Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የህዝቡን እኩል ተጠቃሚነትና ህጋዊ ተጠያቂነትን ማስፈን ሃገሪቱን ላጋጠማት ችግር መፍትሄ ይሆናል- ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ

0 486

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የህዝቡን እኩል ተጠቃሚነትና ህጋዊ ተጠያቂነትን ማስፈን ሃገሪቱን ላጋጠማት ችግር መፍትሄ ይሆናል- ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ

የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች፤ የፍትህ አካላት እየሰጡ ያሉት የአገልጋይነት ስሜት ቀዝቃዛ መሆን፤ ለወጣቱ የስራ እድል መፍጠር አለመቻል ተደራርበው ህብረተሰቡ የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቀውን እያቀረበ በመሆኑ ምላሽ ማግኘት አንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የገለጹት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ለተገኙት ከክልልና ከአዲስ አበባ ከተውጣጡ 25 ሺህ ያል የህብረተሰቡ ክፍሎች ባደረጉት ንግግር ላይ ከላይ የተጠቀሱት የሃገሪቱ ፈተናዎች መፍትሄ ባለማግኘታቸው በርካታ ልዩነቶችን ፈጥረዋል ነው ያሉት፡፡

ይህንንም እድል በመጠቀም የኢትዮጵያን ህዝብ አንድነትና ህብረትን ለማፍረስ ከውጪም ሆነ ከሃገር ውስጥ የተለያዩ አካላት የአፍራሽ ድርጊታቸውን ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ነው የጠቀሱት፡፡

ህብረተሰቡ ሮሮውን እንዲያሰማ ምክንያት የሆኑት የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሃላፊዎች በእውቀትና ችሎታ ላይ የተመሰረተ አገልግሎት እንዲሱጡ በማድረግ ህጋዊ ተጠያቂነትን ማስፈን ግዴታ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ህብረተሰቡን እያማረረ የሚገኘውን የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ መንግስት በትክክለኛ የስራ ልምድ፤ ትምህርትና እውቀት ላይ የተመሰረተ የመንግስት ሰራተኞች ምድባ እንዲካሄድ ለመድረግ አንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

የመንግስት ተቋማት አላስፈላጊ በሆኑ እና በተንዛዙ ስብሰባዎች የስራ ሰዓትን በማባከን ህብረተሰቡ በፈለገው ጊዜ አገልግሎት እያገኘ ባለመሆኑ በአብሮነት እና በይቻላል ስሜት ከተሰራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል የተናገሩት፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጻ እስካሁን ካጋጠሙ ችግሮችም ትምህርትና ግንዛቤ በመውሰድ ለወደ ፊቱ ለህዝቡ ጠቃሚ ስራን ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

የህዝቡን ችግር ለመፍታት እና ጥያቄዎቸን ለመፍታት ከቃል ባለፈ መንግስት ከህብረተሰቡ ጋር ተግቶ ይሰራል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሃገሪቱ የተቻለውን ድርሻ እንዲያበረክት ለማድረግ እኩል ተጠቃሚነትን የሚያሰፍን ስርዓትን ለመዘርጋት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ነው የተናገሩት፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት፤ ጋዜጠኞች፤ አመራሮች እና ባለቤቶች፤ የጥበብ ባለሙያዎችም የሃገሪቱን ገጽታ ግንባታ ለማፈጠንና ትውልድ ሙስናን እና ሌብነት የሚጠየፍ፤ በአቋራጭ ሳይሆን ሰርቶ ለፍቶ ሃብት ማፍራት እንደሚቻል ለማሳየት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡

በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እየፈጠረ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ችግርንም ለመቅረፍ የገቢና ወጪ ስርዓትን ማስፈን፤ የአግሮ ኢንደስትሪን በጥራት ማምረት ይገባል ነው ያሉት፡፡

የምንዛሪ ችግርን ለመቅረፍ በሃገሪቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር ይደረጋል፡፡
የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችም በሃገራቸው በኢንቨስትምንት ዘርፉ እንዲሰማሩ ልዩ ድጋፍ እና ማበረታቻ ያሰፍለጋቸዋል ብለዋል፡፡

ትርጉም ያለው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ለማስፈን ኢህአዴግ ብቻውን የሚወጣው ሳይሆን ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ድጋፍ ሊሰጣች እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የሃገሪቱ የጸጥታ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እየተወጡ ቢሆንም ወደፊት እነዚህ አካላት ከፖለቲካ ነጻ ሆነው ህብረተሰቡን በቅንነት ማገልገል እንዲችሉ ለማድረግ እንዲሁን ህጋዊ ተጠያቂነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ለመንግስት አንድ ዋንኛ የቤት ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሚቀጥለው የመንግስት መዋቅር ማሻሻያ ላይም ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ፍኖተ ካርት ይዘጋል ነው ያሉት፡፡

ለወጣቶች ልዩ ትኩረት ባለመሰጠቱ ለስደትና ለከፋ ድህነት እየተጋለጡ በመሆናቸው በወንጀልና በልዩ ልዩ አፍራሽ ድርጊቶች ላይ እየተሰማሩ ስለሚገኙ ለወጣቶች የስራ ፈጠራ ትኩረት እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት፡፡

አሁን ወጣቱ ያለውን እምቅ ሃብት ለሃገሪቱ ልማትና ብልጽግና ላይ እንዲያውለም ጠይቀዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy