CURRENT

ለ286 የአውሮፕላን አብራሪዎች ፍቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ

By Admin

April 12, 2018

በተያዘው በጀት ዓመት ለ286 አዳዲስ የአውሮፕላን አብራሪዎች ፍቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለሰልጣኑ ፍቃዱን የሰጠው በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት ነው።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የማስታወቂያና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ አንሙት ለማ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ፍቃዱ የተሰጠው በተለያዩ ዘርፎች ነው።

በዚህም መሰረት ፍቃድ የተሰጣቸው፥ 87 የትራንስፖርት አውሮፕላን አብራሪዎች፣ 48 የንግድ አውሮፕላን አብራሪዎች፣ 8 የግል አውሮፕላን አብራሪዎች፣ 111 የተማሪ አውሮፕላን አብራሪዎች ናቸው።

እንዲሁም በሁለት ዘርፍ የትራንስፖርትም የንግድም አውሮፕላን ለሚያበሩ 32 አብራሪዎችም ፍቃድ መሰጠቱን አቶ አንሙት አስታውቀዋል።

ተጨማሪ 397 የ‘‘A’’ ደረጃ ግራውንድ ቴክኒሻን ፍቃድም ተሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ