Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የክልሉ ወጣቶች ለሚያነሷቸው ችግሮች ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት አቋም ተይዟል-ብአዴን

0 1,217

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ባካሄደው ግምገማ የክልሉ ወጣቶች ለሚያነሷቸው ችግሮች ፈጣንና ተጨባጭ መፍትሄ ለማበጀት አቋም መያዙን  የንቅናቄው ሊቀ-መንበር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሶስት ሳምንታት ግምገማ አካሄዷል።

የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የፌደራል ስርዓት፣ የማህበረሰብ ችግርን ለመፍታት የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎች፣ ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ያለበት ሂደት እንዲሁም የአደረጃጀት ውጤታማነት በግምገማው የተዳሰሱ አበይት ጭብጦች መሆናቸው ተገልጿል።

አገሪቷ በፈጣን ለውጥና ሽግግር ውስጥ አንደምትገኝ  የተናገሩት ሊቀመንበሩ፤ በተለይ የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል የመንግስትንና የህብረተሰቡን የተቀናጀ ተግባር የሚፈልግ መሆኑን አውስተዋል።

በክልሉ ውስጥ አሁንም ቢሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በድህነት ውስጥ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ “ይህን የከፋ ችግር መለወጥ ደግሞ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም” ነው ያሉት።

ብአዴን ከዚህ አንጻር ተራማጅ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ ማስቀመጡንም ጠቁመዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን  “ወጣቶች የሚያነሷቸው ችግሮች ተጨባጭና ተግባራዊ ምላሽ አንደሚጠይቁ” ተናግረው፤ ድርጅቱ ባከናወናቸው ተግባራት አሁንም ቢሆን ሰፊውን ወጣት አንዳላረካ ጠቁመዋል።

የወጣቶችን ችግር ለመፍታት የክልሉ መንግስት ከሚያከናውነው ተግባር በተጨማሪ ወጣቶች እራሳቸው የመፍትሄው አካል መሆን አንደሚገባቸውም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

ድርጅቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በሚፈለገው ደረጃ አለመስራቱን የገለፁት አቶ ደመቀ፤ በቀጣይ የተጀመሩ መሰል ተግባራት ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዘቦችን ባማከለ መልኩ መሰራት አንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል።

ብአዴን ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆችን በክልሉ ልማት ውስጥ ተሳታፊ ለማድረግ ከኢህአዴግ እህትና አጋር ደርጅቶች ጋር የጀመረውን በቅንጅት የመስራት ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ድርጅቱ በቀጣይ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታውን ለማጎልበት ከምሁራን፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎችና ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሰራም ሊቀመንበሩ ገልጸዋል።

የግምገማ ሂደቱን ደረጃ በደረጃ እስከታችኛው አመራር ድረስ በማውረድ ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት እንደሚሰራም አውስተዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy