Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የለውጡ አመላካቾች…

0 352

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የለውጡ አመላካቾች…

                                                           ታዬ ከበደ

አርሶ አደሩን ከዝናብ ጥገኝነት እና ከተለመደው የአመራረት ልማድ እንዲላቀቅ ለማድረግ ቀደም ሲል በቂ ዝግጅት መደረጉን ይታወሳል። በዚህም በተያዘው ዓመት በመስኖ ልማት ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር ለመሸፈን ተችሏል። በመጀመሪያው ዙር የመስኖ ልማትም ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊየን አርሶ አደሮች ተሳታፊ መሆን ችለዋል። ይህም የተፋሰስ ስራው ለውጥ እያመጣ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ለውጡም አርሶ አደሩ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ሰብሎችን፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችንና በገበያ ተፈላጊና የተሻለ ገቢ የሚያስገኙ ምርቶችን እንዲያመርት አድርጎታል።

እርግጥ አርሶ አደሩ ዛሬ ከዝናብ ጥገኝነት በተላቀቁ አመራረት የተገኙትን ምርቶች መጠቀምም እየተቻለ ነው። የመስኖ ልማት ሥራው በበጋ የበቆሎ እሸት ተመጋቢዎች እንዲሆን አስችሎናል። ባለፉት ዓመታት ሥራው ከሁለት እጥፍ በላይ አድጓል። ወጣቶችም በተለይ በተፋሰስ ስራዎች ተጠቃሚ እየሆኑ ነው።

የአገራችን ወጣቶች ባለፉት 16 የፈጣን ዕድገት ዓመታት ውስጥ የመንግስት ልማታዊ አቅጣጫን በሚገባ ተገንዝበዋል። ማንኛውንም ጊዜያዊ ችግር መንግስት እየፈታው ነው። በአንዳንድ ክልሎች ውስጥ ማልማት ካልቻሉ ባለሃብቶች ቦታ በመቀማት ጭምር ወጣቶችን ወደ ስራ የማስገባት ተግባር እያከናወነ ነው። ውጤትም እየተገኘበት ነው። ይህ ሁኔታም መንግስት ምን ያህል ለወጣቱ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ማሳያ ነው ማለት ይቻላል። በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ ትኩረት የመስጠት ተግባሮች እውን እየሆኑ ነው።

እርግጥ አንድ መንግሥት ወይም የፖለቲካ ድርጅት በባህሪው ህዝባዊ ከሆነ፤ የሚያከናውናቸው ማናቸውም ተግባራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያማከሉ መሆናቸው አይቀርም። የኢትዮጵያ መንግሥትም በባህሪው ህዝባዊና ልማታዊ በመሆኑ፤ ከ26 ዓመታት በላይ በአብዛኛዎቹ መስኮች ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ አድርጓል። ዛሬ በተፋሰስ ስራዎች ወጣቶች እንዲጠቀሙ እየተደረገ ያለው ተግባር አብነታዊ አስረጅ ነው።

ቀደም ባሉት ሥርዓቶች በማንነቱም ይሁን በኑሮው አንገቱን ደፍቶ ይሄድ የነበረው ወጣት፤ ዛሬ ቀና ብሎ በአገሪቱ በመመዝገብ ላይ ከሚገኘው ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት በኢኮኖሚው ላይ ባበረከተው አስተዋጽኦ መጠን በየደረጃው ተጠቃሚ ሆኖ ወደ አዲስ ምዕራፍ እየገሰገሰ ነው። ይህም በፌዴራላዊ ሥርዓቱ ያስገኘለት ውጤት መሆኑ አይካድም።

መንግስት ቀደም ባሉት ጊዜያት በአገሪቱ ውስጥ ድህነትን አቅም በፈቀደ መጠን በመቀነስ ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ እንደሚደርግ፤ ትምህርትን፣ ጤናን፣ የመሠረተ-ልማት አውታሮችን እንደሚያስፋፋ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ስር እንዲሰድ አደርጋለሁ በማለት የገባውን የተስፋ ቃል ተፈፃሚ እያደረገ ነው። የአገሪቱ ኢኮኖሚ ዋነኛ የሆነው ግብርና ለወጣቱ ስራ እንዲፈጥርና ወጣቱም ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ ነው። ወጣቶች ይህ ተጠቃሚነታቸውን ያስገኘላቸው ሥርዓቱ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።

የተፋሰስ ስራው ውጤታማ መሆኑ ከወጣቱ ባሻገር አርሶ አደሩ የምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጎታል። መንግስት የማስፋት ስትራቴጂን በመጠቀም በአነስተኛ የአርሶ አደር ማሳ ላይ ለውጥ ማምጣት ተችሏል። ይህም በአነስተኛ ማሳ ላይ ብዙ ምርት ማግኘት ያስቻለ፣ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የላቀ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተመሰረተው በግብርና ላይ እንደመሆኑ መጠን፤ የአርሶ አደሩ የአመራረት ዘይቤ መለወጡ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል።

በዚህም ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ማምረት ተችሏል። ይህም አጠቃላይ የሀገሪቱን ምጣኔ ሃብት ዕድገት ከፍ አድርጓል። በተለይ ባለፉት 10 ዓመታት የተገኘው ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት የምርትና ምርታማነት ማደግ ውጤት ነው።

ባለፉት ዓመታት መንግሥት ግብርናውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ተገንዝቦ ሲሰራ ቆይቷል። በያዝነው ሁለተኛው የልማት ዕቅድ ላይም በመጀመሪያው የዕቅድ ዓመት ላይ የተገኘውን አመርቂ ውጤት ይበልጥ አጎልብቶ ለመቀጠል እየተሰራ መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ።

የግብርና ልማት መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ይችል ዘንድ በበሁለተኛው አምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትኩረት ተሰጥቶታል። እንደሚታወቀው አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ለእርሻ ሊውል የሚችል ሰፊና ለም መሬት እንዲሁም የአርሶ አደሩ ጉልበት አለ። በሀገሪቱ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ታዲያ ይህ ግብርናው ውጭ ከፍተኛ እምቅ ሃብት ነው። ይህ ሃብት ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ሲሆን፤ ገና ምንም ያልተነካ እምቅ በመሆኑም ውጤት ሊያመጣ የሚችል ነው። ሀገሪቱን ለመለወጥ ወሳኙ ሃብት ተደርጎ መወሰዱም እንዲሁ።

ቀደም ሲል እንደገለፅኩት ምርትና ምርታማነት በማደጉ ሳቢያ የአርሶ አደሩ ህይወት በአያሌው ተለውጧል። እንዲያውም በአንዳንድ አካባቢ የሚገኙት አርሶ አደሮች ትርፍ አምራች እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። ይህ ትርፍ አምራችነታቸውም ከተጠቃሚነታቸውባሻገር ሌሎች አካባቢዎች በተፈጥሮአዊው የድርቅ አደጋ በሚጠቁበት ወቅት የሚፈጠረውን ክፍተት እየሞሉ ነው። ምርትና ምርታማነት በማደጉ ሳቢያ ከፍተኛ ምርት እንደሚገኝ ይታሰባል።

ከዚህ በተጨማሪ የሰብል ምርቱን ለማሳደግ አዳዲስና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ ለማስተዋወቅ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። እንዲሁም የአርሶ እደሩን ጉልበት የሚያግዙ የሚደግፉና ጉልበቱን ውጤታማ የሚያደርጉ መጠነኛና አነስተኛ የሜካናይዜሽን ስራዎች እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባ ጥረት እየተደረገ ነው።

ታዲያ ከዚህ የሚኒስቴሩ ማብራሪያ መረዳት የሚቻለው ነገር ቢኖር፤ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ መንግስታዊ ጥረት ላይ የተወሰኑ ተግዳሮቶች መኖራቸውን ነው። እርግጥ የግብርና ምርት የጥራት ችግርና ብክነት አሁንም ያልተሻገርናቸው ችግሮች ናቸው። ያም ሆኖ ችግሮቹን መቅረፍ ያስፈልጋል። ያም ሆኖ የመስኖ አሰራሮችን በመከተል ምርቱን ከፍ ማድረግ ይገባል።

የዋና ዋና ሰብሎችን ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ ዋናው ጉዳይ የአብዛኛውን አርሶ አደር የምርታማነት መጠን ምርጥ አርሶ አደሮች የደረሱበት ደረጃ ማድረስ መሠረታዊ ግባችን ሊሆን የሚገባ መሆኑ ነው። ይኸም በዋና ዋና የምግብ ሰብሎች፣ የፋብሪካ ግብኣቶች እንዲሁም የኤክስፖርት ሰብሎች ጭምር መከናወን ያለበት ግብ ተደርጐ ተወስዷል።

ይህ መሠረታዊ ግብ እንደተጠበቀ ሆኖ በተከታታይ የሞዴል አርሶ አደሮች ምርታማነት ደረጃ ላይ የደረሱ በርከት ያሉ አርሶ አደሮች ያሉ በመሆኑ የግብርና ምርምር ተቋማትን አቅም በማጐልበትና በማበረታታት እነዚህ አርሶ አደሮች ወደ ግብርና ምርምር ተቋማት የምርታማነት ደረጃ እንዲቀራረቡ ተጨማሪ ፓኬጆች ተዘጋጅተው ርብርብ እየተደረገባቸው ነው።  

የአርሶአደሩን የሰብል ልማት የማስፋትና ምርታማነቱንና ጥራትን ከፍ በማድረግ በገበያ ተወዳዳሪ ከመሆን በተጨማሪ የአትክልትና ፍራፍሬ የማልማት አቅሙን የማሳደግና በዘርፉ እመርታ ለማምጣት እየተሰራ ነው። አርሶአደሩ በራሱ፣ ከተማሩ ወጣት አነስተኛ የግብርና ኢንቨስተሮች ወይም ከአገር ውስጥና ከውጭ ባለሃብቶች ጋር በመቀናጀት ምርታማነትንና የምርት ጥራትን እንዲያረጋግጥ እየተሰራ ነው። ይህ ቅንጅት የሚጠቅመን አነስተኛ ማሳ ላይ የሚያመርቱ አርሶአደሮችን በአካባቢ ስፔሻላይዜሽን እንዲሳተፋ የሚያደርግ እንዲሁም የገበያ፣ የመሠረተ ልማትና ሎጅስቲክስ አቅርቦት ማነቆ እንዳይሆን የሚያግዝ ሆኗል።

ለዚህ ተግባር እውን መሆን አርሶ አደሩ የተፋሰስ ስራዎችን በአግባቡ በመጠቀሙ ነው። የተፋሰስ ስራው ቀደም ሲል የነበሩትን ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴን በመቀየር ውጤት በማምጣቱ አስሮ አደሩ የለውጡ ተጠቃሚ እየሆነ ነው። ይህን ተጠቃሚነቱን በማጠናከር የራሱንና የአገርን ለውጥ እውን ሊያደርግ ይገባል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy