Artcles

ተግዳራቶችን እንደ መስፈንጠሪያ!

By Admin

May 04, 2018

ተግዳራቶችን እንደ መስፈንጠሪያ!

ተስፋየ ለማ

በኢትዮጵያ የአዕድገት ግስጋሴ የማይታሰብ ነበር፡፡ ቅድመ 1983 ዓ/ም የነበረው የአገሪቱ አጠቃላይ ሁኔታ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመናሩና የአገሪቱ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ በመዝቀጡ ህዝቦች የዕለት ጉርስ ማግኘት የማይቻሉበት ሁኔታ ላይ ገብተው ነበር፡፡ አገሪቱም የቁልቁል ጉዞ ውስጥ ገብታ ነበር፡፡   ተከዚህ የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ለርሃብ ለእርዛት ለብስቁልና ለስደት መዳረግ ብቸኛ አማራጭ ነበር፡፡ያ ታሪክ ትውስታው ገና አልደበዘዘም፡፡

 

የደርግን  ውድቀትን ተከትሎ  ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መቋጫ ወደሌለው የእርስ በርስ ጦር ይማገዳሉ ኢትዮጵያም ትበታተናለች የሚለው የስነፖለቲካዊ ተንታኞች  ትንበያ ሚዛን የደፋበት ነበር፡፡ በጊዜው የነበረውን ዓለም አቀፋዊ አህጉራዊ ቀጠናዊና ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ ስለነበር ትንበያው መሰረት አልባ ነበር ማለት አይቻልም፡፡  በመሆኑም ትነበያውን ተከትሎ በርካቶች ስምምነታቸውን ይገልጡ ነበር፡፡

አፋኙን አገዛዝ ለመገርሰስ በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል  ለኢትዮጵያ ህዝቦች የአዲስ ዘመን ምዕራፍ ከፋች ብቻ ሳይሆን ለተከታይ ትግል አጋዥ ኃይል ያለው የብርታት ምንጭ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ወታደራዊ አገዛዙ የተገረሰሰበት ድልና እሱን ተከትሎ የታየው የልማት ተስፋ ለቀጣይ ብሩህ ተስፋ  አቅም የሰነቅንበት የብርታት ስንቅ አሁን ለደረስንበት ደረጃ አድርሶናል፡፡

ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር ነች። በአገሪቱ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕጋዊ እውቅና አግኝተው የተወከሉ የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቁጥር 75  መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ።  ይህ ትልቅ ሃብት ነው፡፡ ይህንን ሃብት አንድ ላይ አስተባብሮ የአገሪቱን ህዳሴ እውን ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ በመከተል ባለፉት 27 ዓመታት ቀላል የማይባል ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

85 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርና የሚተዳደር በመሆኑ ይህንን በሚገባ በመረዳት የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ ለመቀየር ግብርናው ላይ ኣተኩሮ መስራት በማሰፈለጉ መንግስት የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ለውጦችን ደረጃ በደረጃ እያስመዘገበ መጥቷል፡፡

 

በመሆኑም  ድህነትንና ኋላቀርነትን  ለመቅረፍ የተደረገው እልህ አስጨራሸ ትግል ፍሬ እያፈራ አሁን ያለንበት ሁኔታ በተስፋና በተግዳሮት መካከል ላይ ተደርሷል፡፡  የተመዘገቡት የልማት ተስፋዎች በሌሎች አዳዲስ ተግዳራቶች የተከበቡ የሚያጎመጁ ስኬቶች የተመዘገቡበትና ብቅ ብለዋል፡፡ እነዚህ የልማት ስኬቶች የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሳይቀሩ ምስክርነታቸውን እየሰጡበት  ይገኛል፡፡

በቅርቡ አይ ኤም ኤፍ ያወጣው ዘገባ ለዚህ  ዋቢ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት 8 ነጥብ 5 በመቶ ዕድገት እንደሚታስመዘግብ ትንበያውን ይፋ አድርጓል፡፡  

አገሪቱ አጋጥሟት የነበረው የሰላም ቀውስ ሳይበግራት አሁንም የንግድ እና የኢንቨስትመንት ማዕከል ሆና መቀጠሏና ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ ኢንቬስተሮች ወደ አገሪቱ እየገቡ ይገኛሉ፡፡ ይህ አገሪቱ እያስመዘገበች ያለው የኢኮኖሚ እድገት የገነባው  መሰረት ጠንካራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ እስካሁን በጽኑ መሰረት ላይ የገነባችውን የሰላም የዴሞክራሲና የልማት በማጠናከር ህዳሴዋን እውን ለማድረግ በሚስችል መንገድ ጎዞዋን ቀጥላለች፡፡

ባለፉት ጥቅት ዓመታት የተከሰተው ችግር በዘላቂነት የአገሪቱን ሰላም የሚያውክና ልማትዋን የሚያደናቅፍ ሳይሆን ጊዜያዊ ቀውስ በመሆኑ ቀውሱን በመፍታት  የህዝቡን አንድነት በማጠናከር ላለፉት ዓመታት የተከናወኑት ግዙፍ ስራዎች በማስቀጠል ለበለጠ ለውጥ በመስራት የተሰነቀው ተስፋ ዳር ለማድረስ እየተሰራ ይገኛል፡፡

አዲሱ አመራር በአሁኑ ወቅት እያደረገ ያለው ህዝቡን የማስተባበርና አንድነቱን የማጠናከር ተግባር በማጠናከር  የአገራችንን ፈጣን እድገት ማረጋገጥ እንደሚቻል አያጠራጥርም፡፡ የኢኮኖሚ እድገቱ ግለቱን ጨምሮ እየተጓዘ ባለበት በአሁኑ ወቅት  አንዳንድ ፈታኝ ነገሮች ተጋርጠው የነበሩና አሁንም በከፊል ያሉ ቢሆንም የአገሪቱ ኢኮኖሚ በ 8 ነጥብ 5 በመቶ እድገቱ እንደሚቀጥል የአይ ኤም ኤፍ ዘገባው ማሳየቱ አገሪቱ ጠንካራ መሰረት መገንባቷን ያረጋግጣል፡፡

 

ይህ ስኬት የተገኘው  ሁሉም ብሔሮች ሔረሰቦችና ሕዝቦች ድህነትን ታሪክ ለማድረግ  ቆርጠው በመነሳታቸውና ጠንክረው በመስራታቸው ነው፡፡ በተለይ በአንድ በኩል አገሪቱ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የከፋ ድርቅ አጋጥሟት ባለበት ሁኔታ እንደዚሁም በእነዚህ ዓመታት በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተከሰተው የሰላም መደፈረስና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢንቬስትመንት  ላይ ያሳደረው ጫና የአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ፈታኝ ቢሆኑም ቀደም ስል የተገነባው ልማት መሰረተ ጠንካራ በመሆኑ ነውጡን ተቋቁሞ ፈጣን እድገቱ እየቀጠለ ይገኛል፡፡

የአገሪቱ  የእድገት ግስጋሴ  ያሰጋቸው አንዳንድ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ይህንን እድገት  ለመግታት የህዝብን ስሜት ሊያነሳሱ ይችላሉ ያልዋቸውን ወቅታዊ ችግሮች እያነፈነፉ በመፈለግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የእድገት ግስጋሴውን ይገታሉ ያልዋቸውን አማራጮች ሁሉ ከመተግበር አልተቆጠቡም ውጤት ያስገኛል ያሉትን    ማንኛውንም አይነት ሴራ ከመሸረብም አልተቀጠቡም፡፡ ለዚህ እኩይ ተግባራቸው እንቅልፍ አጥተው ሌት ተቀን ሲደክሙ ይስተዋላል፡፡

የአገራችንን ልማት ለማደናቀፍና ሰላሟን ለማወክ አእንቅልፍ ያጡ ወገኖች ወቅታዊ ችግሮችን በማባባስ የተለያዩ ጥረቶች ማድረጋቸውን ቀጥለውበታል፡፡  በዚህ መልክ ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት ተፈጥሮ የነበረው ጡዘት ታልሞለት የነበረውን ዓላማ ከመምታቱ በፊት በመክሸፉ አሁንም ለሌላ መስፈንጠር መንገድ መክፈቱን ሙሁራን ይናገራሉ፡፡

መንግስት አሁን የተጀመረው የአንድነት የመደመርና የመተባበር መንፈስ አጠናክሮ በመሄድ ላይ በመሆኑ መላው የአገራችን ህዝቦች  ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎችን ሰንቀን የተጀመረው የእድገት የሰላምና የዴሞክራሲ ተስፋ የሚያጨልሙ የጠላቶች እንቅስቃሴዎችን በመግታት የአገራችን ህዳሴ እውን ለማድረግ መረባረብ ለመላው ህዝባችንና ለአገራችን ሉአላዊነት ታፍሮና ተከብሮ መዝለቅ የሚኖረው ፋይዳ በእጅጉ የጎላ ነው፡፡

ለማጠቃለል ያህል ሁሉም እንደሚያውቀው በ1983 ዓ/ም አገሪቱ መኔታ መንገድ ላይ በወደቀችበት ወቅት መንግስት ህዝቡን በማስተባበር ለሰላም ለልማትና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መስፈንጠሪያ ተጠቅሞበታል፡፡

 

ከዚያ በህዋላም የሻዕቢያ መንግስት ወረራ በፈጸመበትና እሱን ተከትሎ በመጣው አስከፊ ጦርነት ጋር ተያይዞ በአገሪቱ የነበሩ የመበስበስ አደጋዎችን በመለየትና የነበሩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ከህዝብ ጋር በማስተዋወቅ ከመከፋፈልና ከመበተን ወደ አንድ አስተሳሰብ በመምጣት የተጀመረው ልማት የበለጠ ለማጠናከር መወንጨፊያ ሆኖ አገልግሏል ማለት ይቻላል፡፡  

በተመሳሳይ መልኩ በ1997 ዓ/ም ከልማት በተፈለገው መልክ አለመሄድ ጋር ተያይዞ በህዝብ የተነሳው ድምጼን አልሰጥም ጥያቄ በተከታይ ዓመታት ሁኔታዎችን በማስተካከል ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት የመጣውን ሁለንተናዊ ልማት እውን ለማድረግ አግዟል፡፡ አሁን እያጋጠመ የነበረው የሰላም መደፍረስ ጉዳይም መቋጫ እያገኘ የመጣ ይመስላል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተጋረጡ ተግዳራቶች  በስኬቶች የታጀቡ በመሆናቸው እንደሁሌ አሁንም ተግዳራቶቻችን ለመስፈንጠሪያ እንደሚናውላቸው አያጠያይቅም፡፡