Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶክተር አቢይን የማደናቀፍ ሴራን እናክሽፍ

0 461

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዶክተር አቢይን የማደናቀፍ ሴራን እናክሽፍ

በ ሂካ መርጋ

ሃገራችን ኢትዮጽያ በአዲሱ ጠ/ሚ ዶ.ር አቢይ መመራት ከጀመረች ሳምንታትን አስቆጥራለች፡፡ የዶክተሩ
የስራ ጅማሮም ለህብረተ-ሰቡ ትልቅ ደስታን የፈጠረና እንደ ሃገር ትልቅ መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡
ነገር ግን ይህ የዶክተር አጀማመርና የህዝቡን ስሜት መግዛት መቻሉ ያልተመቻቸዉ አካልም አይጠፋም፡፡
እነኚህ አካላት ብዙ ጊዜ ዉጫዊ አካል ብሌን የምንፈርጃቸዉ አካላት ላይሆነ ይችላሉ፤ እዛዉ የመንግሰት
መዋቀር ዉስጥ ሆኖ ስልጣንን ሽፋን በማድረግ የሃገሪቷን ሃብት ያለ አግባብ ስመዘብሩ የነበሩ፤ ስልጣንን ያለ
አግባብ ተጠቅሞ ሰዉን ያሰሩ፤የገደሉ፤አካል ያጎደሉ፤ ዜጎችን ከንብረትና ከቤታቸዉ ያፈነቀሉ፤ ኮንትሮባንድን
የገቢ ምንጩ አድርጎ የሚኖር፤ሙስናን በመደበኛነት የሚሰሩ ወዘተ ይገኙበታል፡፡
ለነዘህ አካላት አሁን እየመጣ ያለዉ የዶክተር አቢይ አመራር ፈጽሞ ለህገ-ወጥ ድርጊት እንደማይመቻቸዉ
ከማንም በላይ ያዉቃሉ፡፡ ስለዚህ በተወሰነ ደረጃ ራሳቸዉን ለማዳን የማያደርጉት ጥረት እንደማይኖር
መገመት አይከብድም፡፡
ምክንያቱም እኛም እንደ አንድ ዜጋ ያገኘነዉ ልምድ ስላለ ነዉ፡፡ በ ቀድሞ ጠ/ሚኒስቴራችን ክቡር አቶ
ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጊዜ መንግስት ሙስናን ና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፋታት ስራ በጀመረበት
ማግስት እነኚህ ጥፋተኞች መያዛቸዉ ስለማይቀር የግዴታ አጀንዳዉን ወደ ሌላ መቀየር ስለ ነበረባቸዉ
የሃገሪቷን ሰላም እስከ ማስበጥበጥ እንደደረሱ ለሁላችን ግልጽ ነዉ፡፡
በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ብር ይመድቡና ወጣቶቻችንን በመጠቀም በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች ብጥብጡ
ከክልል የተነሳ አስመስሎ እንዲሁም በመንግስትና ህብረተ-ሰቡ መካከል የእርጋታ ጊዜ እንደይኖር እድሜያቸዉን
እያራዘሙ ዛሬ ደርሷል፡፡
ይህ ሲሆን ደግሞ መንግስተም ሆነ ህዝብ ተረጋግተዉ እንደ ሃገር መስራት የሚጠበቅበትን መስራት ሲገባዉ
በሃገሪቱ ሰላምና የህግ-የበላይንትን ማስጠበቅ ስራ ይጠመዳል፡፡ ይሄኔ ነዉ እነሱ እፎይታ የሚያገኙት፡፡
ቅድም እንደ ነገርኳችሁ በራሱ የመንግስት መዋቅር ዉስጥ ብዙ በቀላል የማይፈቱ ዉስስብ ጉዳዮች አሉ፡፡
ረዥም እድሜ ያለዉና በጣም የረቀቀ የዉንብድና ስራ የሚሰራዉም በዉጪ አካላት ሳይሆን እዛዉ በመንግስት
መዋቅር ዉስጥ ሆኖ ከላይ ከላይ ሲታዩ ለሃገሪቱ ዕድገት፤ደህንነት፤አንድነት ወዘተ የሚቆረቆሩ ይመስላሉ፡፡ ነገር
ግን ዉሰጡ በጥልቀት ሲታይ በጥቅማቸዉ የሚመጣ ነገር ካለ ሃገሪቷ ከምን ብትንትኗ አይወጣ ለነሱ
ደንታቸዉም አይደለም፡፡ ሲበዛ ራስወዳዶች ናቸዉ፡፡
ወደ ዋና ጉዳዬ ስመለስ እነኚህ ግለሰቦች የዶክተር አቢይ አመራር ለስርቆት፤ ለመግደል፤ለኮንትሮባንድ፤
ለሙስና፤ለብጥብጥ ና ወዘተ እንደማይመች ከዶክተሩ አጀማመር አይቶታል፡፡
ለምን አይመችም ካላችሁኝ ደግሞ ሰዉየዉ አመጣጡ የሚነግረን ይኖራል፡፡ እሱም ዶክተሩ በሰራባቸዉ መስራ
ቤት ሁሉ በተጨባጭ የሚታይ ዉጤት ካልሆነ የተመደበዉን በጀት በልተዉ በዉሸት ሪፖርት ስራዉ እንደተሰራ
ተደርጎ ማቅረብ ስለማይቻል፤ ግለ ሰቡ በህገ-መንግስት የበላይነት ስለሚያምኑ የህገ-ወጥ ድርጊት በሳቸዉ
ዘንድ በፍጹም ተቀባይነት ስለማይኖረዉ፤መስራት የማይችለዉን ካቢኔ በትነዉ እንዳዲስ ለሃገሩ ታማኝ
የሆኑትን ብቻ ሊያመጡ ስለተዘጋጁ፤ ከፖሊቲካ የፀዳ የህዝብ መከላከያ ና ደህንነት መዋቅርን ሊያዋቅሩ ስለሆነ
ለ ሌቦችና ለሆድ አደሮች መንገዱ እንደ ካሁን በፊት ክፍት አይሆንም፡፡
እነኚህ ግለ-ሰቦችም( በልተዉ የለመዱ) ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብሎ ያያሉ ማለት ሞኝነት ነዉ፡፡ ከሌላ የባሰ
እነኚህን ማጠራት ራሱ በጣም ጊዜ የሚወስድ መሆኑን ልናዉቅ ይገባል፡፡ ለዚህም ነዉ የቤት ስራ ከማብዛት
ጊዜ ልንሰጠዉ ይገባል የተባለም፡፡
ካሁን በኃላ እንደ ቀድሞ ጊዜ ሁሉ በኦሮሚያ ና በተለያዩ ክልሎች ብጥብጥ የመነሳቱ እድልበጣም አነስተናኛ
ስለ ሆነ ሃገሪቱን ከማበጣበጥ አሁንም ሌላ ስልት ይዞ መምጠቸዉ አይቀሬ ነዉ፡፡
ለምሳሌ በዚህ ቅርብ ቀን በፊት ሞያሌ ላይ የተፈጸመዉ የጥፋት ድርጊት የሚያሳየዉ ተከስተዉ የነበረዉን
የኦሮሞና ሱማሌ ክልል የድንበር ግጭትን ምክንያት ያደረገ ሳይሆን የመንግስት አካል ሆኖም የጥፋት ኃይል
እንዳለ ማሳያ የሆነና የዉንብድና ሰንሰለቱ በጣም የተያያዘ መሆኑን ነዉ፡፡
ስለዚህ ሰላም ወዳዱ የኢትዮጽያ ህዝብ ማወቅ ያለበት ቢኖር አልፎ አልፎ እንደዚህ አይነት ሴራ ሊሰራ

ስለሚችል ጉዳዩ አዲስ ሊሆንብን አይገባም፡፡
ያም ሆነ ይህ ካሁን በኃላ በየቦታዉ የሚነሱ ሁከትና ብጥብጥ የሃገሪቷ የልማት ጥያቄ ሳይሆን ሆን ተብሎ
የዶክተር አቢይን ስራ ለማደናቀፍ የተዘጋጀ ሴራ መሆኑን ቀድመን ልናዉቅ ይገባል፡፡ እነኚህ የሚሰሩ ሴራዎች
ደግሞ ለጥፋተኞች እድሜ ማረዘሚያ ሆኖ አሁንም የምንፈልገዉን የመልካም አስተዳደር ማሻያሻያ
ያሳጣናል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ስለ ሃገሬ ያገባኛል ስሜት ሊኖረን ይገባል፡፡
በመጨረሻም እኛ እንደ አንድ ዜጋ የሚጠበቅብን የሃገራችን እድገት፤ አንድነት፤ እንዲሁም ደህንነት የሚሰማን
ከሆነ ሃገራችንን ከነኚህ ጥፋት ኃይሎች መጠበቅ፤ ካዲሱ አመራር ጋር በመተባበር የምንመኘዉን ለዉጥ
ማምጣት ይጠበቅበናል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy