Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ዶ/ር ወርቅነህ ታዋቂውን እግር ኳስ ተጫዋች ሮናልዲኒሆን በጽ/ቤታቸው ተቀበሉ

0 725

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ዶ/ር ወርቅነህ ታዋቂውን እግር ኳስ ተጫዋች ሮናልዲኒሆን በጽ/ቤታቸው ተቀበሉ

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዝነኛውን የብራዚል እግር ኳስ ተጫዋች ሮናልዶ ዲ አሲስ ሞሬራን(ሮናልዲኒሆ ጎቾ) ዛሬ ከሰዓት በኋላ በጽ/ቤታቸው አነጋግረዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ሮናልዲኒሆን ሲቀበሉ የሰው ልጅ መገኛ ወደ ሆነችዉ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጣህ ብለዋል። የስፖርት ዲፕሎማሲው የዘመናዊ ዲፕሎማሲ አካል መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ ስፖርት ዘር እና ሀይማኖትን ሳይለይ ለሰዎች አንድነት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።

ስፖርት በተለይ የእግር ኳስ ዓለምን እንደ አንድ አድርጎታል ያሉት ዶ/ር ወርቅነህ የሮናልዲኒሆ የግል አድናቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የጠንካራ አትሌቶች አገር የመሆኗን ያህል ብራዚልም የእግር ኳስ ታዋቂ ተጫዋቾች አገር ናት ብለዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ እንደገለፁት ሮናልዲኒሆን ያበቀለችሁ ብራዚል እና ኢትዮጵያ ብዙ ተመሳሳይነት አላቸው። ኢትዮጵያ እንደ አበበ ቢቂላ ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩፅ ይፍጠር፣ ሀይሌ ገብረስለሴ፣ ቀነኒሳ በቀለ ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ የዲባባ ቤተሰቦች እና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶችን ያፈራች አገር ስትሆን በተመሳሳይም ብራዚል የእና ፔሌ፣ስቆራትስ ፣ዱንጋ ፣ቤቤቶ፣ሮማሪዮ ሮናልዶ ፣ኔማር የመሰሉ የዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ልጆች እናት ናት ከእነርሱ አንዱ ጎቾ ነው።

ሮናልዲኒሆ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን ጠቅሶ ስለ አገሪቷ የበለጠ ለማወቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል። ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲታዩ ጠንክረው መስራት አለባቸው ብሏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy