Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የገነገነው  ፀረሰላም ንቅናቄ…!

0 450

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 

የገነገነው  ፀረሰላም ንቅናቄ…!

 

ነጻነት አምሃ

 

ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተገኙ  ኢኮኖሚ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስክቶች የህዝቡን ተጠቃሚነት በየደረጃው እያረጋገጡ የመጡ ቢሆንም መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ አንፃር ሙሉእነት በማጣታቸው የተነሳ የህብረተሰቡን ጥያቄ ሙሉበሙሉ መመለስ ያልተቻለበት ሁኔታ እንዳለ መገንዘብ ይቻላል።  በዚህ ወቅት አገሪቱ ያለችበት የእድገት ደረጃ ቆመን ብለን ቅድመ ደርግና ድህረ ደርግ ያለውን ለውጥ ማስተዋል ከቻልን መጠነሰፊ ለውጥ መመዝገቡን መገንዘብ እንችላለን። ለዚህ ፈርጀበዙ ስኬት ዋናው መሰረት ደግሞ በአገሪቱ አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ መሆኑን በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል።

 

በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ባይኖር ኖሮ የተመዘገቡ ዘርፈብዙ ለውጦች እውን መሆን እንደማይችሉ አያጠራጥርም። ከወታደራዊ መንግስት መደርመስ በህዋላማ አገሪቱ ያጋጠሟት የተለያዩ ችግሮችን ?ሕብረተሰቡን  በማሳተፍ እየፈታች መምጣቷ ይታወቃል። ከዚሁ ጎን ለጎን ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ፍትሃዊ ልማት በማረጋገጥ ህዝብን በየደረጃው ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለበት ሁኔታ ተፈጭጥሯል።

 

ይሁን እንጂ መንግስት በሙሉእነት መፈፀም ያልቻለው ነገር  መልካም አሰተዳደርን ማስፈን ነው። መልካም አስተዳደር በአገልግሎት አሰጣጥና በልማት ፍትሃዊነት ለይተን ስናየው የሁለተኛው በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ የመጣ ቢሆን በመጀመሪያ የተገለጸው ግን አሁን በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል። የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ለወጣቱ ፍትሃዊ የስራ እድል ከመፍጠር ጋርም ይያያዛል።    

 

ከህዝቡ በተለያየ ጊዜ እየተነሱ የነበሩ ችግሮችን በመውሰድ ይህ ችግር ደግሞ በአንድ ወገን ጫና የመጣ በማስመሰል በህዝቦች መካከል መቋጫ የሌለው   ደም መፋሰስና እልቂት ለመፍጠርና በአገሪቱ የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ልማት ለማደናቀፍ ዓላማ አንግበው እየሰሩ ያሉ ወገኖች ይህንን የህዝብ ሰላማዊ ጥያቄ  ወደራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ በማዞርና ወጣቱን በማወናበድ በዚች አገር የተረጋጋ ህይወት እንዳይኖረ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

 

መላው የአገሪቱን ብሔሮች ብሕረሰቦችና ሕዝቦች በማስተባበር ታላቁን የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ ልማት መሰረት የሆነውን የአገሪቱን ሰላም በማደፍረስ ሁከትና ብጥብጥን ለመፍጠር የዝቦችን አንድነት የማይሹ  ወገኖች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየገነገነ በመምጣቱ የዜጎች በሰላም ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የመዘዋወር ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድረገዋል።

 

ይህ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ  የተገነቡ የልማት አውታሮችን እስከ ማውደም የደረሰ  ስርዓት አልባ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር የሚያፋልስና የሚያናጋ መስመር በመሆኑ መንግስት ይህንን የማስታገስ ሃላፊነቱን መወጣት የግድ ብለሎታል።

 

በተለይ ማንነትን መሰረት ያደረገ ግጭትና ሁከት ለመፍጠር በሚንቀሳቀሱ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚኖሩ ቡድኖች እየተደረገ ያለው የጥፋት ዘመቻ የተነሳ በግንባታ ላይ ያሉ ትላልቅ የልማት አውታሮችን ማደንቀፍ የሚችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሱ መንግስት ህግንና ሰላምን የማስከበር ሃላፊነቱ በተገቢው መልክ መወጣት ስላለበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።

 

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ  እንዳይሆን የተለያዩ መሰናክሎች ያጋጠሙ ቢሆንም መንግስት እነዚህን በትግስት በማለፍ አዋጁ ከህዝብ ጋር በመተባበር ተግባራዊ እያደረገው ይገኛል። የአዋጁ ዋና ዓላማ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥና ሰላምን ለማረጋገጥ ሲሆን በተገቢነቱም ከጸረ ሰላም ሃይሎች በስተቀር መላው ሰላም ወዳድ የኢትዮጵያ ህዝብ ተገቢነቱ አመኖበት እየተተገበረ ይገኛል።

 

ተሰባጥሮ የሚኖር ከሰባ አምስት በላይ ብሔሮች ብሕረሰቦችና ሕዝቦች ባላት አገር  የእርስ በርስ ግጭትና ሁከትን መፍጠርና ዜጎች በማንነታቸው ብቻ የሚደበደቡበት የሚገደሉበትና ንብረታቸው የሚወድምበት ሁኔታ መከሰቱ አገሪቱን ወደ መበታተን የሚያመራት በመሆኑ ይህንን የማስቆምና መልክ የማስያዝ ተገቢነት አያጠራጥርም።  ለዚህም ነው መንግስት አዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንዲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክርብት አስጸድቆ በሰራ ላይ እንዲውል እያደረገ ያለው። ከዚህ አካያ የአስቸካይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም።

 

አዋጁ ከሁሉም በፊት ሰላምን የማረጋገጥና የዜጎች ከአንደ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመዘዋወርና የመስራትም ሆነ  የመኖር መብት የማስከበር ዓላማ ያለው ነው። ዜጎች በወጡበት ደመከልብ ሆኖ ከመቅረት ለመታደግ የሚያስችልም ነው። ይህ አዋጅ ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የተጀመረው ፈጣን ልማት በማስቀጠል ሕዝቦች በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ መፍጠርን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ እሙን ነው።

 

ሰላም ከሌለ ልማት የሚታሰብ አይደለም። ልማት ከልለ ደግሞ ሰላምና ተረጋጋ ህይወት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም። በመሆኑም የመጀመሪው አንገብጋቢ ጉዳይ ሰላምን ማስፈን የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና የዜጎች ደህንነትን ማስጠበቅ እንደሆነ እሙን ነው።  ሰላምን በማረጋገጥ የተጀመረውን ተስፋ ሰጪ ልማት ማስቀጠልና ዳር ማድረስ ሌላው የአዋጁ ዓላማ ነው።

 

አገሪቱ በአሁኑ ወቅት የደረስችበትን እድገት ደረጃ ማስቀጠል የሚቻለው ሰላምና መረጋጋት ከሰፈነ ብቻ ነው። የልማት አውታሮች እየተቃጠሉና እየተዘረፉ ዜጎች ለስራ ወጥተው ባላሰቡት ሰዓትና ስፍራ እንደወጡ እየቀሩ ለዓመታት ሰርተው ያካበቱት ሃብትና ንብረት በደቂቃዎች እየወደመባቸው ልማትን ማስቀጠል አይቻልም።

 

በመሆኑም ሕግን የማስከበር ጉዳይ መደራደሪያ ሊሆን አይችልም። በሰላም ድርድር በየትኛውም አገር አልታየም። በተለይም ሌላ ዓላማ ባላቸው ጥቂት ቡድኖች የሚታመስ አገር ሊኖር አይገባም። በመሆኑም መንግሰት ሰላም ማስከበርና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነትና  ግድታ አለበት። አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ ሰላምነ ለማስከበር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ የግድ ይለዋል። ከዚህ አንፃር አዋጁ ተገቢና ለህዝብ አስፈላጊ ጉዳይ ነው።

 

ከተወሰኑ ጸረ ሰላም ሃይሎች በስተቀር መላው የአገሪቱ ህዝብም ይህንን በመረዳት ከኮማንድ ፖስት ጋር እየተባበረ ይገኛል። እነዚህ ጸረ ሰላም  ሃይሎች አገሪቱን ለመበታተን አልመው የህዝቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄ ወደ ራሳቸው አጀንዳ በመቀየር በዚች አገር ሰላም እንዳይኖር በመነገድ ላይ ይገኛሉ።

 

መረጃዎች እንደሚያሳዩት በተለይም የግብጽ መንግስት የአገራችንን ልማት ለማደናቀፍ ቀላል የማይባል ገንዘብ ድጋፍ  እመደበ ነው። የግብፅ ፈላጎት ምን እንደሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ካሁን ቀደም አልኢሳም በተባለ ቴልቪዥን ጣቢያ የተላለፈ አንድ ዘገባ እንዳድስተጋባው የኮንጎና የአባይ ወንዞች ሃላፊ የሆኑት ግብፃዊትዋ ዶ/ር ናንሲ  አገራቸው በኢትዮጵያ የሚካህድ ማንኛውም አይነት መንግስትን የሚቃውም አመጽ ትደገፋለች። በተለይም ደግሞ ወደ ታላቁ የህዳስ ግድብ የሚወሰዱ መንገዶች ባሉባቸው አካባቢዎችና ክልሎች የሚነሱ ሁከቶችናና ብጥብጦችን ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆነች አስታውቀዋል።

 

ግብጽ  የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማደናቀፍ ያለመ ማንኛውም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ እንደሆነችም በተለያየ መልክ በተለያዩ የአገሪቱ ሃላፊዎች መነገሩ ይታወቃል። በመሆኑም ቀላል የማይባል ገንዘብ ለዚህ ተግባር እየዋለ እንደሆን ይነገራል። ድጋፉ ተጠናከሮ እንደሚቀጥልም ሃላፊዋ አስታውቀዋል።

 

በአሁኑ ወቅት በአገራችን እየተከሰተ ያለው ሁከትና ብጥብጥ እየመሩ  ያሉ በውጭ አገራት የሚኖሩ አንዳንድ ከሃዲዎችም የዚህ ገንዘብ ተቋዳሽ  ናቸው። እነ ጀዋርና ግንቦት ሰባት በዚህ መልክ በአገራቸውና በህዝባቸው እየነገዱ ይገኛሉ። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁኔታውን በአግባቡ ካለመገንዘብ ካልሆነ በስተቀር በአገሩ ልማት በአገሩ ሉአላዊነት አይደራደረም።  በአገሩ ሰላምም እንደዚሁ። ለዚህ ማሳያው ደግሞ በአሁኑ ወቅት ታላቁ የህዳስ ግድብን ዳር ለማድረስ ሕዝብ እያደረገ ያለውን የማያቋርጥ ድጋፍ ማስተዋል በቻ በቂ ነው።

 

አንድ ወቅት ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮነን ባስተላለፉት መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ።  “የታላቁ የህዳሴ ግድብ የትውልዱን የህዳሴ ቁርጠኝኘት ያስተጋባ፣ በይቻላል መንፈስ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ያግባባ ለወዳጀና ለጎረቤት አገራት አርቆ አሳቢነትን ያሳዬ፤ ለጋራ ተጠቃሚነት ያለንን አዎንታዊ አመለካከት ያስመሰከረ ነው። በዚሁ ግድብ ላይ የተፈጠረው የልማት መነሳሳትና ተሳትፎ በሌሎች ዘርፎች ላይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ታላቁ መሪ ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ምስጋና ይግባቸውና ከታላቁ የአባይ ወንዝ ጋር የዘላቂ ልማት መንፈስ እንዲፈጠርና የይቻላል መንፈስ እውን እንደዲሆን በወሰዱት እርምጃና ያመራር ሚና ታሪክ በልዩ ስፍራ ዘላለም ሲያስታውሳቸው ይኖራል፡፡”

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy