Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አስመስጋኙ ተግባር

0 367

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አስመስጋኙ ተግባር

                                                          ታዬ ከበደ

በአሁኑ ጊዜ አፍሪካ መሪዎች ሥልጣንን ላለመልቀቅ ሕገ መንግሥት እስከ ማሻሻል አሊያም ስልጣንን የሙጥኝ በማለት ለህዝብ እልቂት መንስኤ እስከመሆን በሚደረስበት ሁኔታ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኃላፊነታቸው ለመነሳት በገዛ ፈቃዳቸው መጠየቃቸው እርሳቸውንም፣ ድርጅታቸውንም የሚያስመሰግን ነው። ሁኔታውም አፍሪካ ውስጥ ያለው የሥልጣን አተያይ የቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ የአገራችን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የደረሰበትን ደረጃና የወደፊት ተስፋውን የሚያመላክት ነው ማለት ይቻላል። ጥያቄው በተለይ በበለፀጉት አገራት እንጂ በአፍሪካዊ መለኪያ አዲስና እንግዳ ቢሆንም አገራችን እንደ አፍሪካ ተምሳሌትነቷ በዚህ ረገድም ጅምር ሁኔታን እያሳየች ነው። ይህም እኛንም ይሁን አፍሪካን የሚያኮራ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ የኢፌዴሪ ህገ መንግስቱ በአንቀፅ ስምንት ላይ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸውንና ሉዓላዊነታቸው የሚገለፀውም በህገ-መንግስቱ መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ አማካኝነት እንደሚሆን ደንግጓል።

ይህ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ በግልፅ እንደሚያሳየው ማንኛውም የፖለቲካ ስልጣን የሚያዘው የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት በሆነው ህዝብ ይሁንታ ብቻ መሆኑን ነው። ህዝቡ ሲፈልግ ይሾማል፤ ሳይፈልግ ደግሞ ይሽራል። ይህን መብት ለህዝቦች የሰጡት ራሳቸው ህዝቦች ናቸው። ሌላ የትኛውም ወገን አይደለም። በዚህ ሁኔታ ውስጥ በህዝብ ይሁንታ ስልጣን የያዘው ገዥው ፓርቲ የራሱ ባህል ያለው ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስራ የመልቀቅ ጥያቄ ከዚህ ድርጅታዊ ባህል አንፃር የሚታይ ነው።

የእርሳቸው የመልቀቂያ ጥያቄ እዚህ ሀገር ውስጥ ግልፅነትና ተጠያቂነት እየጎለበተ መምጣቱንም የሚያሳይ ነው። እንደሚታወቀው መንግስት ሁሌም በአሰራሮቹ ላይ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የህዝቦችን ህገ መንግስታዊ ፍላጎት እውን ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህም በመሆኑ በየጊዜው ለህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የየወራት ስራዎቹን ያቀርባል። ያስገመግማል። መጠንከርና መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዩች ላይ የሚሰጡትን አስተያየቶችንም ይቀበላል።

የመንግስት የተጠያቂነት አሰራር የዴሞክራሲ አንዱ መገለጫ ነው። በዴሞክራሲ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት የሆነው ህዝብ አስተሳሰብ፣ በጊዜ ሂደት ለምርጫ የሚሰጠው ትርጉም የሚያድግና የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እንዲሁም እየሰፋ የሚመጣ ብሎም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በምርጫ የሚኖራቸው ተሳትፎ እየጎለበተ የሚሄድበት አውድ ነው። ይህ ተጨባጭ ሁኔታም በጅምር ላይ ያለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እና ረዥም ዕድሜን ያስቆጠረ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በምንም መልኩ አንድ ሊሆን እንደማይችሉ የሚያመላክት ነው።

እናም የሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ስንመለከተው ሂደቱ 26 ዓመታትን ብቻ ያስቆጠረ ጅምር በመሆኑ ምንም ዓይነት ተግዳሮቶች የሉበትም ለማለት የሚያስደፍር አይመስለኝም። አሁን የምንገኝበት ደረጃ የህዝብ አስተሳሰብ አድጓል፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳርም በሚፈለገው መጠን ሰፍቷል ለማለት አይቻልም።

እናም ሀገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው መንግስት የህዝቦች የዘመናት ጥያቄ የሆነውን ዴሞክራሲ በጥልቀት ማስፋትና ማጎልበት ይጠበቅበታል። የአሰራሩን ተጠያቂነትና ግልፅነት በዚያኑ ልክ ለህዝቡ ማረጋገጥ አለበት።

ዴሞክራሲ ሲጎለብት ይበልጥ አሳታፊ፣ ግልፅነት የተሞላበትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በበቂ ሁኔታ ሊያሳትፍ የሚችል ይሆናል። ይሁንና አንዳንድ ፅንፈኛ ሃይሎች መንግስት ዴሞክራሲን ለማስፋት ፍላጎት የሌለው አድርገው ሊስሉት ሲሞክሩ ይታያል። ይህ ስህተት ነው።

እንደሚታወቀው ሁሉ ገዥው ፓርቲ ከአምባገነኑ የደርግ ስርዓት ጋር ያደረገው መራርና እልህ አስጨራሽ ትግል የነበረው አንዱ ጉዳይ የዴሞክራሲ እጦት ነው። ደርግን አስወግዶ ስልጣን ከያዘም በኋላ ቢሆን፣ ይህን የህዝቦችን ጥያቄ ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለማከናወን ጥረት አድርጓል።

ገዥው ፓርቲ ገና ከስልጣን መባቻው ወቅት ጀምሮ የታጠቁና ወደ 17 የሚጠጉ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማወያየትና በማከራከር ባህሉ የሚታወቅ ነው። ይህም ዴሞክራሲን ለማስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው ለማስቻል ክርክርና ድርድር ማድረግ ለገዥው ፓርቲ አዲስ ጉዳይ አለመሆኑን የሚያሳይ ይመስለኛል።

እዚህ ሀገር ውስጥ ልማትንም ይሁን ዴሞክራሲን ለማሳለጥ የሚከናወኑ ማናቸውም ሁነቶች ማንንም ለማስደሰት አሊያም ለማስከፋት ሳይሆን የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የታገሉላቸውን መብቶች በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆመ ታስቦ የሚከናወን ተግባር መሆኑን መገንዘብ የሚገባ ይመስለኛል።

ስለሆነም  በገዥው ፓርቲም ይሁን በመንግስት በኩል የሚከናወኑ ጉዳዩች ሁሉ ለሀገርና ለህዝብ ጠቀሜታ ሲባል እንጂ፣ ለታይታ አሊያም ለሌላ ጉዳይ የሚከናወኑ አይደሉም፤ ሊሆኑም አይችሉም።

ያም ሆኖ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታችን መጠናከርና ማበብ ጤናማ እና ገንቢ ሚና የሚጫወቱ የፖለቲካ ፖርቲዎች መኖር አለባቸው። መንግስት በሀገሪቱ ዴሞክራሲን የሚያጠናክሩ ፖርቲዎች መኖር አለባቸው። ተደጋግሞ እንደሚነገረውም የመንግስት ፍላጐት የሀገራችን የመድብለ ፖርቲ ስርዓት ዳብሮ እና ጐልብቶ ማየት ነው። ይህ ፍላጎቱ በአሁኑ ወቅት እየታየ ካለው ትክክለኛ መንገድ በመነሳት እውን እየሆነ ነው ማለት ይቻላል።

እርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያምን ልናመሰግናቸው ይገባል። ምስጋናችን ህዝብና ሀገር የጣሉባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ለመወጣት ባሳዩት ቁርጠኝነት ነው። የድርጅቱን መርህ ተከትለውና ሀገር ለገጠማት ችግር የመፍትሔው አካል በመሆን ያሳዩት ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው።

በመሆኑም አቶ ኃይለማርያም ኢህአዴግ ያፈራቸው የህዝብ ልጅ ናቸው። ቅድሚያ ለራስ ሳይሆን ለሀገርና ለህዝብ በማሰብ በሀገራችን የተፈጠረው ችግር የመፍትሔ አካል ለመሆን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ባሳዩት የሚያኮራ ዴሞክራሲያዊ ምልከታ የሚመሰገኑ ናቸው።

እንደ እኔ…እንደ እኔ ጠቅይ ሚኒስትሩ አገራችን ውስጥ አዲስ የስልጣን ምልከታ እንዲኖር ያደረጉ ናቸው። ስልጣን የግለሰቦች ፍላጎት መገለጫና መጠቀሚያ ሳይሆን ሁሉንም ነገር ከአገር ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ የሚቃኝበት አንድ የስራ ስምሪት ዘርፍ መሆኑን አስተምረውናል። ስለሆነም እርሳቸው ቀደም ሲል የነበረውን የስልጣን የተሳሳተ አስተሳሰብን መስበር በመቻላቸው መመስገንና መወደስ አለባቸው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy