና ያልታጠቁ የፖለቲካ ኃይሎች፣ የሲቪክ፣ የወጣቶችና የሴቶች ማህበራት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የግል ድርጅቶች ተወካዮችና ሌሎች በሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ውክልና ያላቸው ሀይሎች እየተሳተፉ ነው።

የመጀመሪያው የሰላም ስምምነት ማሳለጫ ስብሰባ በታህሳስ ወር 2010 ዓ.ም ለ4 ቀናት በአዲስ አባበ የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተካሂዶ በስኬት መጠናቀቁ ይታወሳል።

መረጃውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው ያገኘነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy