ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች የሚሳተፉበት የሰላምና የልማት ህዝባዊ ኮንፍረንስ ከመጋቢት 19 2010 ዓ.ም ጀምሮ በመቐለ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
በትግራይ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የሚዲያዎች አቅም ልማት ግንባታና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ግርማዬ እንዳሉት፥ ለ4 ቀናት የሚካሄደው የኮንፍረንሱ ዓላማ የህዝቦችን አንድነት ለማጠናከር ነው።
የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በቆይታቸው በሰላም፣ በልማትና በዴሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ እንደሚወያዩ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
የክልሉ መንግስት ባዘጋጀው በዚሁ ኮንፍረንስ ከ2 ሺህ 500 በላይ የማህበረሰብ ተወካዮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
ምንጭ፦ ኢዜአ