Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የወጣቶች ተሳትፎ እንዲጎለብት…

0 435

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የወጣቶች ተሳትፎ እንዲጎለብት…

ዳዊት ምትኩ

ባለፉት ስድስት ወራት ከወጣቶች ተጠቃሚነት ከ882 ሺህ ለሚበልጡ የከተማና የገጠር ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል። ይህም ከተያዘው እቅድ አንጻር 68 በመቶ ብቻ ነው። ለዚህም በዋናነት በሀገሪቱ የተከሰተው የፀጥታ ችግር፣ የአስፈጻሚ አካላት ቅንጅትና የመፈፀም ድክመት እንዲሁም የወጣቶች ተሳትፎ ማነስ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል። ያም ሆኖ በቀሪው ግማሽ የበጀት ዓመት የአፈጻጸም ጉድለቱን ለማካካስ በዋነኝነት ሰላምና መረጋጋትን ማጠናከር እንደሚገባ እንዲሁም ወጣቶች ለሥራ ፈጠራ ትኩረት ሰጥተው ተሳትፏቸውን ማሳደግ ይኖርባቸዋል።

የማስፈፀም አቅም ችግር የማንኛውም በማደግ ላይ ያለ አገር ችግር ቢሆንም ተግዳሮቱ ችግር የማይሆንበት ደረጃ ማድረስ የመንግስትና የተጠቃሚው አካል የጋራ ቅንጅታዊ ስራ ወሳኝ ነው። መንግስት ከወጣቶች ጋር በመሆን የጀመረውን ሰላምና የማረጋጋት ስራዎችን መከወን ይኖርበታል። ምክንያቱም ሰሞኑን በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች የታየው ስርዓት አልበኝነት ተግባር እንዳይከናወን የሚያደርገው ይመስለኛል።

ፌዴራላዊ ሥርዓታችን በህዝቦች መስዋዕትነት በመረጋገጡ የአገራችን ወጣቶች በማንነታቸው መኩራት መቻላቸውን፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንዲማሩ፣ እንዲዳኙና አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዲሄዱ ብሎም በአገሪቱ ማናቸውም የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ተጠቃሚነታቸው እየጎለበተ መሄዱን፣ መንግስት ባመቻቸላቸው የገንዘብ አቅርቦት ራሳቸውን ጠቅመው አገራቸው የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ እያሳለጡ ይገኛሉ።   

እንደሚታወቀው ሁሉ ወጣቶች ባለፉት 16 የፈጣን ዕድገት ዓመታት ውስጥ የመንግስት ልማታዊ አቅጣጫን በሚገባ ተገንዝበዋል። ማንኛውንም ጊዜያዊ ችግር መንግስት እየፈታው ነው።

እንደ ኦሮሚያ ባሉ ክልሎች ውስጥ ማልማት ካልቻሉ ባለሃብቶች ቦታ በመቀማት ጭምር ወጣቶችን ወደ ስራ የማስገባት ተግባር እያከናወነ ነው። ውጤትም እየተገኘበት ነው። ይህን ሁኔታ ለማጎልበት ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ አለባቸው። ለዚህም መንግስት በሚያከናውናቸው የሰላምና መረጋጋት ስራዎች ውስጥ በጉልህ ተሳታፊ መሆን አለባቸው። ወጣቱ የውስጥና የውጭ የአመፅና የጥላቻ ጥሪዎችን በሁለት ምክንያቶች ማምከን ያለበት ይመስለኛል፡፡ አንደኛው፤ መንግሥት የሚከተለው ልማታዊ አቅጣጫ ማንኛውንም ጊዜያዊ ችግሮች የመፍታት አቅም ያለው ስለሆነ ነው፡፡

ሁለተኛው ደግሞ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የገነባውን ቃል የማያጥፍ መሆኑን ባለፉት ጊዜያት በተግባር ስለሚያውቀው ነው፡፡ ወጣቱ ሚዛናዊና ፍትሃዊ አስተሳሰብ ያለው በመሆኑ፤ በሁከት ፈጣሪ ሃይሎች አማካኝነት የሚቀርቡ “ጎስም ነጋሪት፣ ክተት ሰራዊት” ዓይነት የጥፋት እንዲሁም ፀረ-ልማት ጥሪዎችን አይቶ እንዳላየ፤ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ ማለፍ ይገባዋል፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ ወጣቱ ባለፉት 16 የፈጣን ዕድገት ዓመታት ውስጥ የመንግሥት ልማታዊ አቅጣጫን በሚገባ ይገነዘባል፡፡ እናም ማንኛውንም ጊዜያዊ ችግር መንግሥት እንደሚፈታው ማመን ያለበት ይመስለኛል። እናም ችግሩን በመቋቋም ወደ ዘላቂው መፍትሔ መግባት ያለበት ይመስለኛል፤የሁከት ኃይሎች መጠቀሚያ ከመሆን የሚገኝ ነገር የለምና።

ምንም እንኳን ወጣቱ በአሁኑ ወቅት ስልጣንን ለግል ጥቅማቸውና ለኑሮ ማደላደያነት ለማዋል በሚሹ ኃይሎች አማካኝነት የተፈጠረ ችግር ቢኖርበትም፤ ችግሩ በሀገሪቱ በመመዝገብ ላይ የሚገኘው ልማታዊ ድል ጊዜያዊ እንቅፋት መሆኑን መረዳት ያለበት ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ባሻገርም፤ የመንግሥትን የለውጥ ኃይልነት ስለሚያውቅ፤ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ እንደማይወጣና እንደሚለወጥም ማመን ይኖርበታል፡፡

እርግጥ አንድ መንግሥት ወይም የፖለቲካ ድርጅት በባህሪው ህዝባዊ ከሆነ፤ የሚያከናውናቸው ማናቸውም ተግባራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያማከሉ መሆናቸው አይቀርም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም በባህሪው ህዝባዊና ልማታዊ በመሆኑ፤ ላለፉት 26 ዓመታት በአብዛኛዎቹ መስኮች ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች በተለያዩ የስራ መስኮች ተደራጅተው ተጠቃሚ መሆናቸውን ማንሳት ይቻላል። እናም ወጣቱ በአሁኑ ወቅት የላቀ ተጠቃሚ ለመሆንም ቁርጠኛ አቋም ከመንግስት ጋር መስራት ያለበት ይመስለኛል፡፡

 

ከድህነት ጋር ፍልሚያ ገጥሞ ተጠቃሚ እየሆነ ያለው ወጣት፤ በምንም ዓይነት ምክንያት ሁለንተናዊ የጥቅም ተጋሪነቱ የኋሊት ተጎትቶ እንዲሸረሸርበት አይፈልግም፡፡ ነገ ትልቅ የዕድገት ባለቤት ለመሆን ያለመው ወጣት ዜጋ፤ ትኩረቱን ማድረግ ያለበት የትናንት እሱነቱን በስራ ለመቀየር ደፋ ቀና በማለት እንጂ፤ ሁከትን በማዳመጥ አይደለም፡፡

እናም እነርሱ ባህር ማዶ ሆነው ልጆቻቸውን በሰላም እያስተማሩ እዚህ ሀገር ውስጥ ያለውንና ህይወቱን ለመቀየር እየተጋ ያለውን ወጣት በእሳት ለመማገድ የሚሹ የሁከት ኃይሎችን ጥሪዎች ማምከን ይኖርበታል። ወጣቱ ከሁከቱ ወዲህ ስለ እነዚህ ኃይሎች ባዶና የአሉባልታ አጀንዳ አራማጅነት እንዲሁም ስለ መንግሥት ትክክለኛነት የልማት አቅጣጫዎች መገንብ አለበት።

ምንም እንኳን የሁከት ኃይሎቹ በተቀናጀ ሁኔታ የህዝቡን ብሶቶችና የራሳቸውን አሉባልታዎች በማያያዝ አያ ለማራገብ ቢሞክሩም እንዲሁም ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረኑና የሚምታቱ ፀረ-ልማት ሃሳቦችን እያቀረቡ ለማሳሳት ቢሞክሩም ወጣቱ ጆሮውን ሊሰጣቸው አይገባም።

የማናቸውም ችግሮች መፍትሐሔ የሚመነጨው በሀገሪቱ መንግስት እንጂ የራሳቸውን አጀንዳ ለማራመድ ብሎም የሌሎች ፀረ-ኢትዮጵያ ሃይሎች ተላላኪ በመሆን በህዝቦች ስቃይ ትርፍ ለማጋበስ በሚፈልጉ ኃይሎች ባለመሆኑ ሃቁን መገንዘብ ይኖርበታል።

በመሆኑም መንግሥት የአዳዲስ ልማታዊ ሃሳቦችና አሰራሮች አመንጪ ብሎም ለወጣቱ ችግር የሚደርስ ህዝባዊ አካል መሆኑን ወጣቶች ሁሌም አለባቸው። በመንግስት በኩልም የወጣቱ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት መደረግ አለበት። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የታዩ ህገ ወጥ ተግባሮች እንዳይፈፀሙ በቀሪዎቹ የበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት አፈፃፀሙን በማሻሻል የወጣቶች ተጠቃሚነት እንዲጎለብት መስራት ይኖርበታል።

ወጣቱም ቢሆን ወጣቱ ስራ ፈጣሪ እንጂ ስራ ጠባቂ ሊሆን አይገባም። የፌዴራል መንግስትና ክልሎች ወጣቱ በስራ ውስጥ እንዲያልፍ ጥረት እያደረጉ ነው። በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ውስጥ የተመቻቸ የስራ ምህዳር አለ። ዋናው ነገር ይህን ምቹ የስራ ድባብ በፈጠራ ክህሎት አጅቦ እንዴት ውጤታማ ማድረግ እንደሚቻል ማወቁ ላይ ነው። በመሆኑም አንድነት ኃይል ነውና በቅድሚያ ተደራጅቶ አዋጪ ስራን መምረጥ፣ የተገኘን ባጀት በስራ ላይ ብቻ ማዋል፣ እንደ አንድ ሆኖ ማሰብ፣ በተመረጠው ስራ ላይ በእኔነት መንፈስ መንቀሳቀስ እንዲሁም ከተጀመረው ስራ የሚገኝ ትሩፋትን በቁጠባና አግባብ በሆነ መንገድ ብቻ መጠቀም ከወጣቱ የሚጠበቁ ተግባሮች ናቸው። ስለሆነም ይህ አገር ተረካቢ ትውልድ በመንግስት በኩል የተዘጋጀለትን ስራ አጥነትን የመቅረፍ ተግባር መጠቀም አለበት። ይህ የሚሆነው ግን ራሱን ለስራና ለስራ ብቻ በማዘጋጀት መሆኑን ሊያውቅ ይገባል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy