Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

“ይህን እሳት ፋብሪካ ገንቡበት…”

0 355

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“ይህን እሳት ፋብሪካ ገንቡበት…”

ስሜነህ

“እናንተ ተስፋ ካላችሁ ሁላችንም ተስፋ ይኖረናል! እውቁ ግሪካዊ ዪሪፒደስ በአንድ ወቅት እንዳለው ሃብታም ለመሆን ከሁሉም የተሻለው ጊዜ ወጣትነት ነው፤ ድሃ ለመሆንም ከሁሉም የተሻለው ጊዜ አሁንም ወጣትነት ነው፡፡ ሁለቱም ያለው በእጃችሁ ስለሆነ፤ እባካችሁ የተሻለውን ምረጡ፡፡ እናንተ ተስፋ ካላችሁ ሁላችንም ተስፋ ይኖረናል! ሃገራችንም ተስፋ ይኖራታል፡፡የኢትዮጵያ ተስፋ እውን ይሆን ዘንድ ክንዳችንን አጠናክረን በጋራ ስራ ሳንንቅ እንድንተጋና ጉልበታችንን ሃብት ለመፍጠር እንድናውል በታላቅ ትህትና ልጠይቃችሁ እፈልጋለው፡፡” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሚሊኒየም አዳራሽ ለወጣቶች ካስተላለፉት መልእክት የተወሰደ ነው። ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነውም ይህና ተከታዩ የጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር ነው።

“ውድ የሃገሬ ወጣቶች ፤-ወጣትነት የእሳት ጊዜ ነው፡፡ወጣትነት ውስጥ በእርግጥም እሳትነትና ከባድ ግለት አለ፡፡ ይሄንን እሳት ብረት አቅልጡበት ወንዝ ጥለፉበት ተራራ ናዱበት፤ይሄንን እሳት ፋብሪካ ገንቡበት፤ይሄንን እሳት ድልድይ አንፁበት  ከምንም ከማንም በላይ ደግሞ ይሄንን እሳት ህይወት ለማዳን ተገልገሉበት፡፡” የዚህ መልእክት አድራሻን መጠቆም ነው የዚህ ጽሁፍ ግብ። አድራሻው የሚገኘው ደግሞ በሁለተኛው ዙር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ነው።

ወጣቶች የዛሬ አፍላ የልማትና የዴሞክራሲ ኃይሎችና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች እንደመሆናቸው በትምህርት የታነፀና የተገነባ አቅም እንዲኖራቸው ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑ በእቅዱ ተመልክቷል፡፡ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ብቃት

በማሳደግ በሀገሪቱ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም ልማታዊ አስተዳደር ግንባታ እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተደራጀና በተቀናጀ አኳኋን የነቃና ግንባር ቀደም ተሳትፎ እንዲያደርጉና ከውጤቱም በተገቢው መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደረግ መሆኑም በመንግስት በኩል አስቀድሞም አቋም የተያዘበት ነው፡፡ ይህንን በማድረግ በሀገሪቱ ወጣቶች ከሥራ ስምሪት ጋር ተያይዞ የሚታየውን የተሳታፊነትና ፍትሐዊ ተጠቀቃሚነት ጥያቄ ለመመለስ ከወጣቱም አካባቢ ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን የተመለከተ ነው የጠቅላይ ሚንስትሩ ከላይ የተመለከተ መልእክት የሚያሳስበው።  

የሴቶችና የወጣቶች ፓኬጆች ትስስርና ተመጋጋቢነት ባለው ሁኔታ ተፈጻሚ እንዲሆን ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን የተለያዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፎች የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑ፣ ወጣቶች በህብረት ሥራ ማህበራት በመደራጀት የብድርና ቁጣባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግም መንግስት ስራ መጀመሩን እዚህ ላይ ልብ ማለት ያሻል፡፡

በተለይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከቴክኒክ ሥልጠና ማዕከላት ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት የወደፊት የሀገራችን ተስፋ በሆኑ አምራች ዘርፎች ማለትም ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችና ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ተሠማርተው የወደፊት የሀገራችን ልማታዊ ባለሀብቶች መፍለቂያ እንዲሆኑ ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ  እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ውስጥ የወጣቶች እሳትነት አስፈላጊ ይሆናል

የሴቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በማሳደግ በሀገሪቱ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዳደር ግንባታ እንዲሁም በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ በተደራጀ አኳኋን የነቃና ግንባር ቀደም ተሳትፎ እንዲያደርጉና ከውጤቱም በተገቢው መንገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደረግ እንደሆነም በእቅዱ ተመልክቷል፡፡ጠቅላይ ሚንስትሩም በበአለ ሲመታቸው ይህንኑ ማጽናታቸውንም ማስታወስ ይገባል። ካለሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ የትኛውንም አይነት ውጤት ማምጣት ስለማይቻል።

ሴቶች በብዙ አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ኢትዮጵያን ገንብተው ፣ ታሪክ ሰርተው እና ትውልድ ቀርጸው ኢትዮጵያን ዛሬ ላይ ማድረሳቸው አይተባበልም።   “በትግላችሁም የተሻለች ሃገር እንድትኖረን ብዙ መስዋዕትነት ከፍላችኋል።” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ አጽንኦት መስጠታቸውም ስለዚህ ነው። “ትግላችሁ የፍትህ ትግል ነው፣ ትግላችሁ ክቡር ትግል ነው፣ ትግላችሁ ትግላችን ነው።” ስለዚሁ ወሳኝነት ያለው ሃገራዊ ሚናቸው ነው። መንግስት የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና በሃገራችን ሁለንተናዊ የእድገት ግስጋሴ ውስጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ከሰራው ይልቅ ያልሰራቸው ስራዎች እጅግ እንደሚበዙ እንደሆነም አምኗል።እምነቱንም “ በቀጣይ የሃገራችን ሴቶች ተፈጥሮ እና ኑሮ የሰጧችሁን በረከቶች ተጠቅማችሁ ለሃገራችን እድገት እና ብልጽግና እንዲሁም ለፖለቲካችንም ስምረት አዎንታዊ ሚና እንደምትጫወቱ ተስፋዬ የላቀ ነው።”ሲል በጠቅላይ ሚንስትሩ በኩል አረጋግጧል።

አገራዊ ማንነታችን  ያለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ምንም ነው። አገሪቷን የገነቡ፣ ያገለገሉ፣ ያቆሙ ሴቶችን እውቅና በመንፈግ ሀገራዊ ትንሳኤን ማረጋገጥ አይቻልም። መንግስታችን ለሴቶች መብትና እኩልነት የሚቆመው፣ ለሴቶች ውለታ ለመዋል ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵ ነው። ግማሽ አካሉን የረሳን ሀገር ሙሉ የሀገር ስዕል ይኖረው ዘንድ ከቶ እንደማይችልና ወደፊትም እንደማይራመድ መንግስት በውል የተገነዘበ መሆኑንም አረጋግጧል።“ በመሆኑም መንግስታችን ከዚህ ቀደም ከነበረው ፍጥነት እና የትግበራ ስኬት በላቀ መልኩ ለሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት ይሰራል።” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ በበአለ ሲመታቸው መናገራቸውም ስለዚሁ እና አስቀድሞም በእቅድ ዘመኑ ላይ ስለተመለከተና በመንግስት በኩል አጽንኦት ስለተሰጠው ነው።

የሴቶችና የወጣቶች ፓኬጆች ትስስርና ተመጋጋቢነት ባለው ሁኔታ ተፈጻሚ እንዲሆን ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን የተለያዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፎች የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆኑ፣ ሴቶች በህብረት ሥራ ማህበራት በመደራጀት የብድርና ቁጣባ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚደረግ እንደሆነ ከዛሬ ሁለት አመት አስቀድሞ ተወጥኗል፡፡የወጣችና ሴቶች እሳትነት ከተጨመረበት ነገ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል በጣም ቀላል የሆነ ስራ ነው።

በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች የሥርዓተ ጾታ ዕኩልነትን ማረጋገጥ፣ ለሴት ተማሪዎች ምቹ የትምህርት ከባቢ ሁኔታ መፍጠር፣ የሴት መምህራን ቁጥርን ከፍ ማድረግ፣ የጾታ ዕኩልነትን በሥራ ሥምሪት፣ በመሬትና ሌሎች ቋሚ ዕሴቶች ባለቤትነት ማሳደግ፣ ጐጂ የሆኑ ባህሎችን ለምሳሌ በሴቶች ላይ በሚደረግ የኃይል ጥቃት፣ በፍትህ ሥርዓቱ ተደራሽነት እና በሴቶች ላይ ህገወጥ ድርጊት ፈፃሚዎች ላይ ወቅታዊ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ የሚደረግ መሆኑን የተመለከተው ውጥን ደግሞ የወጣቶችና ሴቶችን እሳትነት የሚያጋግል ቤንዚን ነው፡፡ እንዲሁም ሴቶችን በፖለቲካና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ዕኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠውና ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል የሚለው የእቅዱ አካል በሚንስትሮች ምክር ቤት ሹመት ላይ በተግባር የታየና የመንግስትን ቁርጠኝነት ያመላከተ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy