NEWS

የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና ረቂቅ አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

By Admin

April 15, 2018

የጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችንና ረቂቅ አዋጆችን በማፅደቅ ተጠናቀቀ።

ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የጨፌው መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቋል።

ጉባኤው በዛሬው ቆይታ አቶ ደሳ ቡልቻ ነሞምሳን የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እንዲሁም አቶ ማህመድኑሬ ጎበናን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።

ወይዘሮ ማህቡባ አደም የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ፣ አቶ ወርቁ ጋቸና የኦሮሚያ ክልል ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ አዲሱ አረጋን የኦሮሚያ ክልል ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ የቦርድ ሰብሳቢ በማድረግ ሾሟቸዋል።

ከዚህ ባለፈም በ2002 ዓ.ም የክልሉን የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ እና የኦሮሚያ ክልል ብሮድካስቲንግ ኔትወርክን ዳግም ለማቋቋም የወጣውን አዋጅም አጽድቆታል።