Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አለመረጋጋቶችን በህግ የበላይነት

0 266

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አለመረጋጋቶችን በህግ የበላይነት

                                                          ሶሪ ገመዳ

በአንዳንድ አካባቢዎች ብቅ ጥልቅ የሚሉ አለመረጋጋቶችን በተመለከተ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። መንግሥት ይህን የማደረግ ሃላፊነት ያለበት አካል ነው። አሁን ባለው ሁኔታ የኮማንድ ፖስቱ ፀጥታ የማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚወጣ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። በዚህም የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶ ገልጿል።

እርግጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ ጥያቄዎች መሠረት አድርጎ የሚካሄደው ማንኛውም ተቃውሞ ጥያቄዎቹም ይሁኑ ጥያቄዎቹ የሚቀርቡበት መንገድ ሰላማዊና ሕጋዊ መሆን ይኖርባቸዋል። ህገ ወጥ አካሄዶች ለአገርም ሆነ ለህዝብ የማይጠቅሙ ብቻ ሳይሆኑ፣ ጎጂም ስለሆኑ መንግሥት የህግ የበላይነትን የማስከበር ኃላፊነት ስላለበት ይህንኑ መገንዘብ ይገባል።

በማንኛውም አገር ውስጥ የዜጎች ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በህግና ሥርዓት የሚመራ ካልሆነ የትኛውም ወገን የመኖር ዋስትና ሊኖረው አይችልም። የመኖር ዋስትና በሌለበት ሀገር ውስጥ ደግሞ ሰላምና መረጋጋት ይጠፋና እንደ ሰው ለመንቀሳቀስ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ሊደረስ ይችላል።

መብት ሰጪና ነሺ በጉልበታቸው የሚተማመኑ ጉልበተኞች ይሆናሉ። ጉልበተኞቹም በህገ ወጥነት ሌሎች ዜጎችን እንዳሻቸው ለማድረግ መሻታቸው የሚቀር አይደለም። እንኳንስ ዜጎችን ቀርቶ፣ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ የሚተጉ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎችን ጭምር በአጉራ ዘለለልነት እስከማጥቃት ይደርሳሉ።

ታዲያ ይህን ሁኔታ ለመከላከልና በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የህግ የበላይነት መኖር የግድ ይላል። እርግጥ መንግስት ባለበት ሀገር ውስጥ ማንም ሰው ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየደረጋቸው ከመጣው መንገድ መውጣት የለበትም።

እርግጥ ኢትዮጵያ የጀመረችው የዕድገትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ባህል ግንባታ ሂደት ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል፤ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነበት ምህዳርን መፍጠር የግድ ነው። ምክንያቱም ሀገራችን ፈጣን ልማትን ማምጣትና ከተመፅዋችነት መላቀቅ ብሎም ዴሞክራሲን መገንባት የሞት ሽረት ያህል የህልውና ጉዳይ አድርጋ ስለያዘችው ነው።

ታዲያ ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላት ዘንድ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚኖርባት ይመስለኛል።

የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ሰላምን እንጎናፀፋለን። ሰላምን ስንጎናፀፍ ደግሞ የምናውዳቸውን የልማትና የዴሞፐክራሲ ስራዎችን ዕውን እናደርጋለን። ህጎች ለአንዱ የሚሰሩ ለሌላው ደግሞ የማይሰሩ ለሆኑ አይችሉም።

ህግ ለድርድር ሳይቀርብ ሲቀር ሁላችንም በህግ ፊት እኩል እንስተናገዳለን። የሚያንስም ይሁን የሚበልጥ አይኖርም። የህግ የበላይነት ሲኖር ሁላችንም ከሚገኘው ሀገራዊ ጥቅም ተካፋዩች እንሆናለን። ከሁሉም በላይ ደግሞ የሀገራችንን ህገ መንግስት አክብረን እናስከብራለን።

እንደሚታወቀው ሁሉ ህገ መንግስቱ የህጎች ሁሉ የበላይ መሆኑ፤ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት እንደሆነ፤ ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለስልጣኖቻቸው ህገ መንግስቱን የማክበርና ለህገ መንግስቱ ተገዥ የመሆን ኃላፊነት እንዳለባቸው ይደነግጋል። ይህን የህግ የበላይነት አለመፈፀምና ለድርድር ለማቅረብ መሞከር መልሶ ከህገ መንግስቱ ጋር መጋጨት ይሆናል።

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን የምታከብረው የምትከተለው ፌዴራላዊ ስርዓት ስለሚያዛት ብቻ ነው። ስርዓቱ ደግሞ ህዝቦች በበርካታ መስዕዋትነት ያመጡት ነው። ራሳቸው ይሁንታ እነዚህ ሀገር ውስጥ እውን እንዲሆን የፈቀዱት ነው። ሰብዓዊ መብቶችን በማይነካና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የህግ የበላይነትን የማስከር ስራ እንዲከናወን ይፈቅዳል።

በአጠቃላይ ሰላምን እውን ለማድረግ፣ ልማትንና ዴሞክራሲን ለማሳለጥ የህግ የበላይነት እውን እንዲሆን የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።

በዴሞክራሲያዊ አገር ውስጥ የህግ የበላይነት ልዕልና ካልተጠበቀ በሀገሪቱ የሚረቀቁ ማናቸውም ህጎች በሚፈለገው መጠን ገቢራዊ ሊሆኑ አይችሉም። ህጎች በሚፈለገው መጠን ገቢራዊ ካልሆኑና በቸልታ የሚታለፉ ከሆኑ የዜጎች መብቶች ሊሸራረፉ ይችላሉ።

የመብት መሸራረፎች ደግሞ አንዱ እንዳሻው እንዲፈነጭ የሚያደርገው ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ህግና ስርዓትን አክብሮ እንዲንቀሳቀስ ያደርገዋል። ይህም ህግና ስርዓትን የሚያከብረው ዜጋ ሌላውን በመመልከት ወደ ተሳሳተ መንገድ ሊያመራ ይችላል።

ስለሆነም የዴሞክራሲ አንድ ዘውግ የሆነው የህግ የበላይነት በተገቢው ሁኔታ መረጋገጥ አለበት። የህግ የበላይነት ካልተረጋገጠ ዴሞክራሲው እውን ሊሆን አይችልም። ዴሞክራሲ ለሁሉም ዜጎች እኩል መብት የሚሰጥ ስለሆነ አንዱ በሌላው ላይ የበላይ ሆኖ ፍላጎቱን በሃይል እንዳያስፈፅም የህግ የበላይነት ሁሌም ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል።

የህግ የበላይነት መከበር ለሀገር ሰላምና መረጋጋት ብሎም ልማትን ለማሳለጥ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል። ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት የህግ የበላይነት ከሌለ ሰላም የሚባልን ነገር ማሰብ አይቻልም። ሰላም ከጠፋ ደግሞ ስለ ልማትና ዴሞክራሲ ማሰብ አይቻልም። ፀረ-ልማትዊነትና ፀረ-ዴሞክራሲያዊነት ቦታውን ይረከባሉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ እንደ እኛ ሰላምን፣ ልማትንና ዴሞክራሲን የህልውናው ጉዳይ ላደረገ ሀገር አሜኬላ እሾህ መሆኑ አያጠያይቅም።

እርግጥ ኢትዮጵያ የጀመረችው የዕድገትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ባህል ግንባታ ሂደት ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል፤ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነበት ምህዳርን መፍጠር የግድ ነው። ምክንያቱም ሀገራችን ፈጣን ልማትን ማምጣትና ከተመፅዋችነት መላቀቅ ብሎም ዴሞክራሲን መገንባት የሞት ሽረት ያህል የህልውና ጉዳይ አድርጋ ስለያዘችው ነው። ታዲያ ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን መከላከልና መቆጣጠር ያስችላት ዘንድ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ የግድ ይላታል።

የህግ የበላይነት ሲኖር ሁላችንም ከሚገኘው ሀገራዊ ጥቅም ተካፋዩች እንሆናለን። የህግ የበላይነት በህገ መንግስቱ ላይ የተረጋገጠ ብቻ ሳይሆን፤ ለአገራችን ጠቃሚነቱ ታምኖበት እንዲተገበር ምክንያት የሚሆን ነው። ህግና ስርዓትን የበላይ አድርጎ መመልከት ሰላምን፣ ልማትንና ዴሞክራሲን የሚያፀና ነው። ስለሆነም ኮማንድ ፖስቱ ህግና ሥርዓትን ለማስከበር በሚያደርጋቸው ጥረቶች ህብረተሰቡ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል።  

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy