Artcles

ከመጸጸት በፊት

By Admin

March 29, 2018

ከመጸጸት በፊት

                                                               ይልቃል ፍርዱ

በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ የሰላም መደፍረሶችና ተከትሎ እየተደረጉ ባሉ ሕግና መስመርን ባለፉ ሁኔታዎች ላይ ይበልጥ ቤንዚን እያርከፈከፉ በለው ከማለት ይልቅ  በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭም ያሉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በጥልቀትና በስክነት ሊያስቡበት የሚገባው ግዜ ቢኖር ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡ ብዙሀኑ ዳያስፖራ ሰርቶ ለፍቶ አዳሪ ከመሆኑም ሌላ ዘወትር ለሀገሩ ሰላምና እድገት የሚያስብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ ባሕርማዶ ሁነው የማያባራ አታሞ በመደለቅ በሀገር ላይ እየታየ ያለውን የሰላም መደፍረስ ጥፋትና ወድመት እየደገፉና እያጀገኑ የበለጠ ጥፋትና ቀውስ እንዲደርስ ሲያበረታቱ ውለው ያድራሉ፡፡ ይህ የዜግነትና የሀገር ፍቅር የጎደለው ድርጊት ነው፡፡

በዚህ ስራ የተጠመዱ ጥቂቶች ባሕር ማዶ የተቀናጣና የተመቸ ሕይወት ውስጥ ተደላድለው እየኖሩ ቤተሰብ በድህነት በብዙ ልፋትና ድካም ያሳደጋቸውን ወጣት የሕዝብ ልጆች ለጥፋት በማነሳሳት ተግባር መጠመዳቸው በሌላው ደም የመቆመር ታላቅ አደጋ ነው፡፡ ለሀገርና ለሕዝብ መጨነቅ ማሰብ ሀገሬ ወገኔ ማለት እልቂትና ጥፋትን እየሰበኩ አይደለም፡፡ ይልቁንም ጥፋትን ባስወገደ መንገድ ሰላማዊ መፍትሄዎችን ማሰብ በውይይትና በመነጋጋር ችግሮች መልክ የሚይዙበትን መፍትሄ ማስገኘት ነበር ለሁሉም የሚበጀው፡፡

በአውሮፓና አሜሪካ ያለው አብዛኛው  ዲያስፖራ ለሀገሩና ለወገኑ ተጨናቂና አሳቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በሀገሩም በወገኑም ላይ ክፉ ነገር ማየትና መስማት አይፈልግም፡፡ ይሄው እውነት እንዳለ ሆኖ ሌሎች በአክራሪ ጽንፈኛነት የተሰለፉ ጥቂት ኃይሎች ደግሞ በሀገራቸው የከፋ ምስቅልቅል እንዲፈጠር፤ የነበረውና የቆየው የመቻቻል ባሕል እንዲጠፋ ብሔረሰብ ከብሔረሰብ እንዲጋጭ አልፎም በብሔር ላይ ያተኮረ የከፋ ቅስቀሳ በማድረግ መርዘኛ ተግባር ተጠምደዋል፡፡ በመሰረቱ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ሊወቀስ ሊከሰስ ሊወነጀል አይገባውም፡፡ከየትኛውም ብሔረሰብ የወጡ የተወሰኑ ግለሰቦች ሙሉ ብሔረሰቡን ሊወክሉ አይችሉም፡፡

ግለሰቦች የሚከተሉት አስተሳሰብም ሆነ የሚሄዱበት ፖለቲካዊ መንገድ የግድ የአንድ ድፍን ብሔር ወይን ብሔረሰብ አቋም ሊሆን አይችልም፡፡ በየትኛውም ማሕበረሰብ ውስጥ እንዳለውና እንደሚኖረው ሁሉ የተለያዩ እምነቶች፤ የፖለቲካ አተያዮች፤በፖለቲካውም ረገድ ቢሆን አደረጃጀቶች አሉ፡፡ ወደፊትም ይኖራሉ፡፡ ይህንን የዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ  መብት ጉዳይ በጥልቀት ማየትም የተገባ ይሆናል፡፡ አይደለም በአንድ ብሔር ብሔረሰብ ውስጥ ቀርቶ በአንድ ቤተሰብ ውስጥም ሰፊ የአመለካካት ልዩነቶች አሉ፡፡

በጅምላ መወንጀል በጥላቻ ማየት በሰው ሕይወት ላይ መፍረድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ እነዚህ ከቀደመው ትውልድ የተወረሱ ኋላ ቀር የፖለቲካ እኩይ አስተሳሰቦች በዘመን እድገትና ሽግግር ውስጥም ሊለወጡ አልቻሉም፡፡ ለሀገርና ለትውልድ ሲባል  ሊቀየሩ ሊለወጡ ግድ ይላል፡፡

በዚህ አካሄድ ሀገራችን በቀደሙት ዘመናት ብዙ መተኪያ የሌላቸውን ውድ ልጆቿን አጥታለች፡፡ በደርግ፤ በኢህአፓና በመኢሶን፤ በኦነግ፤ በሕወሐት፤ በነኢኮፓ በነኢጭአት በማሌሪድ በኃላም በኢድህን በሌሎችም ስመ ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ የነበሩት በሙሉ የአንድ ዘመን ትውልድ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡

በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ ከድሀው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ  ከአርሶአደሩ ከፋብሪካው ወዛደር ከመንግስት ሠራተኛው ከመምሕራኑ ከወታደሩ ወዘተ የተገኙ ቤተሰብ በብዙ ድካምና ልፋት ያስተማራቸው ለቤተሰባቸውም ለሕብረተሰባቸውም የተሻለ ልማትና እድገት ሊያስገኙ የሚችሉ ነበሩ፡፡ የአንድ ዘመን ትውልድ ነው በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እርስ በእርሱ ወደመጠፋፋት የተሻገረው፡፡

በግትርና የእኔ እውነት ብቻ ነው ትክክል በሚል ልዩነትን የዲሞክራሲ መገለጫ አድርጎ በማይወስድ ፖለቲካ ውስጥ ገብተው አንዱ ሌላውን በጠላትነት እየፈረጀ  መጨረሻቸው ተያይዞ መጥፋት ሆነ፡፡ በሁሉም ጎራ ተሰልፈው የወደቁት የዚህችው መከረኛ ሀገር ልጆች ናቸው፡፡ መደማመጥ መቻቻል ጠፍቶ፤ልዩነትን በልዩነት ይዘው በጋራ ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው መቆምና መስራት ሲችሉ ታሪካቸው በጥፋትና በውድቀት ተደመደመ፡፡ ዛሬ ይህ አይነቱ ታሪካዊ ስህተት ሊደገም አይገባውም፡፡ ከስህተት መማር አዲሱንም ትውልድ መታደግ ይገባል፡፡

በአብዛኛው ቡድናዊ እንጂ ሀገራዊ ራእይ ይዘው በጋራ ለመነጋጋር ለመወያያት ለችግሮችም መፍትሄ ማስቀመጥ ባለመቻል አንዱ ሌላውን በጠላትነት ሲፈርጅ የነበረበት  ለመግደል የሚሮጥበት በዚህም ብዙ ሕይወቶች የተቀጠፉበት ጥቁር ታሪክ ነው ያለፈው፡፡ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶች መቼም ቢሆን ይኖራሉ፡፡ የግድ ሁሉም ተመሳሳይ አቋም ይኑረው የሚል የለም፡፡ ዲሞክራሲ በልዩነት ውስጥም ቢሆን ተቻችሎ መኖር ነው፡፡ የሀሳብ ልዩነቶችን ማክበር ነው፡፡ በሚግባቡበት ተግባብተው በልዩነት ነጥቦች ደግሞ ተከባብሮ ተቻችሎ መቀጠል ነው፡፡

አንዱ ከቀድሞ ጀምሮ እስከዛሬ የዘለቀው ዘመን ያልሻረው ችግር ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች በሚባል መልኩ የእኔ መስመር ብቻ ትክክል ነው፤የሌላው ጸረ ሕዝብና ጸረ ሀገር ነው ፤አባላቱም ደጋፊዎቹም ጸረ ሕዝቦች ናቸው የሚለው በጥላቻ የተሞላ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ የሀገርና የትውልድ ውድቀት አስከትሎአል፡፡ ለመጠፋፋት በር ከፍቶአል፡፡ ትውልድና ሀገር የገደለው የትላንት በሽታ ተጋቦቱ ዛሬም ቀጥሎአል፡፡ የሀሳብና የአመለካካት ልዩነትና ብዝሀነት መኖር ይህንንም ማክበር ነው የዲሞክራሲ መሰረታዊነት፡፡

የተለየ አመለካከት በመያዝ የሚሰጠው ውንጀላ ስም ማጥፋት ነው አንዱ ዲሞክራሲን እየገደለ ከትላንቱ እስከዛሬው ትውልድ ተሻግሮ እየበከለ ያለው፡፡ የሁሉም የተለያዩ ድርጅቶች አስተሳሰብና ልዩነት በሀገሬ ጉዳይ ያገባኛል ብለው የሚይዙት መስመር ትክክል ነው ብለው የሚሉትን ሌላው ወገን ደግሞ ላይስማማበት ላይቀበለው ይችላል፡፡

ሆኖም ግን ጉዳዩ የጋራ ስለሆነችው ሀገር እስከሆነ ድረስ ልዩነትን በመከባባር ይዞ ከጥፋትና በጠላትነት በጥላቻ ከመተያየት ወጥቶ የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በሰላም አብሮ መስራት ይቻላል፡፡ ከቀድሞው ስህተት መማር ሀገርና ሕዝብ የማይጎዱበትን የሀገር ሀብትና ንብረት የማይወድምበትን ትውልዱ ከጥላቻ የሚወጣበትን መንገድ ማሰብ ነው የሚበጀው፡፡ በድሮ በሬ ያረሰ የለም እንዲሉ፡፡

በእልህ በጥላቻ በስሜታዊነት ተሞልቶ የሚኬድበት መንገድ መቸውኑም ለዚህች ሀገር የተረጋጋ ሰላምን አያመጣም፡፡ አሁን በሚታዩትና በማሕበራዊ ሚዲያ በሚተላለፉት የጥፋት መልእክቶች መንገድ መዝጋት፤ የነዳጅ ቦቴ አቃጥሉ፤ ኤልክትሪክ መስመር በጥሱ ወዘተ የሚሉት በቀጥታ በሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ በሕዝብ ላይ የከፋ ችግር ለመፍጠር የተወጠኑ እሳቤዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ድርጊቶች ተጎጂና ሰለባ የሚሆነው ሕዝቡ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ድርጊት ነው እነሶርያን ሊቢያን ኢራቅን ሌሎችንም ያወደመው፡፡

በእልህና በመተናነቅ በጥላቻ ፖለቲካ መመራት የመጨረሻው ምእራፍ የሀገርን መጥፋት የሕዝብን እልቂትና ስደት ነው የሚያስከትለው፡፡ ዛሬ ላይ እንደዋዛ የሚታየው የሀገር ነጻነት ተከብሮ መኖር እንዲያውም በልማት በእድገት ወደተሻለ ምእራፍ መሸጋጋር በቅጡ ካልተያዘ፤ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እየተቻለ የጥፋት አቅጣጫን ሙጥኝ ማለቱ በኃላ መመለሻ ከሌለው ጸጸት ውስጥ እንዳይከተን በስክነት ማሰቡ ይበጃል፡፡