ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለህዝቡ አማራጭ ሆኖ ለመገኘት ለሚያደርጉት ጥረት ምስጋና አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በብሄራዊ ቤተመንግስት ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር ለእራት ተቀምጠዋል።
በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሀገሪቱ ለምርጫ እና ፉክክር ያለበት ፖለቲካ እንዲፈጠር ምህዳሩን የማስፋት ስራ እንደሚከናወን ተናግረዋል።
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሟላ ፖሊሲን ይዘው በመቅረብ ብቁ ተፎካካሪ መሆን እንደሚገባቸውም ነው ያሳሰቡት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የዜሮ ድምር ውጤት ፖለቲካንም በመንቀፍ ይህ ሀገሪቱን ዋጋ እንደሚያስከፍል ነው ያነሱት።
በብሄራዊ ቤተመንግስት በተካሄደው የእራት ግብዣ ላይ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች በተጨማሪ ጥሪ የተደረገላቸው የሀይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።
Photo credit: Addis fortune