Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከደባው ራሳችንን እንታደግ

0 279

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከደባው ራሳችንን እንታደግ

                                                         ታዬ ከበደ

አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች የአስኳይ ጊዜ አዋጁን ምክንያት በማድረግ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ሆን ብለው የመሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት እንደተፈጠረ በማስመሰል ዋጋ በመጨመር ደባ እያከናወኑ ነው። በአዋጁ ምክንያት ምንም ዓይነት እጥረት እንደማይፈጠርና የነበሩት ማናቸውም ግብይቶች ሳይስተጓጎሉ በነበሩበት እንደሚቀጥሉ ይተወቃል። የስግብግብ ነጋዴዎች ተግባር ህገ ወጥ ነው። ይህ ህገ ወጥ ተግባር በአዋጁም የተከለከለ ስለሆነና ተጎጂውም ህብረተሰቡ ራሱ በመሆኑ የተግባሩን ፈፃሚዎች ለህግ አሳልፎ በመስጠት ይኖርበታል። ይህ ተግባርም ራስን ከደባው በማዳን ከብዝበዛ መከላከል  ነው።    

እንደሚታወቀው ሁሉ መንግስት ባለፉት ዓመታት የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ምላሹ እጅግ ፈጣን ነበር። እዚህ ላይ በምርቶች ላይ በታየው የዋጋ ንረት የመንግስትና የህዝቡ ስሜትና ፍላጎት አንድና አንድ ነበር በምልበት ጊዜ፤ የችግሩ መፈጠር “ጮቤ” ያስረገጣቸው ኃይሎች ጥቂትም ቢሆኑም ጭርስኑ አልነበሩም እያልኩ ግን አይደለም፡፡

በገበያው ውስጥ ያጋጠመው ጊዜያዊ አለመረጋጋት አስቦርቋቸው የነበሩ ኃይሎች እነማን መሆናቸው ጉዳዩ ውሎ አድሮ ገሃድ ሲወጣ ያስተዋልነው ሃቅ ነውና። ከእነዚህ ውስጥ አንድ ጊዜያዊ ችግር በተከሰተ ቁጥር ተገቢ ያልሆነ ትርፍ ለማጋበስ የሚቋምጡ ነጋዴዎች ይጠቀሳሉ። ይህ ሁኔታ በአንድ በኩል የሀገራችንን የነፃ ገበያ ስርዓት መከታ በማድረግ እናዳሻቸው ትርፍ ለማግኘት የሚከጅሉ ቡድኖች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል።

እንደሚታወቀው ሀገራችን በተመረጡ መስኮች የመንግስት ጣልቃ ገብነት ባለው የነጻ የገበያ ሥርዓት መመራት ከጀመረች ከ25 ዓመታት በላይ ዕድሜ በላይ አስቆጥራለች፡፡ ይህም በሃገር ውስጥ ፈጣን፣ ዘላቂ፣ ተወዳዳሪና ፍትሐዊ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ያስቻለ ነው።

ሸማቹም ሆነ አምራቹ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የንግድ ልውውጡን እንዲያካሂዱ ሙሉ ነፃነት የሰጠ ስርአት ከመሆኑም ባሻገር፤ ልማታዊ ባለሃብትን በጥራትና በብዛት እንዲፈጠርም የማይተካ ሚና ተጫውቷል፤ በመጫወት ላይም ይገኛል። መንግስትም የነጻ ገበያ ሥርዓቱን ከመዘርጋት ጀምሮ ስር እንዲሰድ በማድረግ በኩል የአንበሳውን ድርሻ ይዞ ችግሩን በቁርጠኝነት እየተወጣ ይገኛል።

ይሁን እንጂ በነጋዴው ውስጥ በመሸጉ ኪራይ ሰብሳቢዎች አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ልክ እንደ አሁኑ ዋጋን ያንራሉ። በሌለ የምርት እጥረት ገበያውን ለመመረዝይ ይሯሯጣሉ። እንደሚታወሰው በንግድ ሥርዓቱ ላይ ያለመረጋጋት ችግር መታየት በጀመረበት ወቅት በሁሉም የምርት ዓይነቶች ላይ የተከሰተ የዋጋ ንረት አልነበረም፡፡ ሊከሰትም አይችልም ነበር።

መንግስት ከራሱ ካዝና ደጉሞ የሚያስገባቸው እንደ ስኳር ዘይትና የመሳሰሉት መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ያለ አንዳች ምክንያት በእነዚሁ ስግብግብ ነጋዴዎች ዋጋቸው ይጨምራል።

ሆኖም መንግስት እነዚህን ጉዳዩች በመገንዘብ እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ አላለም።  ይህ ደግሞ የመንግስትን ሩቅ አሳቢነት አጉልቶ የሚያሳየን ሃቅ ነው፡፡ መንግስት ለጊዜያዊው ችግር መፍትሄ ያላቸውን እርምጃዎች በመውሰዱ በገበያው ውስጥ እፎይታ ሊፈጠር ችሏል። ይሁን እንጂ መንግስት ችግሩን ለማቃለል በሚረባረብበት ወቅት ከመንግስት አስተሳሰብ በተቃራኒው የቆሙ ስግብግብ ነጋዴዎች በችግሩ ላይ ነዳጅ ለማርከፍከፍ ከመረባረብ አልቦዘኑም።

በእርግጥ እነዚህ ኃይሎች ጥቂቶች ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሊያደርሱ ከሚችሉት ጥፋት አንጻር ሲመዘኑ ግን ቀላል ግምት የሚሰጣቸው አይደሉም፡፡ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም ያላቸው ከመሆናቸው ባሻገር፤ በገበያው ውስጥ ስር የሰደደ ትስስርም ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ አቅሞቻቸውን በማስተባበርም ከፍተኛ ጥፋት ለማስከተል ሲረባረቡ ይስተዋላል፡፡

በአንድ በኩል ምርቶችን በመደበቅ በገበያ ውስጥ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ፤ በሌላም በኩል ደግሞ ልማታዊ ነጋዴው በሚያዋጣው ዋጋ እንዳይሸጥ ተፅዕኖ ለመፍጠር መጠነ ሰፊ ዘመቻም ያካሂዳሉ፡፡

እነዚህ ስግብግብ ነጋዴዎች የዘረጉት የጥፋት መዋቅር በአዲስ አበባ አሊያም በጥቂት የክልል አካባቢዎች ብቻ የታጠረ ላይሆን ይችላል፡፡ እስከ አርሶ አደሩ ድረስ ዘልቆ በመግባት ተፅዕኖ የሚያደርሱ ናቸው፡፡ አርሶ አደሩ ምርቱን ወደ ገበያ እንዳይወጣ የሃሰት ፕሮፓጋንዳን በመንዛት፣ ነጋዴውም ምርቱን እንዲሰውርና አጋጣሚውንም ተጠቅሞ የእጥፍ እጥፍ ትርፍ እንዲያገኝ ውስጥ ለውስጥ ቅስቀሳ ከማካሄድ ይቦዝናሉ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ባለፉት ጊዜያት የታዩት እውነታዎች የሚነግሩን እነዚህን እውነታዎች ነው።

እነዚህ ስግብግብ ነጋዴዎች በሚያደርጉት የተፈጠረው የገበያ አለመረጋጋት ዞሮ ዞሮ  የሚጎዳው ህብረተሰቡ ነው፡፡ በዚህ ወቅት መንግስት በገበያ ውስጥ የተፈጠረው ጊዜያዊ አለመረጋጋት እየተባባሰ ከመሄዱ በፊት የነጻ ገበያ ሥርዓቱን በማይጎዳ መልኩ የህዝብን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ አማራጮችን በመፈተሽ እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

መንግስት የዋጋ ንረትን ለመከላከል ባለፉት ጊዜያት ልዩ ልዩ ጠቃሚ እርምጃዎችን በመውሰድ ህዝብ ተኮር ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ እነዚህ እርምጃዎችና ተግባራት የዋጋ ንረቱ በዜጎች ህይወት ላይ ጫና እንዳያስከትል አስተዋጽኦ የነበራቸው መሆኑ አይካድም፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ እንደሚታወቀው በተለያዩ ወቅቶች መንግስት የዋጋ ግሽበትን ለማረጋጋት ተከታታይ የሆኑ ልማታዊ እርምጃዎችን በመውሰድ የህዝቡን ጥያቄ መልሷል። የዋጋ ግሽበቱ ባለ ሁለት አሃዝ በነበረበት በዚያ ወቅት፤ ህብረተሰቡ እንዳይጎዳ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የፍጆታ ዕቃዎችን ራሱ በማስገባትና በሸማቾች ማህበራት አማካኝነት አከፋፍሏል።

እንዲሁም ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገዛበትን እንደ የጅምላ መሸጫና የሸማቾች ማህበርን በማደራጀት የህዝቡን ጥያቄዎች የመለሰና በመመለስ ላይ የሚገኝ መንግስት ነው። ይህም የኢፌዴሪ መንግስትን ህዝባዊነትና ሁሌም ቢሆን ለህዝቡ የገባውን ቃል የማያጥፍ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

እርግጥ ቀደም ሲል የጠቀስኳቸው ምሳሌዎች እጅግ ከሚበዛው የመንግስት ተግባራት ውስጥ ጥቂቶቹን ነው። ምንም እንኳን እነዚህ መንግስታዊ ህዝባዊነት ምሳሌዎች ቢሆኑም፤ ዋናውንና መንግስት ለህዝቡ የገባውን ቃል የማያጥፍና ሁሌም ተግባሮቹን የሚያከናውነው ህዝቡን ጥያቄ ተነስርቶ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። እንደ ነዳጅ የመሳሰሉ ምርቶችን የመደጎምና እጥረት ያለባቸውን ንብረቶች ከውጭ ጭምር ገዝቶ በማስገባት እያደረጋቸው ያሉት ተግባሮች የማረጋጋት ስራውን እጅግ ያገዙ ናቸው።

ይህ መንግስታዊ ጥረት ባለበት ሁኔታ ያለ አንዳች የመሰረታዊ ሸቀጦች እጥረት ገና ለገና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል በማለት አንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች ህብረተሰቡን ለመበዝበዝ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን መቃወም ይገባል። ምክንያቱም በአስቿይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ህጋዊነት ይበልጥ ይጨምራል እንጂ ከተለመደው ግብይት ውጭ የሚፈጠር ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ነው። በመሆኑም ስግብግብ ነጋዴዎች የሚፈፅሙትን ደባ በመጋለጥ ለህግ የማቅረብ ስራ የሁሉም ዜጋ መሆን አለበት።       

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy