Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

 ለበሰለ እና በስራ ለተፈተነ የአመራር መዋቅር

0 412

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 ለበሰለ እና በስራ ለተፈተነ የአመራር መዋቅር

                                                                       ዮናስ

በሀገሪቱ የሚከሰቱ ቀውሶች ሁለት ዋነኛ መንስኤዎች እየተመጋገቡ የሚፈጥሩት ቀውስ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። የህዝቡ ቅሬታዎች ወደተቃውሞ ሲያድጉ ነው የሚለው አንደኛው ምክንያት ሲሆን፤ የኢህአዴግና አጋሮች ችግሮች ወደህዝቡ እየተዛመቱ የሚፈጥሩት ቀውስ ደግሞ ሁለተኛው ነው።

የመጀመሪያውን ችግር ለመፍታት ተከታታይና ሰፋፊ ስራዎችን ይጠይቃል። ግዜም ይወስዳል። እንዲያውም ከኢህአዴግም በሰፋ የተለያዩ ባለድርሻዎችን ተሳትፎ ይሻል። ሁለተኛው ኢህአዴግና አጋሮች የየራሳቸውን ውስጣዊ መዋቅር ሆነ የእርስበርስ ግንኙነታቸውን ሀላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ባለመምራታቸው፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለሁከትና ለግጭቶች ምክንያት መሆናቸው ነው። ይህ ሁለተኛው ችግር በአንጻራዊ መልኩ በፍጥነትና በኢህአዴግ ውስጣዊ አቅም ሊፈታ የሚችል ነው። ኢህአዴግ በየድርጅቶቹ ውስጥ፣ በግንባሩ ደረጃ እና ከአጋሮቹ ጋር ያለውን ግንኙነት መልክ የሚያስይዝበት ውይይትም ያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

ይህ ውይይት በተጨማሪም ከአብዝሀው አመራርና ከአጋሮች ጋር መልካም ግንኙነት ያለው፣ የበሰለ እና በስራ የተፈተነ አመራርን በየደረጃው ማዋቀርንም ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ተመልክቷል። በማንኛውም መለኪያ ግን የህዝቡን ብሶቶችና የሀገሪቱን ችግሮች ሁሉ ኢህአዴግና አጋሮች ብቻቸውን ሊፈቱት አይችሉም። ሁሉንም ባለድርሻ የሚያሳትፉ ሰፊና ተከታታይ ስራዎች ያስፈልጋሉ።

አሁን ኢህአዴግ ሊያደርግ የሚችለውና የሚገባው ነገር፤ የድርጅቱ ተቋማዊ ይዞታ የሚሻሻልበት፣ የሀገራዊ መፍትሄ አካል የሚሆንበት፣ ብሎም ሁሉን አሳታፊ መሪ ሚና ለመጫወት የሚያስችለው ድርጅታዊ ሰላምና መናበብ መፍጠር መቻል ነው። የኢህአዴግ ምክር ቤትም በዚህ መንፈስ ውሳኔዎችን ያሳለፈ ይመስላል። ከዚህ ባሻገር አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን እንዲጎለብት ኢህአዴግ እንዲሰራ ግድ የሚሆንበት ዋነኛ ምክነያት ለዓመታት የስርዓታችን አደጋ ናቸው በሚል ሲታገልባቸው የቆዩ ሆኖም ከውስጡ መንቀል ያልቻላቸው አስተሳሰቦች አሸናፊ እየሆኑ በመምጣታቸው ነው፡፡ ትምክህትና ጠባብነት የደረሱበት ጫፍ ለአገራዊ አንድነታችን አደጋና ስጋት የሆኑባቸውን አጋጣሚዎች ያለፉት 3 ዓመታት በሚገባ አሳይተውናል። በእርግጥም እነዚህን አስተሳሰቦች ማምከን የሚቻለው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን ሲጠናከር ብቻ ነው። ስለሆነም አሁን ላይ አንድነታችን እንዲጠበቅ መስራት ተገቢነቱና አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይሆንም ማለት ነው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦች ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን አደጋ ውስጥ እየከተቱ በመሆኑ ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን እኛም እንደዜጋ በጋራ አንድነት ልንመክታቸው የሚገባ መሆኑን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ አስረግጦ ያሳያል፡፡ ለዚህ ደግሞ መላውን ህዝብ የሚያስተባብሩና አቅም የሚገነቡ በሳል አመራሮች ያሹናል።

ሌላው አገራዊ አንድነታችንን ማጠናከር ላይ ማተኮር ያለብን መሰረታዊ መነሻ ኪራይ ሰብሳቢነት የወለዳቸው የጎጠኝነት ስሜቶች በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በማይሆን ስሌት ውስጥ በመግባት አደጋ እያስከተሉ መሆኑ ነው፡፡ ለአብነትም በአንዳንድ አካባቢዎች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና መፈናቀሎች፣ በየዩንቨርሲቲዎች አልፎ አልፎ የሚከሰተው ብሄርን ማዕከል ያደረገ ጥቃት፣ ከክልሌ ውጡ፣ ወደ ክልሌ ልመለስ በሚል የሚነሱ አስተሳሰቦች፣ ብሄርን መሰረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮች . . . ወዘተ እየተበራከቱ መምጣታቸው በእርግጥም ለዓመታት በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተችውን ዴሞክራሲያዊት አገር አደጋ ላይ የሚጥልና ኢትዮጵያዊነት ጥንካሬያችንን አደጋ ውስጥ የሚከት በመሆኑ ከምንም በላይ በሳል አመራሮች ያስፈልጉናል። ግን ደግሞ ለእነርሱ ብቻ የምንተወው ሳይሆን እኛም ዜጎች ልናተኩርበት የሚገባው መሆኑን ያመላክታል፡፡

እነዚህ መጥፎ አዝማሚያዎች የዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ብቻም ሳይሆን አጠቃላይ የሀገራችን ህዝቦች የቆዩ ወርቃማ እሴቶችንም ጭምር የሚቃረኑ ናቸው፡፡ የህዝቦች አብሮ የመኖርና የመደጋገፍ መስታግበሮችን በመናድ ሀገራችን ልትደርስበት ያቀደውችውን የብልጽግና ራዕይ የሚያደናቅፉ ናቸው፡፡ በግጭትና የሰላማዊ ኑሮ መስተጋብር መዛባት የሚያተርፍ የለም፡፡ ይልቁንስ ሁሉም ኪሳራን ይከናነባል፡፡

የፌዴራል ስርዓታችን የአገር አንድነትን የሚያጠናክር እንጅ ለአንድነታችን አደጋ የሚሆን አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ምናልባት ይህንን ለማስጨበጥና የተሄደበት ርቀትና ሌሎች ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮ ካልሆነ በስተቀር ችግሩ ስርዓቱ በህዝቦች ያልተገደበ ትግል እውን የሆነና አዲሲቷ ኢትዮጵያ በግድ የሚኖሩባት ሳይሆን ፈቅደው የሚገነቧት አገር መሆኗን እውን ያደረገ ነው፡፡ በመሆኑም የፌዴራል ስርዓታችን በርካታ አገራት ተግብረውት አንድነታቸውን ጠብቀው እንዲሄዱ ያስቻለና በበርካታ አገራትም ተግባራዊ ሆኖ ውጤት ያስመዘገበ፣ ዛሬም ላይ በርካታ የሰለጠኑ አገራት የሚተገብሩት ነው፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያንም አንዳችን ያለአንዳችን በአንድ እጃችን እንደማጨብጨብ ነው፡፡ ውበትም ጥንካሬም አይኖረንም፡፡ ሃብት በራሱ ለስኬት አያበቃም፡፡ የስነልቦናዊ አንድነት መኖር ግድ ይላል፡፡ አንድ ስንሆን እንበረታለን፤ አቅምም ይኖረናል፤ መነጣጠል ሃይልን ያዳክማል እንጂ ማንንም አገር ጠንካራ አድርጎ አያውቅም፤ ለዚህ ደግሞ የቀድሞዋን ሶቬት ህብረት  ምሳሌ ማድረግ ይቻላል፡፡ ግዙፍ ኢኮኖሚ ለመገንባት ግዙፍ ማህበረሰብ፣ እምቅ ሃብትና የሰው ሃይል ግድ ነው፡፡ እኛም በአፍሪካም ሆነ በዓለም ተደማጭነታችን የሚጎላው የማትበገር አገር በመገንባት በመሆኑ ለዛ መትጋት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ስለዚህ እንደ አገር የማትበገር አገር መገንባት የሚቻለው አንድነታችንን ለማጠናከር የሚተጉ አመራሮች በየደረጃው ያሹናልና ነው ምክር ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ የተወያየበት፡፡

ታላቁ መሪ ጓድ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት እንደገለጸው ኢትዮጵያዊነት በአባይ ወንዝ ይመሰላል፤ አባይን ትልቅ ወንዝ የሚያደርጉት የተለያዩ ገባር ወንዞች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያም ትልቅ ሀገር የሚያደርጓት ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ናቸው፡፡ ህልውናቸው፣ ዕድገታቸውና ቀጣይ ዕጣ ፈንታቸው ከአብሮነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ሆነው ጠንካራ ሀገር ሲገነቡ ይደመጣሉ፡፡ አንዱ ለአንዱ አስፈላጊ ነው፡፡ አይደለም የአንድ ሀገር ህዝቦች መላው የዓለም ህዝብ በግሎባላይዜሽን በተሳሰረበት በአሁኑ ወቅት እኛ ኢትዮጵያውያንም ዴሞክራሲያዊ አንድነት ከመገንባት ውጭ አማራጭ የለንም፡፡

በኢህአዴግና በብሔራዊ ድርጅቶች የተካሄደው ግምገማም ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑ ከሰጣቸው መግለጫዎች መገንዘብ ይቻላል።

“ጊዜ የለንም” በሚል መንፈስ ለህዝቡ ጥያቄ የተሟላ ምላሽ ለመስጠት የአመራር አባላት በሚያደርጉት ትግል የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጫቸው አረጋግጠውልናል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ፣ የብሔራዊ ድርጅቶችና የኢህአዴግ ምክር ቤት ያካሄዱት ግምገማ ተመጋጋቢና በግንባሩ አመራር አባላት መካከል የሃሳብ አንድነት በማምጣት የተጠቃለለ መሆኑን ተናግረዋል። ምክር ቤቱ በስራ አስፈጻሚውና በብሔራዊ ድርጅቶች የታየውን ግምገማ በስፋት መመልከቱን፤ መድረኩ በድርጅቶች መካከል የተፈጠረውን መጠራጠር ያስወገደና አቅም ፈጥሮ በመውጣት ለቀጣይ ጉዞ መፍትሄ ያስቀመጠ መሆኑንም በመግለጫቸው ላይ አጽንኦት የተሰጠው ጉዳይ ነው።

ተወደደም ተጠላ ግን የተደረገው የግምገማ ውጤት የሚለካው የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ስኬት ሲመዘገብ ነው። ይህ እንዲሆን ደግሞ ቀዳሚው አጀንዳና መስፈርት በየደረጃው ያለውን መንግስታዊም ሆነ ድርጅታዊ መዋቅር በበሰለና በስራ ልምድ በተካነ አመራር ማጠናከር  ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy