Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

…ለአገሩ!

0 496

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

…ለአገሩ!

                                                        ታዬ ከበደ

የዓለም ላብ አደሮች ቀን ሚያዚያ 23 ቀን 2010 ዓ.ም በአገራችን ተከብሮ ውሏል። እንደሚታወቀው ለዓለም የላብ አደሮች ቀን በዓል ወይም ሜይ ዴይ ውልደት ቀጥተኛ መነሻ የሆነው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1884 በአሜሪካ የተካሄደው አንድ ሰራተኛ በቀን ውስጥ ለስምንት ሰዓት ብቻ በስራ ላይ መቆየት አለበት የሚለው ትግል ነው።

ይህ የሰራተኞች እንቅስቃሴ በአሜሪካ የላብ አደሮች ፌደሬሽን እንዲቋቋም ምክንያት ሆነ። በቺካጎ በተካሄደው ብሄራዊ ኮንቬንሽንም በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሜይ አንድ 1886 ጀምሮ ስመንት ሰዓት የእለት ህጋዊ የስራ ሰዓት ሆኖ ታወጀ።

የሰራተኞቹ እንቅስቃሴና የትግል ውጤትም በመላው ዓለም ተስፋፍቶ በፈረንጆቹ በ1890 ሜይ 1 የአለም የላብ አደሮች ቀን ሆኖ እንዲዘከር ተወሰነ። በዓሉ ዘንድሮም በዓለም ከ129ኛ ጊዜ በዓሉ ሲከበር በኢትዮጵያም ለ43ኛ ጊዜ ተከብሮ ውሏል። በዚህ መሰረትም “የተረጋጋ የኢንዱስትሪ ሰላም በተደራጀ ሰራተኛ ይረጋገጣል” ቢል መሪ ቃል በአገራችን ዕለቱ ተከብሯል።

ላብ አደሩ አገራችን ለምታደርገው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር እየተወጣ ያለውን ሚና ከፍተኛ ነው። በመሆኑም በየተሰማራበት የሙያ መስክ ለአገሩ ይበልጥ ተግቶ በመስራት ህዳሴዋን ቅርብ ማድረግ ይኖርበታል።

እንደሚታወቀው ሁሉ የመደራጀት መብት አገራችን ውስጥ ህገ-መንግስታዊ እውቅና እና ከለላ የተሰጠው ነው። ማንኛውም ዜጋ ለፈለገው ዓላማ የመደራጀት መብት አለው። በተናጠል፣ በግንባር፣ በቅንጅትና በውህደት ተሰባስበው ተደራጅተው እውቅና የተሰጣቸው አካላት በርካታ ናቸው።

ከእነዚህ አደረጃጀቶች ውሰጥ ውስጥ ላብ አደሩም ጥቅሙን ለማስከበር ሲል በሰራተኛ ማህበር ከንፌዴሬሽን አማካኝነት ተደራጅቷል። ይህ እውን የሆነው በኢፌዴሪ ህገ መንግሥት ነው።

ላብ አደሩ በአብዛኛው የሚገኝበት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ውጤት እንዲያመጣ መንግሥት ትኩረት ሰጥቷል። ላብ አደሩ የአገሩን ህዳሴ እውን ለማድረግ የበኩሉን ሚና መጫወት ይኖርበታል።

እንደሚታወቀው የኢንዱስትሪው ዘርፍ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥን ዕውን ለማድረግ የሚከናወነው ስራም ሀገራችን ለነደፈችው ራዕይ የሚጫወተው ሚና ሊተካ አይችልም። እንዲያውም የሞት ሽረት ጉዳይ ነው ማለት ይቻላል። ለዚህም ከተጀመረ ሶስተኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።

ይህ ዕውነታም የሀገር ውስጥና የውጭ ቀጥተኛ በአዳዲስ ኢንቨስትመንቶችም ሆነ በነባር ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የምርታማነት የጥራትና የተወዳዳሪነት ደረጃ እመርታና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመጣ በከፍተኛ ደረጃ መንቀሳቀስ እንዲቻል ያደርጋል።

እናም በልማት ዕቅዱ ዘመን በኢኮኖሚው ላይ የሚታይ መዋቅራዊ ለውጥን ለማስጀመር የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በየዓመቱ ቢያንስ የ24 በመቶ ዓመታዊ አማካይ ዕድገት ማስመዝገብ ይኖርበታል። ይህ ማለት በ2012 ዓ.ም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለውን ድርሻ ወደ ስምንት በመቶ ከፍ እንዲል ያደርገዋል።

ይህ ለውጥም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ድርሻ በአሁኑ ወቅት ከሚገኝበት በአራት እጥፍ እንዲያድግ በማድረግ ወደ መጀመሪያው የመካከለኛ ጉዞ መንገድ ለመድረስ ለታለመው ዕቅድ እስከ 18 በመቶ የማድረስ ግብን ዕውን ይጥላል። ሀገራችን ለያዘችው የመካከለኛ ገቢ ራዕይን ለማሳካትም መደላድል ይፈጥራል። በዚህ ሂደት ውስጥ ላብ አደሩ ጉልህ ሚና ማበርከት ይኖርበታል።

መዋቅራዊ ለውጡን ገቢራዊ በማድረግ ረገድ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው የኤክስፖርት ሚናው ሁነኛ ማሳያ ነው። ዛሬን ከነገ ጋር ብናስተያየው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ አሁን ካለው ሁኔታ አኳያ ሲታይ ከጠቅላላው የኤክስፖርት ገቢ ከአስር በመቶ አይበልጥም።  

ይሁን እንጂ ይህን አሃዝ በ2012 ዓ.ም ላይ ወደ 25 በመቶ ከፍ ለማድረግ ታስቧል— አምስት ቢልዮን ዶላር ገቢ እንዲያስገኝ ለማድረግ በማሰብ። የዚህ ድምር ውጤትም ወደ መካከለኛ ገቢ እናመራለን ብለን ባሰብንበት በ2017 ዓ.ም 40 በመቶ እንዲደርስ ትልም ተይዟል። ላብ አደሩ ቀጥተኛ ተግባሩን መወጣት ከቻለ ይህን እውን ማድረግ የሚከብድ አይደለም።

እርግጥ መንግስት የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከወዲሁ እያከናወና ያለውና በዕቅድ ደረጃ የያዛቸው የተለያያዩ የተጠቃሚነት ማዕቀፎች ሃቁን የሚያሳዩ በመሆናቸው በቀሪው የልማት ዕቅዱ ዘመን ላብ አደሮች ተግባራቸውን በብቃት መወጣት ከቻሉ ስኬቱን ማረጋገጥ ይቻላል።

እርግጥ በዕቅዱ ላይ በዘርፉ የተጠቀሱትን ስኬቶች እውን ለማድረግ በሁለት ዘርፎች ትልሞች ተይዘዋል—በጥቃቅንና አነስተኛና መካከለኛ እንዲሁም ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ለመስጠት።

ይህ ሁኔታም በሁለቱም ዘርፎች ውስጥ ኤክስፖርት መር የኢንዱስትሪ አቅጣጫን ለመከተልና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ በሚደረገው ሽግግር ውሰጥ የራሱን ሚና ይጫወታል። ለሽግግሩ የመሪነት ሚናውን የሚጫወተው መንግሥት ተግባሩ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ላብ አደሩም በተሰማራበት መስክ የመኩሉን ማበርከት ከቻለ ውጤቱ ያማረ ይሆናል።

መንግስትም ዜጎቹ በተለየዩ የስራ አማራጮች መብቶቻቸው ተከብረው መስራት እንዲችሉ በየጊዜው የሰራተኛውን ጥቅም የሚያሳድጉ ይቀይሳል። የሰራተኞችን የመደራጀት ህገ መንግስታዊ መብት በሚነፍጉ አሰሪዎች ላይ መንግስት እርምጃ ሊወስድ መውሰድ ይኖርበታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰራተኛ አገናኝ በሆኑ ኤጀንሲዎች በኩል ባልተገባ መንገድ የሚፈጸሙ የሰራተኞች የጉልበት ብዝበዛ ላይ
መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግም አለበት።

ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እውቀት የማይጠይቁ የስራ መስኮች አሁን ላይ በውጭ ሀገር ዜጎች እየተያዙ መምጣታቸው ሰፊ የስራ አጥ ቁጥር ባለበት አገር ላይ አሳሳቢ መሆኑን አንስተዋል።

ዝቅተኛ ወይም መነሻ ደመወዝ ወለል በአገር አቀፍ ደረጃ ለመተበበር የተያዘው እቅድ ለሰራተኛው የስራ ላይ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል በፍጥነት ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል። በአጣቃላይ መንግስት የራሱን ኃላፊነት የሚወጣ ሲሆን ላብ አደሩም ለአገሩ ኢንዱስትሪ እመርታና ኢንዱስትሪው ከግብርናው የመሪነት ሚናውን ለመውሰድ የሚደረገውን ርብርብ መደገፍ ያለበት ይመስለኛል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy