Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፌዴራሊዝም እና ኢትዮጵያ

0 416

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ፌዴራሊዝም እና ኢትዮጵያ

ወንድይራድ ኃብተየስ
ፌዴራሊዝም የመንግሥት ሥልጣንና ተግባራት በፌዴራል የመንግሥት መስተዳድር እና በክልል መንግሥታት መካከል
በሕገ-መንግሥት በግልፅ የሚከፋፈልበት ሥርዓት ነው። በዓለማችን በርካታ አገሮች ፌዴራላዊ የመንግሥት አወቃቀር
ሥርዓትን ይከተላሉ።እነዚህ አገሮች ይህን ስርዓት ሲመርጡ እንደየአካባቢያቸው ነባራዊ ሁኔታ፣ ታሪክ፣ ወግ፣ ባህልና
ከህዝቦቻቸው ፍላጎት በመነሳት ነው።
ከዚህ በተጨማሪም የፌዴራል ሥርዓትን የሚከተሉ አገሮች በተለየ አግባብ ለህገ-መንግሥት የበላይነት መረጋገጥ ልዩ
ትኩረት ይሰጣሉ። ምክንያቱም የፌዴራል ህገ-መንግሥት የፌዴራል የፖለቲካ ማኅበረሰብ ከመገንባትም ባሻገር ሕዝቦች
ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤት መሆናቸውን መሠረት ስለሚደርግ ነው። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ብዝሃነትን
ለሚያስተናግዱ አገራት ፌዴራላዊ ሥርዓት አማራጨ የሌለው ነው።
በዚህ ሥርዓት ውስጥ ደግሞ የመንግሥት ሥልጣን፣ ኃላፊነት፣ አስተዳደር፣ ግብር የመሰብሰብና የፋይናንስ ሀብት
የውሣኔ አሰጣጥ ሂደት በአንድ ማዕከል ወይም ቦታ ብቻ እንዲከማች አይደረግም።
የፌዴራል የፖለቲካ ሥርዓትን የሚከተሉ አገሮች የተፃፈ ህገ መንግሥት ያላቸው ናቸው። ህገ-መንግሥት በአንድ
የፖለቲካ ማኅበረሰብ ውስጥ በጋራ ጉዳዮቻቸው የጋራ የመንግሥት መስተዳድር ተቋማትን አቋቁመው ለየራሳቸው
ጉዳዮች ደግሞ ከሌላው የራስ መንግሥት መስተዳድርን በማቋቋም ፈቃድና ፍላጎታቸውን የገለፁበት የቃል ኪዳን ሰነድ
ነው። በዚህም የፌዴራል ሥርዓቱ መስተዳድሮቹ ለህገ-መንግሥቱ ተገዥ የመሆን ግዴታ እንዳለባቸው ያስገድዳል።
የፌዴራል የፖለቲካ ስርዓትን የሚከተሉ ሀገሮች የተፃፈ ሕገ መንግስት ያላቸው ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም የዚሁ
ስርዓት ተከታይ ሀገሮች በተለያየ ሁኔታ ለሕገ-መንግስት የበላይነት መረጋገጥ ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ።
የፌዴራሊዝም ሥርዓት አንድነት የሚያራምደው ፌዴሬሽኑን ያቋቋሙትን አካላት የተለየ ማንነት የራሳቸው ለሆኑ
ጉዳዮች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበትን ብሎም ለጋራ ጉዳዮቻቸው በጋራ መስተዳድራቸው የውሣኔ
አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የሚወከሉበትንና የሚሳተፉበትን ተቋማዊ ማዕቀፍ በህገ መንግሥት ዋስትና የሚሰጥ የሥርዓት
አወቃቀር ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ፌዴራሊዝም የሚያልመው በአንድና በተመሳሳይ ጊዜ አንድነትንና
ህብረብሔራዊነትን በመጠበቅና በመኮትኮት ዓላማ ያለው መሆኑ ነው። በዚህም የተነሳ በፌዴራላዊ ሥርዓቱ የጋራ
እሴቶችን እና ሁሉ አቀፍ ማንነትን መገንባት ይቻላል።
በዚህ ረገድ የፌዴራሊዝም ሥርዓት ነፃነትን እና ዴሞክራሲን በማጠናከር በኩል ቁልፍ ሚና አለው። የመንግሥትን
ሥልጣን እንደተለመደው ወደ ጎን በማለት በህግ አውጪው፣ በህግ አስፈፃሚውና በዳኝነት አካላት መካከል ብቻ
በማከፋፈል ሳይሆን ፌዴራሊዝም የመንግሥትን ሥልጣን በአግድሞሽ በፌዴራል መስተዳድሩና በአባል ክልል
መንግሥታት መካከል በማከፋፈል ሥልጣን ላይ ተጨማሪ ገደቦችን በመጣል ለግለሰቦችና ለማኅበረሰቦች የተግባር
ነፃነትን እና የፖለቲካ ሥልጣን ምህዳርን ያሰፍናል።
የፌዴራሊዝም ሥርዓት ከውጭ የሚመጣ ወታደራዊ ጥቃትን ወይም የጦርነት ሥጋትን በመከላከል ሠላም እና
ደህንነት እንዲረጋገጥ ይረዳል። ይህ ጉዳይ በተሳካላቸው አገሮች የፌዴራሊዝም ሥርዓትን በመሠረቱበት
የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ጥቃትንና ሥጋትን በጋራ የመከላከል እሴት ተስተውሏል። ለአብነት በአሜሪካ የውጭ ጥቃትን
ወይም የጦርነት ሥጋትን በጋራ የመመከትና ሠላምና ፀጥታን ማስፈን ዓይነተኛ የፌዴራሊዝም እሴት ሆኖ እያገለገ
ይገኛል። በአሜሪካ ኮንፌዴሬሽን ውስጥ ያሉት መንግሥታት ፌዴሬሽንን ያቋቋሙበት አንዱ ዐብይ ምክንያታቸው
ከውጭ ሊቃጣባቸው የሚችሉ ጦርነቶችን እና የጦርነት ሥጋቶችን ለማምከንና ለመከላከል ጠንካራ የመከላከያ አቅም
ለመፍጠር በማቀዳቸው ነው።

ከዚህም አልፎ የፌዴራሊዝም ሥርዓት የማኅበረሰብንም ሆነ የግል ነፃነቶችን ለመጠበቅ የሚያገለግል ጠቃሚ
የመንግሥት አወቃቀር መሆኑን መመልከት ይቻላል። በመሆኑም የፌዴራላዊ ሥርዓት በማንኛውም ወቅት የሚፈጠሩ
ነባራዊ ችግሮችን መፍታት የሚችልበት የፖለቲካ ምህዳር አለው። የሥርዓቱን ጥቅሞች እስከመጨረሻው ድረስ አሟጦ
መጠቀም እንዲሁም በሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችንም በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችል የመፍትሄ አካል
ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy