Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለዘላቂው መፍትሔ…

0 247

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለዘላቂው መፍትሔ…

                                                      ደስታ ኃይሉ

ሰሞኑን የብሄራዊ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም በአሁኑ ጊዜ በድርቅ ሳቢያ በአገራችን እርዳታ የሚያስፈልገው ህዝብ ቁጥር 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል። ይህ አሃዝ ካለፈው ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የተወሰነ ጭማሪ ያሳየ ነው። ይህ የሆነው በግጭት ምክንያት ዜጎቻችን ስለተፈናቀሉ መሆኑም በመግለጫው ላይ ተመልክቷል።

በድርቅ ላይ የሰላም እጦት ሲጨመር ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማንም ግልጽ ይመስለኛል። ድርቅ ማንም ሊቋቋመው የማይችለው የተፈጥሮ ክስተት ነው። ይሁን እንጂ አደጋው ወደ ረሃብነት እንዳይቀየር በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት እንዲሁም በመስኖ ልማት ዘላቂ ስራ እየተከናወነ ነው። ስለሆነም ህብረተሰቡ በእነዚህ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በመረባረብ ካለፈው ጊዜ በበለጠ ከመንግስት ጎን መቆም የሚኖርበት ወቅት አሁን ይመስለኛል።

በተፈጥሮ የአየር መዛባት ምክንያት በሀገራችን የድርቅ አደጋ ሲከሰት አዲስ ነገር አይደለም። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰት ጉዳይ በመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም። ሆኖም ይህ በየጊዜው ሀገራችንን የሚጎበኛት የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብነት እንዳይቀየር መንግስት ብርቱ ጥረት አድርጓል።

እንደሚታወቀው ሁሉ ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ  ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆመቆየቱ አይዘነጋም። የኤልኒኖ አደጋ በተከሰተበት ወቅትም አደጋውን በመቀልበስ የልማት አጋር ሀገራትን ድጋፍ እምብዛም ሳያገኝ ችግሩ ወደ ረሃብነት ሳይቀየር መቋቋሙ ይህን ጥረቱን አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ከማንም የተሰወረ ጉዳይ አይደለም።

መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረግ እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ በሆነ አኳሃን ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉ ለዜጎቹ ያለውን የኃላፊነትና የተጠያቂነት መንፈስ ስሜትንና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው።

መንግስት የአርሶና የአርብቶ አደሩ ኑሮ እንዲሻሻል ተገቢውን ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ አገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና እንዲፈጠር አድርጓል። ለዚህ ስኬት በመንግስት በኩል የተወሰዱት እርምጃዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው ማለት ይቻላል።

ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት  የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆይቷል። በዚህም መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን ድርቅ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረጉ እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ በሆነ አኳኋን ጥቅም ላይ እንዲውል የክትትል አሰራርን መከተሉ አሁን ላለበት አቅም ያበቁት ይመስለኛል። ያም ሆኖ አርሶና አርብቶ አደሩ ይህን የመንግስትን ጥረት በመደገፍ እየተካሄደ ያለውን የተፈጥሮ ጥበቃና የመስኖ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል አለበት፤ ዘላቂው መፍትሄ ይኸው ስለሆነ።

የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና በመስኖ ልማት ድርቅን በዘላቂነት መከላከል ይቻላል። የመስኖ ልማት በተለይ የተፋሰስ ስራዎች የግብርናው ዘርፍ መሰረቶች ናቸው። በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ኑሮው እንዲሻሻል ተገቢ ትኩረት አግኝቷል። ለዚህም በቂ ማሳያዎችንም ማቅረብ ይቻላል። መንግሥት የዘመናት ቁጭቱን አገራዊ መሠረት ባላቸው አቅጣጫዎች የመፍታት ትግሉን እያካሄደ ነው። አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና ላይ መሆኗን አረጋግጧል።

በአርሶ አደሩ እጅ እንዳለ የሚታሰበው መሬት አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ካለችው መሬት የሚያገኘው ምርት ዝቅተኛ ነው። ይህን መንግሥት በሚገባ በመገንዘቡ ዘርፈ ብዙ የማሻሻል ጥረቶች አድርጓል። በውጤቱም አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮችን ይዞ ለውጥ  ማምጣት አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ መስበር ችሏል።

አርሶ አደሩ የለውጥ መስመሩን ተረድቶ በእምነት ወደ ሥራው በመግባቱ በዓመት ሁለቴና ከዚያም በላይ ለማምረት ችሏል። እንዲሁም በከርሰ ምድርና በገጸ -ምድር ያለውን የውኃ ሃብት የመጠቀም ሰፊ ተግባር አከናውኗል።

በውኃ ማሰባሰብና ማቆር፣ የጉድጓድ ውኃን በመጠቀም የወንዝ ውኃን ጠልፎ ጥቅም ላይ በማዋል ብዙ ርቀት ተጉዟል። በመሆኑም አርሶ አደሩ ከራሱ ፍጆታ አልፎ ለከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት የሆኑትን ምርቶች ማቅረብ ችሏል። ከነዚህ ውስጥ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናቸው።

ከዝናብ ጥገኝነት በተላቀቁ አመራረት የተገኙትን ምርቶች መጠቀምም እየተቻለ ነው። የመስኖ ልማት ሥራው በበጋ የበቆሎ እሸት ተመጋቢዎች እንዲሆን አስችሎናል። ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ ሥራው ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል።

ለአርሶ አደሩም በዚያው ልክ ገበያው ተመቻችቷል። አርሶ አደሩ በራሱ ባቋቋማቸው የአርሶ አደሮች የህብረት ሥራ አማካይነት ምርቱን ለገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል። በዚህም ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ነው።

የግብርናው ዘርፍም በአስተማማኝ ሁኔታ ገበያው ሳያሳስበው ምርትና ምርታማነቱን በማሳደግ ላይ ብቻ አተኩሮ ለልማት ለውጥ ሽግግሩ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርበት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ይቻላል። ለዚህም በአሁኑ ወቅት በተለይ ወጣቱን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ የሚገኘው የተፋሰስ ስራ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል።

መንግስት በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ጉልበት ሳይባክን ጥራቱን የጠበቀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ በየደረጃው እያከናወነ ነው። ይህም አካባቢያዊ ጠቀሜታዎችን ከማረጋገጥ ባሻገር ሀገሪቱን ብሎም ዓለምን እያሰጋ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለመቋቋምና ለመላመድ የበኩሉን ድርሻ ያበረክታል።

የግብርናው ዘርፍ እየዘመነ ትርፍ አምራች አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱት እንዲደርሱ እንዲሁም ድርቅ የሚያጠቃቸው አካባቢዎችም አምራች እንዲሆኑ የሚያስችል ነው። በእኔ እምነት ይህ ሁኔታ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ የመምታት ያህል ነው።

በአሁኑ ወቅት ለግብርናው ምቹ የሆኑ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ናቸው። በተቀናጀ የተፋሰስ ስራዎች አማካኝነት መገኘት የሚገባው ምርትና ምርታማነትም ያድጋል። ርግጥ በዚህ ረገድ ባለፉት ጊዜያት በተከናወኑት ስራዎች ብዙ ርቀት መሄድ የተቻለ ይመስለኛል።

በተለይም በውኃ ማሰባሰብና ማቆር፣ የጉድጓድ ውኃን በመጠቀም የወንዝ ውኃን ጠልፎ ጥቅም ላይ በማዋል ብዙ ርቀት ተጉዟል። በመሆኑም አርሶ አደሩ ከራሱ ፍጆታ አልፎ ለከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት የሆኑትን ምርቶች ማቅረብ ችሏል። ከነዚህ ውስጥ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች በግንባር ቀደምነት ተጠቃሽ ናቸው።

ከዝናብ ጥገኝነት በተላቀቁ አመራረት የተገኙትን ምርቶች መጠቀምም እየተቻለ ነው። የመስኖ ልማት ሥራው በበጋ የበቆሎ እሸት ተመጋቢዎች እንዲሆን አስችሎናል። ባለፉት ዓመታት ሥራው ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል። ይህን የተፈጥሮ ሃብትን የመጠበቅና ከዝናብ ጥገኛ የሆነን አስተሳሰብ በመለወጥ ድርቅን በዘላቂነት መቅረፍ ይቻላል። አርሶና አርብቶ አደሩ በዚህ ረገድ ጠንክረው መስራት ይኖርባቸዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy