Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ተቃርኖዎቹ

0 245

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ተቃርኖዎቹ

                                                         ታዬ ከበደ

በአገራችን ተአምራዊ ሊባል በሚችል ደረጃ ዕድገትና ለውጥ እየተመዘገበ ነው። በሌላ በኩልም በለውጡ አለመርካትና እስከ ሰላማችን የሚያናጉ ተግባራት መፈፀም እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ወይም ተቃርኖ ያላቸው ክስተቶች ይስተዋላሉ። የጉዳዩቹን ተቃርኖአዊ ሂደት ነባራዊ ናቸው። በዕድገቱ ሂደት የተፈጠሩም ናቸው።

ነገር ግን ከዕድገቱ ጋር አብረው የሚመጡ የተወሳሰቡ ጥያቄዎችን ፈጥረዋል። መንግስት በቀላሉ የማይረካ ጠያቂ ህብረተሰብ መገንባት አለብን ብሎ በመስራቱ ይህ በሂደት እውን እየሆነ ነው።

ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በመገንዘብ በወቅቱ ለመፍታት በመሪው ድርጅት ውስጥ የነበረው የዝግጁነት መጓደል ሁኔታዎቹ እንዲወሳሰቡ ምክንያት ሆኗል። ያም ሆኖ ተቃርኖዎቹን በተሃድሶው ለውጡ ሂደት በማስታረቅ ለአገር ዕድገት የድርሻቸውን እንዲጫወቱ ማድረግ ይቻላል። ሌሎች አገሮችም በዚህ ዓይነቱ ተመሳሳይ ሂደት ያለፉ ናቸው። ተቃርኖዎቻቸውን ለበጎ ዓላማ ተጠቅመውበታል። ተስፋዎችንና ስጋቶችን በመገንዘብ የዕድገታቸው ማረጋገጫዎች አድርገዋቸዋል።

በእኛም አገር ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም። ሕገ መንግሥታችን አገሪቱ ፍትሃዊ የምጣኔ ሀብት ዓላማዎችን ማራመድ እንዳለባት በግልጽ ይደነግጋል። ይህንን ዓላማ ለማረጋገጥ መንግሥት ዜጎች በአገሪቱ የሚገኘውን ሃብት በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሠራር ቀይሶ ተፈጻሚ እያደረገ ይገኛል። በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ክልሎች በመንግሥት ልዩ እገዛ ተደርጐላቸው ጭምር የልማቱ ተጠቃሚነታቸው እየተረጋገጠ መጥቷል። ህገ መንግሥቱም በግልጽ ለነዚህ መብቶች ዋስትና ሰጥቷል። መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብቶችን በሕዝብ ስም በይዞታው ሥር በማድረግ ለዜጎች የጋራ ጥቅምና ዕድገት የማዋል ኃላፊነት እንዳለበት በህዳር ወር 1987 ዓ.ም የፀደቀው ህገ መንግሥት ያረጋግጣል፡፡

ሕገ መንግሥቱ ሁሉም ዜጐች ለልማት መሠረት የሆኑ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች፣ የምግብ ዋስትና፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ፣ የመኖሪያና የማህበራዊ ዋስትና የማግኘት መብት እንዲኖራቸው ይደነግጋል፡፡

እንዲሁም በደርግ ሥርዓት ማንኛውም ዜጋ ተገፍፎ የነበረውን የግል ንብረት ባለቤት የመሆን መብት ጠብቆ ሁሉም ዜጋ የግል ንብረት ባለቤትነት መብቱ በህገ መንግሥቱ እንዲከበር አድርጓል። ከሁሉም በላይ ህገ መንግሥቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የማይሸጥ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ንብረት እንደሆነ በግልፅ አስፍሯል፡፡

በመሬት ጉዳይ የሕዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት በጽኑ መሠረት ላይ ጥሏል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የሕዝብ ብቻ እንደሆነ ደንግጓል፡፡ የኢትዮጵያ አርሶና አርብቶ አደሮች መሬትን በነፃ የማግኘት፣ በመሬቱ የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብታቸው ህገ መንግሥታዊ ዋስትና አግኝቷል።

ዛሬ በኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ በማንኛውም የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ውስጥ የመሰማራትና ለመተዳደሪያው የመረጠውን ሥራ የመከወን መብት አለው። ሁሉም ዜጋ በመንግሥት ገንዘብ በሚካሄዱ ማህበራዊ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብቱ ተረጋግጦለታል። እነዚህ ሁሉ የግንቦት ሃያ ትሩፋቶች ናቸው፡፡

መላ ኢትዮጵያዊያን በሁሉም ዘርፎች በርካታ ድሎችን ጨብጠዋል። የድል ፍሬዎቹንም ማጣጣም ይዘዋል፡፡ ሕይወታቸው ተለውጧል። ከዚህ ማዕድ ላይ የሚያፈናቅላቸውን በዋዛ ያልፉታል ተብሎ አይጠበቅም።

በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች መሠረት ሕዝቦች የኑሮ ሁኔታቸው የመሻሻልና የማያቋርጥ ዕድገት የማግኘት መብት እንዳላቸው በተግባር እየታየ መጥቷል፡፡ በብሔራዊ ልማት የመሳተፍ፣ በሚቀረፁ ፖሊሲዎችና ኘሮጀክቶች ላይ አስተያየት የመስጠት መብት ዜጎች እንዳላቸውም በገሃድ ታይቷል።  

የልማቱ ዓላማ የዜጐችን ዕድገትና መሠረታዊ ፍላጐቶችን ማሟላት በመሆኑ መንግሥት የሚያወጣቸው ፖሊሲዎችና የሚያደርጋቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች የአገሪቱን ሕዝቦች ተጠቃሚነት መብት የሚያስከብሩ ስለመሆናቸው ከጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ዜጐች በመንግሥት ገንዘብ በሚካሄዱ አገልግሎቶች በእኩልነት የመጠቀም መብትታቸው ተረጋግጧል፡፡

ዜጐች ንብረት የማፍራት፣ በመረጡት የሥራ መስክ የመሰማራት መብቶች በማረጋገጥ በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት የሚመራ ፈጣንና ፍትሃዊ ልማት ማምጣት ተችሏል፡፡ ይህ ሁኔታም በህብረተሰቡ ውስጥ ያለመርካትና ይበልጥ ጠያቂ የመሆን መንፈስን ፈጥሯል፡፡ መንፈሱ ምንም ዓይነት ችግር የለውም፡፡ መንግሥትን ይበልጥ የሚያበረታታና የበለጠ እንዲሰራ የሚያደርግ ነው፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ የሀገራችን ህዳሴ እንቅፋት ይሆናል ተብሎ የሚታሰበውን ሙስናንና ኪራይ ሰብሳቢነትን አስተሳሰብና ድርጊት ከምንጩ ለማድረቅ ሲባል መንግስት የራሱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ሳይቀር በህግ ፊት በማቅረብ ቁርጠኝነቱን አሳይቷል። በዚህም አስተማሪ በሆነ መንገድ ትምህርት ለመስጠት ሞክሯል።

ምንም እንኳን የሙስና እና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ሊውል የሚችል ባይሆንም፣ ድርጊቱን በሂደት የመቅረፍ ስራዎች ተከናውነዋል። በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የበፊቱን ሁሉን አቀፍ ክንዋኔዎች የሚያጠናክርና አዳዲስ አሰራሮችን በመከተል ተግባሮቹን እየተወጣ ነው።

ባለፉት ዓመታት መልካም አስተዳዳርን ለማስፈን በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ህብረተሰቡን በተደራጀ መልኩ የማንቀሳቀስ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡ በተለይም በገጠሩ አካባቢ መልካም ውጤቶች ተገኝተዋል፡፡ እስሁን ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ ቢሆኑም አሁንም ጠንካራ ሥራ መከናወን እንዳለበት አይካድም፡፡

ልማታዊ ፖለቲካ ኢኮኖሚ መገንባትና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማዳከም የዛሬ 16 ዓመት ገደማ በተካሄደው የተሀድሶ መስመር ተግባራዊ መሆን ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ መልካም ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ ታዲያ አሁንም ልማታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ የበላይነት ያለው እንዲሆንና የግብርናና የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት የበለጠ መትጋት ያስፈልጋል፡፡

የህዝቡ ያለመርካት ጥያቄዎች አንዱ መነሻ ይኸው በመሆኑ መንግስት ይበልጥ እንዲበረታ ያደርገዋል፡፡ በአንድ በኩል በአገራችን የተፈጠረው አስደናቂ የልማት እድገት፣ በሌላው ወገን ደግሞ በልማት እድገቱ ምክንያት የተፈጠሩት ያለመርካት ሁኔታዎች ሁለት ተቃርኖዎች ሆነዋል፡፡

እነዚህን ተቃርኖዎች ለበጎ በመጠቀም ይበልጥ ተግተን መስራት እንችላለን፡፡ ማንኛውንም ተግባር ወደ በጎ እሳቤ የመለወጥ ባህሪይ ያለው የኢፌደሪ መንግሥት በህዝቡ ውስጥ እንዲፈጠር የፈለገው የጠያቂነትና ያለመርካት ስሜት መንግሥት ለበለጠ ሰላም፣ ለበለጠ ልማትና ለበለጠ የዴሞክራሲያዊ ግንባታ ሂደት የሚያነሳሳው ነው።

ልማታዊ ፖለቲካ ኢኮኖሚ መገንባትና ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማዳከም የዛሬ 16 ዓመት ገደማ በተካሄደው የተሀድሶ መስመር ተግባራዊ መሆን ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ መልካም ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ ታዲያ አሁንም ልማታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ የበላይነት ያለው እንዲሆንና የግብርናና የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማምጣት የበለጠ መትጋት ያስፈልጋል፡፡

የህዝቡ ያለመርካት ጥያቄዎች አንዱ መነሻ ይኸው በመሆኑ መንግስት ይበልጥ እንዲበረታ ያደርገዋል፡፡ በአንድ በኩል በአገራችን የተፈጠረው አስደናቂ የልማት እድገት፣ በሌላው ወገን ደግሞ በልማት እድገቱ ምክንያት የተፈጠሩት ያለመርካት ሁኔታዎች ሁለት ተቃርኖዎች ሆነዋል፡፡ እነዚህን ተቃርኖዎች ለበጎ በመጠቀም ይበልጥ ተግተን መስራት እንችላለን፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy