Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ያስተዋዩ ህዝባችን ትጋት!

0 361

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ያስተዋዩ ህዝባችን ትጋት!

ነጻነት አምሃ

 

በአሁኑ ወቅት ለአገራችን  የሚያስፈልገው ዋና ጉዳይ የውስጥ ሰላማችንን በአስተማማኝ ማረጋገጥ ነው  ለሰላም መታወክ በብዙ መልክ ተጋላጭ በመሆናችን ከውጭ የሚሰነዘረብንን ሰላማችንንና ልማታችንን የሚያደናቅፉ ችግሮች ለመመከት የሚቻለው ውስጥ ያለንን ሰላም ማጠናከር ስንችል  ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የውስጥ ሰላማችንን መሰረት ለመናድ የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ ጠላቶች ተነስተውብናል፡፡

 

በመሆኑም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚደረገው ጥረት የተለያዩ መሰናክሎች እያጋጠሙት ይገኛል። የውስጥና የውጭ ተጽእኖዎች እንዳሉ ሆነው በቀጠናው ያለው ሽብርተኝነትም ሌላው ችግር ነው። ኦነግና ግንቦት ሰባት የተባሉ አሸባሪዎች ከአልሸባብና ከሌሎች ሽብርን ከሚደግፉ መንግስታት ጋር በመተባበር በሽብር ተግባራቸው የበርካታ ንጹሃን ዜጎች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ይገኛሉ።  

 

ይህንን መመከት የሚቻለው  የውስጥ ሰላማችንን በተገቢው መልክ ማረጋገጥ ከቻልን ነው፡፡  ካልሆነ ለሰላም እጦት ተጋላጭነታችንን ያሳድገዋል፡፡ ከሌሎች አገራት ተሞክሮ እንደሚታየው በርካታ አገራት የውስጥ ሰላማቸውን ማረጋገጥ ባለመቻላቸው ለእርስ በርስ ግጭትና እልቂት ተዳርገዋል፡፡ የአገራችንና ሕዝባችን ጠላቶችም ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ እንዲያጋጥመን የማይበጥሱት ቅጠል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡

 

ሌላውን ሁሉ ወደጎን ትተን በቅርቡ አገራችንን ሰላም ለማረጋገጥና ህግና ስርዓትን ለማስከበርና  የዜጎችን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ ተዘዋውሮ መስራትና መኖር መብት ለማስጠበቅ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለህዝብ አይጠቅምም በማለት ህዝብን ለማደናገር ላይ ታች ሲሉ ማየታችን እውነትም እነዚህ ቡድኖች ሃገራችንን ህልውና ማየት የማይፈልጉ መሆናቸውን መረዳት ይቻላል፡፡ አስተዋዩ ህዝባችን ግን አሁንም ጆሮውን ለጸረ ሰላም ሃይሎች አይሰጥም። ሰላሙን ከመንግስት ጎን ሆኖ እየጠበቀ ይገኛል፡፡ ይህ ሰናይ ተግባር አሁንም ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ አንድነታችንን አጠናክረን ሰላማችንን በማረጋገጥ የተጀመረውን ልማት ዳር ማድረስ ይጠበቅብናል፡፡

 

የተጀመረው ልማት እውን የሚሆነው በአገሪቱ ሰላም ሲረጋገጥና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደቱ ሲፋጠን ነው፡፡ ሰላምን ማረጋገጥ ካልተቻለ ለዘመናት የህዝባችንን አንገት አስደፍቶ የኖረው የገነገነ  ድህነት አሸንፈን ለድል መብቃት አይታሰብም፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት አገራችን ካለችበት ፈታኝ ሁኔታ ለማውጣት ያላሳለሰ ጥረት ይጠይቃል፡፡

ይህ መላውን የአገራችንን ህዝብ እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ እንዲገባ ያስገድደዋል፡፡ ትልቁ ፈተና ያለው ማንነት ላይ ያነጣጠረ በታኝ የሆነ በአገራችን ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ ነው፡፡ ይህንን አደጋ ለመመከትና አገሪቱ የሰነቀችውን ተስፋ እውን ለማድረግ  ሰላማችንን ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር ይሆናል።

የአገራችን አጠቃላይ ሁኔታ በምናይበት ጊዜ በዋናነት የውስጥ ሰላማችንን በአስተማማኝ ማረጋገጥ ነው ለሰላም መታወክ በብዙ መልክ ተጋላጭ በመሆናችን ከውጭ የሚሰነዘረብንን ሰላማችንንና ልማታችንን የሚያደናቅፉ ችግሮች ለመመከት የሚቻለው ውስጥ ያለንን ሰላም ማጠናከር ሲቻል ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ውስጥ ሰላማችንን መሰረት ለመናድ የሚፈልጉ የውጭና የውስጥ ጠላቶች ተነስተውብናል፡፡ መነሳት ብቻም ሳይሆን ጉዟችንን እያደናቀፉ እንደሆነ የሚካድ አይደለም፡፡

በአገር ውስጥ በተለያየ ወቅት እየተቀሰቀሰ ፈተና የሆነው ሰላምን የማወቅ እንቅስቃሴ  ከአካባቢያችን ሀገራት ከሚመነጨው የሽብርተኝነት አደጋ ጋር ተዳምሮ በልማታችንና በልማትና ዕድገት እድላችን ላይ የሚኖረው አሉታዊ ጫና በቀላል የሚገመት አይደለም።

እንደዚህ አይነቱ ሰላምን የማወክና ልማትን የማደናቀፍ አደጋ በአገራችን ብቻ የተከሰተ ሳይሆን በአጠቃላይ በክፍለ-አህጉሩ አካባቢ ለሚገኙ በተለይ ደግሞ በምስራቅ አፍሪካ በሚገኙ  ሌሎች ሀገራት ጭምር አስጊና አስከፊ እንደሆነ ካለፈው ተሞክሮ አይተናል፡፡

አካባቢያችንን በትኩረት በማየት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ የሚችሉ ሁከቶችንና ብጥብጦችን መላ ህዝባችን እጅ ለእጅ  ተያይዘን መረባረቡ ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ጎረቤት ሀገር ከሆነችው ከኤርትራ አሸባሪዎችን በመመልመል፣ በማደራጀትና በማስታጠቅ ለቀጠናው በተለይ ለሀገራችን ስጋት ሆና መቆየቷ የሚታወቅ ነው፡፡ ቀደም ሲል መንግስት አልባ በነበረችው ሶማሊያ የመሸጉ የተለያዩ የጦር አበጋዞችና አሸባሪ አክራሪ ቡድኖች በዋናነት ይደገፉ የነበረው በአስመራው መንግስት እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያየ ጊዜ ያወጣው ዘገባ አብነት ነው። በውስጥ ያለው ሰላማችን ጠንካራ ስለነበር ግን በተለያየ መልክ ይቃጣብን የነበረው የጥፋት ዘመቻ መቋቋም ችለናል፡፡

ይህ ሁኔታ አሁን…አሁን በውስጥ ያለን ሰላም ችግር ላይ እየወደቀ ሲመጣ ከውጪው ችግር ጋር ተደማምሮ አገራችን የሰነቀችው ተስፋ ያሰናክለው ይሆን ብሎ የሚጠይቅ ዜጋ ቁጥር በርካታ ነው፡፡ እነዚህ ጸረ ሰላም ሃይሎች የገዛ ሀገራቸውን ህዝብ ሠላምና መረጋጋት ከመንሳት አልፈው የቀጣናውን ሀገራት በሽብር የማመስ ዓላማን አንግበው ሲሰሩ ቆይተዋል። ለዚህም በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችንና በጎረቤት ሀገሮች ያደረሷቸው የሽብር ጥቃቶች ከበቂ በላይ ማሳያዎች ናቸው።   

የአገራችን  አጠቃላይ ሁኔታ በምናይበት ጊዜ  በዋናነት የውስጥ ሰላማችንን በአስተማማኝ ማረጋገጥ ካልቻልን የተጀመረው የልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ጥያቄ ላይ ሊወድቅ ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም  ባለፉት በርካታ አመታት ከነበረው የአገራችን ሁኔታ መረዳት እንደሚቻለው ለሰላም መታወክ በብዙ መልክ ተጋላጭ በመሆናችን ከውጭ የሚሰነዘረብንን ሰላማችንንና ልማታችንን የሚያደናቅፉ ችግሮች ለመመከት የሚቻለው ህዝባችን በአንድነት ማሰለፍና ማንቀሳቀስ ስንችል ነው፡፡   

የሰላም ጉዳይ ደግሞ በቀላሉ የሚከወን ባለመሆኑ ሁሉም ዜጋ እጅና ጓንት ሆኖ ሊሰራ ይገባል፡፡ በተለይ ያለንበት ቀጠና ሽብርተኝነት የተንሰራፋበት በመሆኑና ይህ ጸረ ሰላም ቡድን ደግሞ የበርካታ ንጹሃን ዜጎች ህይወት እየቀጠፈ ስለሚገኝ በሌሎች ጎረቤት አገራት የምናየው እልቂትና ችግር ወደእኛ መዛመቱ ስለማይቀር የውስጥ ሰላማችንን ከአስተዋዩ ህዝባችን ጋር በመሆን የማስጠበቅ ተግባር ማከናወን ይኖርብናል፡፡  

ለሰላም እጦት ተጋላጭነታችንን በተገቢው መንገድ መቀነስ በምንችልበት መልክ መንቀሳቀስ የግድ ይለናል፡፡ ከሌሎች አገራት ተሞክሮ እንደሚታየው በርካታ አገራት የውስጥ ሰላማቸውን ማረጋገጥ ባለመቻላቸው ለመበታተንና ለእርስ በርስ ግጭትና እልቂት ተዳርገዋል፡፡ በቀላሉ የሊቢያ፣ የሶማሊያ የየመን ሁኔታን መመልከት ለዚህ አስረጂ ነው፡፡ የአገራችንና ሕዝባችን ጠላቶችም እኛም ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ እንዲያጋጥመን የማይበጥሱት ቅጠል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ በተለይ ደግሞ በአገሪቱ ሰላምን ለማረጋገጥ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማደናቀፍና በዴሞክራሲያዊ መብት ሰበብ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚታገሉ ወገኖችን ለይተን በማወቅ እነዚህን የማጋለጥ ስራ መከወንና ከመንግስት በየወቅቱ የሚወጡ ጉዳዮችን መከታተል የግድ ይላል፡፡  

የአዋጁ ዋና ዓላማ የውስጥ ሰላማችንን ለማረጋገጥ ነው፡፡  ዜጎች ያለምንም ችግር ከቦታ ወደ ቦታ ተዘዋውረው መስራትና መኖር የሚችሉበትን አመቺ ሁኔታ የሚያደናቅፉ ጸረ ሰላም ሃይሎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ ነው፡፡ ይህንን በሚገርም መልክ ለህዝብ እንደማይጠቅም በማስመሰል ሲሰብኩና ህዝብን ለማደናገር ሲጥሩ ይታያል፡፡ ሆኖም ግን አስተዋዩ ህዝባችን በሰላሙ አይደራደርም፡፡ በልማቱም የሚደራደርበት ሁኔታ አይኖርም። አስተዋዩ ህዝባችን ግን አሁንም ጆሮውን ለፀረ ሰላም ሃይሎች አይሰጥም። ሰላሙን ከመንግስት ጎን ሆኖ እየጠበቀ ይገኛል፡፡ ይህ ሰናይ ተግባር አሁንም ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ አንድነታችንን አጠናከረን ሰላማችንን በማረጋጋጥ የተጀመረውን ልማት ዳር ማድረስ ይጠበቅብናል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy