Artcles

ከስልጣን ባሻገር

By Admin

March 01, 2018

ከስልጣን ባሻገር

                                                         ደስታ ኃይሉ

በአገራችን ህገመንግስታዊ ስርዓት መሰረት እየያዘ በመምጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትርን ያህል ባለስልጣን ከኃላፊነት ለመልቀቅ ጥያቄ ሲያቀርቡ ምንም ዓይነት ቀውስ አልተፈጠረም። ይህ የሚያመላክተው በህብረተሰቡ በገዥው ፓርቲ ላይ ያለውን ጠንካራ እምነት ነው።

በኢህአዴግ ውስጥ ግለሰቦች የራሳቸው የስምሪት ሚና ቢኖራቸውም፣ የእነርሱ መምጣትና መሄድ የሚያመጣው ምንም ዓይነት ቀውስ ሊኖር እንደማይችል ሁነኛ ማረጋገጫ ሆኗል። ይህም ዛሬ አገራችን ውስጥ ጠንካራ ህገ መንግስታዊ መሰረት ያለው ሥርዓት በመዘርጋት ላይ መሆኑን ያመላክታል።

ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን እንደ ችግር ጊዜ መውጫ አድርጎ መመልከት ከማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ሀገር የሚጠበቅ ነው። ለዚህም ሩቅ ሳንሄድ የዛሬ ዓመት ገደማ በሀገራችን አንዳንደ አካባቢዎች ተከስቶ የነበረውንና ሁከት ለመለወጥና ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እንድትመለስ በማድረግ ላይ የሚገኘውንና በህገ መንግሰቱ መሰረት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን መጥቀስ ይቻላል። ይህም ማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ሀገር ችግሩን በህገ መንግስቱንና በህገ መንግስቱ አግባብ ብቻ የሚፈታ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ታዲያ ይህን መሰሉ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስት ዕውን እንዲሆን በሙሉ ድምፁ ካፀደቀው ህዝብ በስተቀር ማንም ከመሬት ተነስቶ ሊጥሰው አሊያም እንዲቀር ሊያደርገው አይችልም። የራሱ የሆነ ህግና ስርዓት ያለው በመሆኑም በገዥው ፓርቲም ይሁን በተቃዋሚዎች ወደ ጎን ሊባል አይችልም። ከዚህ ይልቅ ህገ መንግስቱን ለሚፈጠሩ ነባራዊ ችግሮች እንደ መፍትሔ ማፍለቂያ መጠቀም ይገባል። በተለይም በአጎራባች ክልሎች ውስጥ ሰነከባለሉ በመጡ የተሳሳቱ አስተሳሰቦችና በግጦሽ ሳቢያ የሚፈጠቱ ችግሮችን በህገ መንግስቱ አግባብ መፍታት ይገባል።

እርግጥ በየትኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ ግጭት መቼም ቢሆን ሊጠፋ አይችልም። ሆኖም እንኳንስ የህዝቦች ንቃተ ህሊና እየተገነባና ይበል የሚያሰኝ ደረጃ ላይ እየደረሰ ባለበት በእኛ ሀገር ውስጥ ቀርቶ፤ በሥልጣኔ በበለፀጉ ሌሎች ሀገሮች ውስጥም ቢሆን ግጭት መኖሩ አይቀርም። ነባራዊ ክስተት ነው። ለነገሩ የሰው ልጅ ሰው ከራሱ፣ በአቅራቢያው ካለው ማህበረሰብና ከተፈጥሮ ጋር መጋጨቱም አይቀሬ ነው። ይህ በየትኛውም ዓለም ሊኖር የሚችል ግጭት ደግሞ በህግና በስርዓት መመራት ይኖርበታል። በተለይም ዜጎች በሙሉ ፈቃዳቸው ዕውን ባደረጓቸው መሰረታዊ የህገ መንገስት ድንጋጌዎች መፈታት ይኖርባቸዋል ብሎ ማመን ገቢ ነው።  

ዛሬ በመላ አገሪቱ የተረጋገጠው ሠላም የተረጋጋ ማኅበረሰብ እንዲኖር በማስቻሉ የኢትዮጵያ ሕዝቦችና መንግሥት መላ አቅማቸውን አቀናጅተው በድህነትና ኋላ ቀርነት ላይ መዝመታቸው የሥርዓቱ ስኬቶች አንዱ መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ከማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዙ መብቶች ስለተመለሱላቸው ሀገራቸውን ለመለወጥ እንደ አንድ ማኅበረሰብ በልማት አጀንዳዎች ላይ እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ህገ መንግስቱ የሰላም ዋስትና መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል፡፡  

እርግጥ እዚህ ሀገር ውስጥ በተለያዩ ወቅቶች የሚፈጠሩ ግጭቶችን አግባብ ባለው መንገድ ለመፍታት ሀገራችን የምትከተለው ህገ መንግስታዊ ሥርዓት ካለፉት ጊዜያት ጋር ፈፅሞ በማይገናኝ መልኩ ለችግሩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ሁኔታውን በመለወጥ ላይ ይገኛል። የሀገሪቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያላቸውን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ እንዲጠቀሙና ከሌሎች ህዝቦች ጋር በመተሳሰብ የጋራ ሀብታቸው እንዲሆን ማድረግ ችሏል።

ዳሩ ግን ያለፉት ሥርዓቶች በሀገሪቱ ህዝቦች ውስጥ ፈጥረውት ያለፉት የተዛቡ አመለካከቶች እንዲህ በቀላሉ በጥቂት ዓመታት በቀላሉ የሚቀየሩ አይደሉም— ሂደትን፣ ጊዜንና የአስተሳሰብ ለውጥን ይጠይቃሉ። ሆኖም አንዳንዶች ይህን እውነታ ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ጥላሸት ለመቀባት ቢሞክሩም፤ ስርዓቱ ከ23 ዓመታት በላይ ከእነርሱ እሳቤ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ህገ መንግስቱ ምላሽ እየሰጠ መጥቷል።

እንደሚታወቀው ማንኛውም ፌዴራላዊ ሥርዓት በአንድ ጀምበር የተገነባ አይደለም። በሂደቱ ውስጥ ተግዳሮቶች መኖራቸው አይቀርም። እናም በሂደቱ ውስጥ ጥቃቅን ስንክሳሮች ሊያጋጥሙት ይችላል። ዋናው ነገር እነዚህ ጊዜያዊ ችግሮች ህገ መንግስታዊ በሆነ አግባብ በብቃት እየተፈቱ በስርዓቱ መተማመን ላይ ነው።

ጥቂት ወገኖች ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የችግሮች መንስኤ አድርገው በመመልከት በተሳሳተ መንገድ ህገ መንግስቱን ሲቃወሙ ይታያሉ። እርግጥ ማናቸውንም ጉዳዩች መቃወም (ህገ መንግስቱን ጨምሮ) ይቻላል። ህገ መንግስታዊ መብትም ነው።

ዳሩ ግን ተቃውሞው መሰረት ያለውና በተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ የተመረኮዘ መሆን ይኖርበታል። ይህን ግን ከስሜታዊነትና ከጥላቻ በፀዳ ሁኔታ ማቅረብ የሚችል ያለ አይመስለኝም። ቢኖርም አብዛኛዎቹ ውንጀላዎች በማስረጃዎችና በመረጃዎች ላይ የተመሰረቱ አይደሉም። እናም መከራከሪያቸውን “እንዲህ ነው” ብሎ ማቅረብ ማቅረብ የሚችሉ አይመስለኝም። እንዲያው በደፈናው “ህገ መንግስቱ ሊቀየር ይገባል” ይላሉ።

ሆኖም የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አያሌ የሀገራችን ህዝቦች ውድ ልጆች ቤዛ የሆኑለት፣ አካላቸውን ያጡለትና ለተግባራዊነቱም የተረባረቡለት ነው። ይህ ዕውነታም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተስማምተው ያፀደቁትና የሉዓላዊ ሥልጣናቸው ምንጭ የሆነው ህገ መንግሥት እነዚሁ ህዝቦች እስካሉ ድረስ ፈራሽ የሚሆንበት ምንም ዓይነት ዕድል አለመኖሩን የሚያመላክት ነው።

ከዚህ ይልቅ የሀገራችን ህዝቦች በሙሉ ፈቃደኝነታቸው ያፀደቁት ህገ መንግስት፤ በሀገራችን ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን እየፈቱበት የሀገራችንን አስተማማኝ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲን ዕውን ለማድረግ በመፍትሔነት የሚጠቀሙበት መሳሪያ ሆኗል።

ይህ የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፍላጎት ልክ እንደ መቃወም መብት ሁሉ ህገ መንግስታዊ መብት ነው። ይህ መብትም በጥቂቶች ፍላጎት የሚቀለበስ ሊሆን አይችልም። እናም ህገ መንግስቱን የማሻሻልም ይሁን የመተው አሊያም የማፅናት መብት የሀገራችን ህዘቦች እንጂ የጥቂት ፅንፈኞች ፍላጎት ሊሆን አይችልም።

ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ከ23 ዓመታት በላይ ያጎናፀፈን ድሎች በርካታ ናቸው። የሀገራችን ህዝቦች አንደኛው የሌላኛውን መብት የማክበርና የመቻቻል ተግባሮች ተጠቃሽ ናቸው። በዚህም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በተጎናፀፉት ህገ መንግስታዊ መብት ሁለንተናዊ ዕድገታቸውን ማሳለጥ ችለዋል።

ይህ ተግባራቸውም የሀገራቸውን መፃዒ ዕድል የሚወስን በመሆኑም፤ እንዳለፉት ጊዜያት ሁሉ የሚፈጠሩ ችግሮችን ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን መሰረት በማድረግ በመፍታት ቀጥለዋል። ይህ እምነት በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ሲያቀርቡ ህብረተሰቡ ተረጋግቶ ስራውን እንዲቀጥል አድርጎታል። ይህም በሂደት አገራችን ውስጥ የተፈጠረው ህገ መንግስታዊ ስርዓት አስተማማኝ መሰረት ያለው መሆኑን የሚያስረዳ ይመስለኛል።  