Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሠላማችን በጃችን …!

0 1,180

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሠላማችን በጃችን …!

 

ከሲኢድ መሐመድ

 የሞቀ ሳይሆን የተቃጠለ እሳትን ያውቀዋል፡፡ የኢትዮ ህዝብ በቀደሙት ርዓት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባደረጋቸው ጦርነቶች ምክንያት ከጦርነት ተጠቃሚ የሚሆን ወገን እንደሌለ ጠንቅቆ ያምናል።፡ ልጆቹ በግዳጅ ከጉያው እየተነጠቁ  ለእሳት ይዳረጉ የነበሩበት ሁኔታ የማይድን አካላዊና ስነልቦናዊ ጠባሳ ጥሎ እንዳለፈ  የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ሰላም ለኢትዮጵያዊያንም ሆነ ለሌሎች ህዝቦች በምንም ዓይነት ዋጋ ሊገመት የማይችል ፋይዳ እንዳለው እሙን ነው፡፡  ይህን ለኢትየጵያ ህዝብ  መንገር ለቀባሪ የማርዳት ያህል ነው፡፡

 

 ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በአገሪቱ ሰላም ሰፍኗል። በዚህ ምክንያትም ህዝቦች በየደረጃው የልማት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡  የሰፈነውን ሰላምና መረጋጋት አጣጥሞ ሳይጠግብ አዲስ የሁከትና የብጥብጥ አጀንዳቸውን ዕውን ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች መከሰታቸውና የተለያዩ ሰላምን የሚያዉኩ ተግባራት እያከናወኑ እንደሆነ ይታወቃል፡፡  እነዚህ ቡድኖች ህዝቦቻችን መቋጫ በሌለው ደም መፋሰስ እንዲገቡ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ 

 

በአንዳንድ የኦሮሚያና የአማራ አካባቢዎች ስርዓቱን የሚያናጉ የህዝቦች አብሮነትን የሚሸረሽሩና  ቀጣይነት ባለው የሁከትና የትርምስ ምህዋር የሚያሳፍሩ አጀንዳዎችን አንግበው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈጦ የመጣው ማንነትን ረት ያደረገ ግዲያና ዝርፊያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሻሻላል ተብሎ ሲገመት እየተባባሰ መምጣቱ  ዋቢ ማደረግ ይቻላል፡፡

 

ይህ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት እያደረሰ ይገኛል፡፡ በአካባቢው የተከሰቱት ግጭቶች ብሄርን ማዕከል ያደረጉ መሆናቸው ደግሞ ነገሩን ያወሳስበዋል፡፡ ይህ ማንነትን ማዕከል ያደረገ ግዲያና ዝርፊያ   ህዝቦች የፈጸመው እንዳልሆነ ምስክርነት መጥራት አያሻውም፡፡  ይህንን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉ ወገኖች ፀረ ሰላም ይሎች ናቸው፡፡  በየወቅቱ ስለከከሸፋባቸው ሰላምን የማወክ ተግባራቸውን ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በተለያየ ርዕስ ቀደም ብሎም ሲነሱ የነበሩ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

የአገሪቱን ሰላም ለማደፈረስና ልማቷን ለማደናቀፍ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሰበብ ቀላል የማይባል ጥረት መደረጉ ይታወቃል፡፡  ከከሸፉ አጀንዳዎች መካከል በሃይማኖት ስም ህዝብን ከህዝብ ለማፋጀት የተወጠኑ ሴራዎች እንደነበሩ  ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ በአገሪቱ  የሃይማኖት  መቻቻልና መተሳሰብ  ለዘመናት የዘለቀ በመሆኑ ህዝቦች አንድነታቸውን ጠብቀው ኖረዋል፡፡

 

የሃይማኖታዊ መቻቻል፣ መረዳዳትና አብሮነት ኢትዮጵያዊያን  ከሌሎች አገራት ህዝቦች ከምትለይባቸው ዋና ዋና ነገሮች አንዱ  ነው፡፡  በአገሪቱ የሃይማኖት ነጻነት ባልተረጋገጠበት  ወቅት ሳይቀር ኢተዮጵያውያን በሃይማኖት ልዩነት ምክንያት በጋራ ለመኖር ያስቸገራቸው ወቅት እንዳልነበር  ይታወቃል፡፡ መቻቻልና መተሳሰብ  ለዘመናት የዘለቀ አኩሪ ባህላቸው ነው፡፡  አንዱ የሌላውን ሃይማኖታዊ ዝግጅትና ስርዓት ላይ ይገኛል፡፡ በሃዘንም ሆነ በደስታ ይተጋገዛሉ ይደጋገፋሉ፡፡ ይህ ለዘመናት የዘለቀ  የኢትዮጵያውያውያን መገለጫ ነው፡፡

 ዘመናት የዘለቀውን መቻቻል፣ መተሳሰብና አብሮነትን ለመናድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰተ የመጣውና ባለፉት ስድስት ዓመታት በአገሪቱ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ የነበረው አሁንም ሙሉ በሙሉ ተወግዷል ለማለት የማያስደፍረው በሃይማኖት ስም አገሪቱን ወደ ቀውስ ለማስገባት ይደረግ የነበረው ጥረት በህዝብ ትብብር መክሸፍ ችሏል፡፡ ሆኖም ግን ከደርግ ውድቀት ማግስት ይታይ ነበረውና አሁን ተጠናክሮ የመጣው ብሔሮች፡  ብሔረሰቦችና ህዝቦችን የማጋጨት ተግባር ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት አጀንዳ ሆኗል፡፡

ማንነትን ረት ያደረገ ብጥብጥ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች ታይቶ የነበረ ቢሆንም ከስሞ ሁሉም ህዝቦች በአንድነት መኖርና የጋራ አገራቸውን መገንባት በተያያዙበት በአሁኑ ወቅት እንዳድስ እየተቀሰቀሰ መምጣቱ ከበስተጀርባው ሌላ አጀንዳ እንዳለው ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡

 በኢትዮጵያ ትርምስ መፍጠር አጀንዳ ኤርትራን ጨምሮ የአንዳንድ አገራት ረጅም እጅ እንዳለበት የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ የኤርትራ መንግ በቀጠናው ሰላምን ለማወክ በሚያደርጋቸው ዕኩይ ተግባራት ከአገራችን ጋር በገባው ፍጥጫ ምክንያት በዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ተጥሎበታል፡፡ ሲኮነንና ሲወገዝ የኖረው የኤርትራ ዕኩይ አመራር ከአገራችን ጋር በከፈተው ጦርነት የደረሰበት ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ የትየለሌ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ለኢትዮጵያ  የሚኖረው ምላሽ ሽብርን ከመፍጠርና እርስ በርስ ከማጋጨት የዘለለ ይሆናል ተብሎ አይገመትም፡፡

ከህዳሴው ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ የአገሪቱን የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ በተለያየ መልኩ የሚንቀሳቀሱ አገራት እንዳሉ ማወቅ አያዳግትም፡፡ ኢትዮጵያ ለዘመናት ተደፍሮ የማይታወቀውን  የአባይ ወንዝ ላይ ልማት መገንባት መጀመሯ ግብጽ ውሃውን በበላይነት የመቆጣጠር  ፍላጎቷና ቀደም ሲል ከሱዳን ጋር የገባችው ስምምነት መፍረሱን ስታይ የተለያዩ አጋጣሚዎች መጠቀም አትችልም ብሎ መገመት የዋህነት ነው፡፡

በመሆኑም ቀደም ሲል በአንዳንደ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች በአሁኑ ወቅትም በአንዳንድ የአማራ አካባቢዎች  በቀጠለው ችግር ላይ የግንቦት ሰባትና  እነሱን የመሰለ ዓላማ የሚያራምዱ ተዋኒያንና እጅ የለበትም ብሎ መደምደም የዋህነት ቢሆንም በዋናነት ግን የውስጥ ባለመራቱና አመራሩ የሚጠበቅበትን ተግባር በተሰጠው ላፊነት መጠን ባለመወጣቱ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡

 

በአገራችን እያጋጠመ ያለው ችግር ምንም ይሁን ምንም ሰላምን የሚያደፈርሱ ወገኖች ወግዱ ሊባሉ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ  ለዓመታት የገነባችውን ልማት የማፍረስና ሰዎችን በማንነታቸው የመግደልና  ንብረት  የማውደም መንግትን ጥያቄ ማቅረብ ሳይሆን ሕግን መተላለፍና ወንጀል እንደሆነ እሙን ነው፡፡ የአገሪቱን ሕገ መንግ  በሚፈቅደው ረት  የማስከበር ላፊነቱን ባግባቡ ሊወጣ ይገባል፡፡  መንግ ሕገመንግሥቱን የሚያከብረውና የሚያስከብረው  ላፊነቱን ለመወጣት ነው፡፡ ሕገ መንግሥቱን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት  በህዝብ ተሰጥቶታል፡፡ ይህንን ሕግንና ደንብን የማስከበር  አደራ መወጣት ይኖርበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት መንግሥት አደራውን ለመወጣትና ሕግንና ደንብን ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ ቢሆንም  የዘላቂ ሰላም ጉዳይ በመንግሥት ጥበቃ ብቻ የሚፈጸም አይደለም፡፡  የሰላም ባለቤት ህዝቡ ነው፡፡ የአገራችን ህዝብ ሰላም ወዳድ ህዝብ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አሁንም ሰላሙን በዘላቂነት ለመጠበቅ ከመንግሥት ጋር   ተባብሮ ይገባል፡፡  እሳትን የሚያውቀው  የሞቀ ሳይሆን ተቃጠለ ነውእንደሚባለው የሁከትና  ግጭት አሉታዊ ፋይዳ   ለኢትዮያዊያን አዲስ ነገር አይደለም፡፡  እልቂትና እርስ በርስ መተራረዱ ለአስርት ዓመታት አይተውታል፡፡  በዚህም ምክንያት ኢኮኖሚያቸው ደቆ ህዝቦች ለስደት ተዳርገዋል፤ በረሃብ አለንጋ ተገርፈዋል፡፡ ያንን ችግር ረቱ ለመቅረፍ ሲሉ በርካታ ዜጎች ተሰውተዋል፡፡ ተሰውተው አልቀሩም ዕውን አድርገውታል፡፡

  የዜጎች ደም የዜጎች ድካም ከንቱ እንዳይቀር ነው መንግሥት ሕገመንግሥቱን የሚያከብረውና የሚያስከብረው፡፡ በመሆኑም መንግሥት አንድን ቡድን ለመጥቀም ሌላውን ለመጉዳት በሚል  ሕገመንግሥቱን የሚሸራርፍበት ሁኔታ የለም፡፡ በአገራችን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ዕኩልነት ተረጋግጧል፡፡ አንድ ብሔር የበላይ ሌላው የበታች የሚሆንበት ስርዓት ከተቋጨ ሃያ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡  የሃይማኖት ነጻነት በአስተማማኝ መልኩ ተረጋግጧል፡፡ ማንኛውም ዜጋ ያለምንም መሸማቀቅ በነጻነት የፈለገውን ሃይማኖት ማመን ችሏል፡፡  ስለዚህ አንድ ብሔር በሌላ ብሔር የሚነሳበት አግባብና ረት የለም፡፡

 በመሆኑም ማንነትን ረት ያደረገ ትንኮሳ ዓላማው ሌላ መሆኑ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ቀደም ሲል ሃይማኖትን ሰበብ አድርጎ የሀገሪቱን ልማት ለማደናቀፍና ሰላሟን ለማወክ የተኬደበት ሴራ በከሸፈ ማግስት መልኩን ቀይሮ የመጣው ማንነትን እየለዩ ሰዎችን  መግደል አሁንም የውጭ ጠላቶችና አገር ውስጥም ያሉ የውስጥ አርበኞች ተግባር እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡  ለዚህም ነው መንግሥት ውስጡን ማየት ያለበት፡፡  እስካሁን የተደረጉ  ግምገማዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ቢታወቅም ፀረ ሰላም ይሎች ይህ የተሃድሶ ግምገማ ተጠናክሮ እንዳይቀጥልና የውስጥ አርበኞቻቸው እንዳይመነጠሩ  ሁከትንና ብጥብጥን በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች  ቀጥለውበታል፡፡ 

 

75 በላይ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ህዝች በጋራ በሚኖሩባት አገር  በቀደሙት ስርዓታት  እኩልነታቸው ማረጋገጥ የሚያስችል ሁኔታ ባለመኖሩ አንዱ በሌላው የበላይነቱን ያወጀበት  የሁሉም ዜጎች ተጠቃሚነት ያልተረጋገጠበት ሁኔታ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ታሪክ ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ያለው ኋይማኖታዊ ቁርኝንት የጠበቀ  በመሆኑና  የአንድ ሃይማኖት አማኞች ከሁሉም ብሔር፤ ብሔረሰብና ህዝቦች የተውጣጡ በመሆናቸው በብሔር ቢለያዩ በሃይማኖት በሃይማኖት ቢለያዩ በብሄር የተዛመዱ ስለሆኑ  ጠላቶች የጠነሰሱትና ለረጅም ጊዜ የደከሙበት ኢትዮጵያን በሃይማኖትና በብሔር  ከፋፍሎ የማፋጀት ጉዳይ የማይታለም ሆኖባቸዋል፡፡

 የአገራችን ሰላም ባለቤት የሆኑት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለሰላም እያደረጉ ያለውን ትጋት አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል፡፡ ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት የተመዘገበው የኢኮኖሚ ለውጥና በየደረጃው የታየው ተጠቃሚነት ሰላም በመስፈኑ  የመጣ  ነው፡፡ በመሆኑም ቅድሚያ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ለሁሉም እንቅስቃሲያችን ወሳኝ በመሆኑ እጅና ጓንት ሆነን ፀረ ሰላም ይሎችን መዋጋት ይጠበቅብናል፡፡

 ሰላም ለአገራችን የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ መንግሥት የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ለማስፋት ችግርን ለመፍታት ውስጡን በመፈተሽ የተለያዩ የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ደረጃ በደረጃ ችግሮቹን ለመፍታት በሚንቀሳቀስበት በአሁኑ ወቅት ሰላምን የሚያውኩና የአገሪቱን ጉዞ ወደ የሚጎትቱ ተግባራት  እየተከሰቱ በመሆኑ ህዝቡ ይህንን ተገንዝቦ ለሰላሙ ዘብ ሊቆም ይገባል፡፡ ሰላማችን በጃችን ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ይህንን አማራጭ የሌለው የህልውናችን ረት የሆነውን ሰላምን ተባበሮ ማረጋገጥ ይዋል ይደር የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy