Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ እርቀ -ሠላም አስፈላጊነት ዳሰሳ ።

0 1,293

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ እርቀ -ሠላም አስፈላጊነት ዳሰሳ ።

አዘጋጅ:  ልኡል ገብረመድህን (ከአገረ-አሜሪካ)።
ወረሃ ሰኔ 2018፣
ግላዊ እይታ ፣
1.  ያለፈው ሲቃኝ፣

አንድ አገር ሁለንተናዉ መረጋጋት እና እድገት እንዲኖራት ከሚያስፈልጉ ውጫዊ ምክንያቶች አንዱ የአሳኝ አገሮች መረጋጋት እና ስላም ሁኔታ ነው። በተለይ በደም፣ በዘርና በሀይማኖት አንድ የሆኑ ህዝቦች ስላማቸው እንዲዘረግ በብዙ ምክንያቶች  አስፈላጊ አይደለም ። ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተለየ ውህደትና ግንኙነት ያላቸው ወንድማማችና እህተማማች ህዝቦች ናቸው። ለረጅም ዘመናት በክፉም በደጉም አብሮ የነበሩ የተዋለዱና የዘመዱና አብሮ ዘመናትን የዘለቁ ናቸው።

ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የሁለቱ ወንድምና እህት ህዝቦች ስላም መደፍረስ ተከትሎ አስፈላጊ ወደአልነበረው የደም አፍስስ ውጊያ በ1991 ዓ.ም ተገባ ። ይህ የሁለት ወንድምና እህት ህዝቦች ጦርነት በ1992 ዓ.ም በኢትዮጵያ ድል ፈፃሚነት ቢጠናቀቅም ቅሉ አሌ የማይባል የስው ህይወት እና ቁሳዊ ንብረት ቀጥፈዋል፣ አውድመዋል፣በርካታ ህዝብ አፈናቅለዋል። ይህ በተለምዶ የባድሜ ጦርነት በመባል የሚጠራው ጦርነት በብዞቻችን የሚፈለግና የተጠበቀ አልነበረም ።በተለይ ኢትዮጵያ የደርግ ስርዓት አስወግዳ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት ላይ ነበረች። በደቀቀና በወደቀ ኢኮኖሚ ተመስርቶ ዳግም የጦርነት አውድ መግባት በእጅጉ ፈታኝ ነበር ። በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሩ በቀነስበትና ወደ ልማት ባስማራበት ወቅት መኖሩ ደግሞ ሁኔታው እጅግ አስቸጋሪ አድርጎት ነበር። በተቃራኒው የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት በማድረግ በባድሜ፣በፅሮና፣ እንዲሁም በዛላንበስ ቦታዎች የሀይል ወረራ ፈፀመ ።ለወረራው የተሰጠ በቂና አሳማኝ ምክንያት እስከዛሬ አልተገለፀም። የሁለቱም አገር ህዝቦች ለጦርነቱ መጀመር መነሻ የሚያውቁት በቂና አሳማኝ ምክንያት አልነበረም።ነበረ ከተባለም የኤርትራ መንግስት ታንኮች በባድሜ መታየታቸው ነበር። የህዝቡ ጥያቄ ለምን ተወረርን ሳይሆን ለምን ድንበራችን አስቀድመን መከላከል አልቻልንም ነበር።የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው አሳማን ምክንያት አልነበረም ። ህቡዕና የተድበስበስ ጉዳይ ነበር።

የድንበር ግጭቱ የሁለቱም አገር መሪዎች ቅራኔ እንጂ የሁለቱም ህዝቦች ቅራኔ አልነበረም። ምክንያቱም ህዝብ መሪው ይስይማል እንጂ መሪ አይሆንም።ኤርትራውያን ከውንድምና እህት የኢትዮጵያ ህዝብ ሲለዩ የሁለቱ አገር መሪዎች ውሳኔ እንጁ የኢትዮጵያ ህዝብ አልመከረም፣ አልተነጋገረም፣አልወስነምም። ህዝብ የማወቅና የመወስን መብቱ ገዡዎቹ ነፈጉት።የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ክፍለ ሀገር ይኖሩ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን የኤርትራ መንግስት ግፍና የንብረት ፣የፍይናስ ዝርፊያ ሲፈፅምባቸው ያደረገው ጥረት አልነበረም።ከነበረም ከአሳፍሪነት አያልፍም። It was shamefully. በተለይ የኤርትራ መንግስት መሪና መርህ አልባ ምክንያቶች የተለየ ገፅታ ነበራቸው ። አጉል ጀብደኝነት፣ስግብግብነት ፣ እና ትምክህት የተላበስ አመራር ከኤርትራ ጎልቶ በመፈንዳቱ  የኢትዮጵያ መንግስት ተገዶ ወደ ጦርነት ግንባር ዘመመ ። የኤርትራ መንግስት ድፍረትና እብሪት ተላብሶ የኢትዮጵያ መሬትና ግዛት ወረረ።የትግራይ ህዝብና ተራ ምልሻ ከፍተኛ መስዋዕትነት በመገበር ግዜያዊ የመከላከል እርምጃዎች በልበ ምሉዕነት ፈፅመዋል። ወረራውም  ከባድሜ እንዳይዘልቅ አግደዋል። ለዚህ አኩሪ ተጋድሎ የትግራይ ህዝብ ታላቅ ምስጋይ ይድረስው ። ዳር ድንበሩ በመጠበቅ በታሪክ ግንባር ቀደም ህዝብም ነው።

የሁለቱም ህዝቦች ስላም ዕጦትና ጉዳት ግንባር ቀደም ተወቃሾችና ተጠያቂዎቹ የሁለቱም አገር አመራሮችና መሪዎች ናቸው።የኢትዮጵያ መንግስት አገርና ህዝብ መጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ሆኖ ሳለ አስቀድሞ ለመከላከል ያደረገው እርምጃም ሆነ ጥረት አልነበረም ።የመከላከያ ሀይል በተግባር አልነበረም ።ለዚህም ጉዳዩ በወቅቱ የነበሩ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተርና ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። ታሪክም ይወቅሳቸዋል። መንግስታዊ ስህተት ብዙ ዋጋ አስከፍለዋል። ከድንበር ወረራ በፊትም ሆነ ኃላ የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ስህተቶች ነበሩት። የግልፅነት ጉዳይ አንዱ ችግር ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ለህዝቡ በደንበሩ ጉዳይ ላይ ግልፅ አልነበረም። ቀጥሎም የአልጀርሱ ስምምነት መጪውን ሁኔታ ያላገናዘበ፣የኢትዮጵያ ጥቅም ከግምት ያላስገባ ስምምነት ፈረመ ፣ ዳግመኛ ስህተትም ፈፀመ ። የአገር ክብርና ግዛትም አደጋ ላይ ወደቀ።የሁለቱም ህዝቦች ሁሉም አቀፍ ግኑኝነትም ተጎዳ፣ ቆመ።የኢትዮጵያ መንግስት የፈፀመው አገራዊ ስህተት ስልጣን ይዞ እንዲዘልቅ የሚፈቅድለት አልነበረም። የኢትዮጵያ ህዝብ ተጎድተዋል፣ተበድለዋል፣ ድንበሩና የባህር በሩም አጥተዋል።በተለይ ደግሞ የኤርትራ ህዝብ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ  ከባድ የመስደድ አደጋ አጋጠመው።  የተባበሩት መንግስታት በኤርትራ መንግስት ላይ ማዕቀብ ቢጣልም የተጎዳ ህዝቡ እንጂ መንግስት አልነበረም ።የትግራይ ህዝብም ቢሆን ከኤርትራ ጋር የስላም አልባ ሰለባ ሆነዋል። በአልጀርሱ (በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ December 12, 2000 የተፈረመና የፀደቀ) ስምምነት  መሠረትና መነሻነት ሁለቱም አገሮች ጦርነትና ስላም አልባ ሆኖ ለ18 ለዓመታት ቆይተዋል። ይህ ያልበስለና ኃላ ቀር አስተሳሰብ የኢትዮጵያ  መንግስት የቀየስው መርህ ነበር።ዓላማው  ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅ አልነበረም። የኤርትራ ኢኮኖሚ ለማቀጨጭ ከነበር ዓላማው ምን ነበራትና ምን ታጣለች።ቀያሹም አፍራሹም መንግስት ነበር። የኤርትራ መንግስትም የዚህ መርህ አልባ ስምምነት  ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ አልሆነም። አልፎ ተርፎም የለየለት የሽበራ ተግባር መረብ በኢትዮጵያ ላይ ዘረጋ ። በመረጃ የተከሽኑ ተደጋጋሚ የሽብር ፈተናዎች በኢትዮጵያ ላይ አደረሰ ። ለኢትዮጽያ መንግስትና ህዝብ መረጋጋት እንቅፋት ሆነ። ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ቅራኔ ያላቸው ኢትዮጵያኖች  ማዋለል ችለዋል። የቦታና የትጥቅ ክለላም ሠጥተዋል። በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ህውከት(unrest) እንዲሁም አለመረጋጋት ከፈተኛ የፋይናንስ ና ተዛማጅ እገዛዎች ከአረብ አገራት ተቀብለዋል ። ተጠቅሞበታል። ውጤታማም ሆነዋል። ኢትዮጵያ ሁለት ግዜ አስቸኳይ አዋጅ እፅድቃለች።ሁኔታው አሳፋሪም ፣ አዋራጅም ነበር።ሁለቱም የአስቸኳይ አዋጆች ሲታወጁ የደረሰ የሽብር ጥቃት አልነበረም ። መነሻውና መድረሻው ምክንያት የመንግስት ለለውጥ ፍላጎት መንፈግና የለውጥ ሀሳብ (progressive thinking) በር መዝጋት ፣የመንግስት ሀላፊዎች የተደራጀ ስርቆት(collective corruption) ፣እንዲሁም ኢፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ግፍአዊ እሥራት፣የመንግስት ካድሬዎች አፈናና ሽበራ ፣ የሥራ አጥ መበራከት ፣ የተደራጀ የመሬት ዝርፊያ( Collective Land Grapping) በዋናነት ተጠቃሽ ምክንያቶች ነበሩ።

2. የወቅቱ ቅኝት፣

ኢትዮጵያ በአሁኑ ግዜ አገርና ህዝብ አስተዳዳሪ መሪ ስይማለች። ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ናቸው። እኝህ መሪ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተዳደር የአደራ ቃል በፊርማቸው ካፀደቁ 70 ቀናት ተቆጥረዋል ። የስልጣን መቀበያ ንግግርም( Acceptance Speech)  አድርገዋል።እኝህ መሪ ከዚህ ቀደም ባልተለመደዉ ሁኔታ ከፍተኛ የህዝቦች የድጋፍ ድምፆች አግኝተዋል ።  ብስለት የተላበሱ በርካታ ተግባራትም በ60 የስልጣናቸው ቀናት  ለመተግበር  ችለዋል። በኢትዮጵያውያን ታሪክ ያልታዩና ያልተለመዱ ታሪካዊ ክንዋኔዎች ከውነዋል።አገር ዘለል ተግባራትም ፈፅመዋል። በባዕድ አገር የታሰሩት ኢትዮጵያውያኖች ከእስር አስለቅቀዋል፣ በአገር ውስጥ ታስሮ የነበሩት እስረኞችም ፈተዋል ። አገራዊ መግባባትም ፈቅደዋል። የኢትዮጵያ ደህነነትና ጥቅም ለማስጠበቅም ጉዞ ጀምረዋል። በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሰላምና የእንስባስብ ጥሪ አስተላልፈዋል ።የህዝብ ድምፅ ለማዳመጥ ፍቃደኛ ሆነዋል፣ የዲሞክራሲ መንገድ በር ለመክፈት ቁልፍ ከህዝቡ ተረክበዋል።የሚያቆማቸው ሀይል ያለ አይመስልም። ታሪክ ሰርቶ ፣ ህዝብ አስደስቶ በህዝቡ ፍቃድ ስልጣን ይለቃሉ።

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ በሳል፣ አስተውሎ መስደር የሚያውቁ ፣መፈፀም፣ ማስፈፅም አቅም የተላበሱ፣ በኢትዮጵያውያን የተከበሩና የተወደዱ ታላቅ መሪ ናቸው።  የአጭር ግዜ የስራ ውጤታቸውም(Job performance)  ከተጠበቀው በላይ ነው። በተለይ የአገሪቷን ስላም ለማስፈን የተስሩ መልካም ጅምሮች ውጤታማ ናቸዉ ። የፓለቲካ ምህዳር ለማስፋትና ለመወያየት ቁርጠኙነቱን አሳይተዋል ።የተደራጀ የሙስና ተግባር ላይ ለመዝመትም መንገድ ቀይስዋል። ኢትዮጵያ  ከአዋሳኝ ጎረቤት አገራት ጋር ያላት ሁሉም አቀፍ ግንኙነት ዕቅድ ነድፈዋል። ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማስፈን በህግ የላይነት እንደሚመሩ ነግሮናል። የኢትዮጵያዊ ዜጋ በሀሳብ ልዩነት እንደማይታስርና እንደማይስደድ አስረግጦ አብስረዋል። ይልቁንም የሀሳብ ልዩነት ለአገር ዕድገት ያለው አበርክቶ ተንትኖልናል። ህዝብም ሰምተዋል።ለተፈፃሚነቱ የቅርብ ክትትልም ያደርጋል።

ኢትዮጵያ አሁን ታይቶና ተስምቶ የማይታወቅ አስደሳች ምዕራፍ ላይ ነች። የህዝብ መሪ ተሰይመዋል ።ባልተለመዱ አዲዲስ የሀሳብ መርሆች ህዝቡ በመንግስት መዝገበ ቃላት አገላለጽ መሠረት በቀን ሶስቴ ከመመገብ በላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተስፋዎች በማጣጣም ላይ ነው። መንግስት ለውጥ ለውጥ መሽተት ጀምረዋል።የህዝቡን ሰብአዊ መብት አክብሮ በአክብሮት ህግን መሠረት አድርጎ ሰብአዊ መብት ያከብራል፣ ያስከብራልም።  ውንድምና እህት ከሆነው የኤርትራ ህዝብ በሰላምና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መስረት ትስስርና ግንኙነት እንዲኖር በብዙ ምክንያቶች አስፈላጊነቱ በእጅጉ የላቀ ነው።ሚኒስትሩም አምኖበታል።ከምክንያቶቹ አንዱና ግንባር ቀደሙ የሁለቱም አገር ህዝብ በህብለ-ሰረሰር የተሳሰረ ህዝብ ነው።ከደምና ከዘር ትስስር በላይ ህዝብ የሚያቀራርብ የለም። ሌላው ማቀራረብያ መንገድ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ነው። ኤርትራ ባህር አላት ግን ያላት ህዝብ ቁጥር አነስተኛ ነው።በኢትዮጵያ ህዝብ ቀመር ቢስላ ከአንድ ፐርስንት በታች(<1%) ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ ሰፊ የገበያ ምርት ተጠቃሚነት (Consumer Market) እና ሠፊ ቁጥር ያለው ህዝብ አላት።ሁለቱም ተመጣጣኝና  ተመጋጋቢ የጥቅም ግንኙነት አላቸው። ህዝብ የአንድ አገር ትልቅ ሀብት ነው።አሁን ላይ የህዝብ ቁጥር አብላጫ ያለቸው ታላላቅ የአለም አገሮች የተሻለ የኢኮኖሚና የፓለቲካ እድገት ላይ ደርስዋል። ይህውም የህዝባቸው ደህንነትና ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርገው ዕቅድና ፓሊሲ ነድፎ በተግባር በመተግበራቸው እንዲሁም የተበታተነ ህዝባቸው መሰብሰብ በመቻላቸውና በማክበራቸው ነው።ድህነት ለመቀነስ የህዝቦች አንድነትና እኩልነት ወሳኝነት አላቸው ።ያበረ ህዝብ አይራብም፣ ክብሩ አይናጋም፣አይደፈርም።

የኢትዮጵያ መንግስት በዲስንበር 12, 2000 (12, December 2000) በአልጀርያ ሸምጋይነት የተፈረመው የአልጀርስ ስምምነት በመሉ ተቀብያለሁ በማለት በ ጁን 5, 2018 (June 5, 2018) መግለጫ አውጥተዋል ። ይህም ለሰላምና መልካም ጉርብትና ያለው መልካም ፍላጎት ያማላክታል።የስምምነቱ ጉዳይ ቀድሞም አልቆ ደቆ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ምክር ቤት እና በአፍሪካ ህብረት እውቅና ተችሮት ተበክቶ የበሰለ ጉዳይ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅ አለማድረጉ የሞራል ውድቀትም ፣ ክደትም ነው። ስለ አልጀርስ ስምምነት እና ውሳኔ በግላጩ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተነገረው ግን ሁሉም የሚያስታውሰው ጉዳይ ነው። ውስልትና እና ቅጥፈት አዘል የእንካን ደስ አላችሁ መግለጫ ከመንግስት መስማት እንዴት ይዘገንናል። ህዝብ የሚመራ መንግስት እውነት ካልተናገረ ማን እውነት ይናገር።? እውነት ጠያቂ እና መንግስት  የሚያሽመደምድ ማህበረሰብ እስከአልተፈጠረ ደረስ  መንግስት መቅጠፉና  መዋሽቱን ይቀጥልበታል። ይህ ቅጥፈት በሰለጠነ ዓለም በስልጣን መባለግ(power corruption)  ይባላል። ውንጅልም ነው። መንግስት መከስስና ህዝባዊ ቅጣት ተቀጥቶ መወገድ ነበረበት።

አሁን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች ያላቸው የመራራቅ ዕድል ወሰንነት አለው። ለሁለቱም አገሮችና ህዝቦች የቀይ ባህር ቀጠናዊ ቀውስ እንዲሁም ቀጠናዊ የሀይል ቁጥጥሩ በአጭርም ሆነ በረጅም ግዜ የሁለቱም አገር አገራዊና አህጉራዊ ጥቅም ገመድ ላይ እንደተንጠለጠለ ስጋ ይሆናል።
የኤርትራ ስላም መደፍረስ ለኢትዮጵያ የአደጋዎች ሁሉ አደጋ ነው። የኢትዮጵያ ስላም መደፍረስ ግን ለኤርትራ አደጋ አይደለም። ምክንያት ከተጠየቀ ደግሞ ኤርትራ በተጋላጭ የቀይ ባህር ቀጠናዊ ክልል በቅርብ ርቀት ላይ ነች። በቀላሉ የቀጠናው ሀይል ሚዛን ተወዳዳሪ አገሮች  የመጠቃት አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል ። ከዛም ኤርትራን የማዳን ቀትራዊ ስራ የኢትዮጵያ ይሆናል። በጥልቀት መጪውን አደጋ መገንዘብ ከቻልን የባድሜ ጉዳይ የሚያስጨንቅ ትልቅ ጉዳይ አድርጌ አላየውም፣ አልወስደውምም። የሚያስፈልገው የመንግስት ግልፅነት ብቻ ይሆናል።ህዝብ ያማከለ ስራ መከሸን ይኖርበታል ። አስቸጋሪ ውሳኔዎች ላይ ህዝብ መሳተፍና መወሰን አለበት። ለመጪው ትውልድ የሚጠቅሙ አገራዊና አህጉራዊ  ፓሊሲዎች (Strategic policies) ላይ ትኩረት ማድረግ ይበጃል።የአሁኑ ግዜ ለኢትዮጵያ የተወሳሰበ ወቅት ነው። ጥበብና ብስለት የሚጠይቁ በረካታ ጉዳዮች አሉ። አንዳንዶቹ ከፍተኛ አደጋ አዘል ናቸው። ጥሩ የመንግስት አመራር ይፈልጋሉ። ህዝብ እንዳይጎዳ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። በተለይ ችግር ባላባቸው የሴሜኑ አዋሳኝ ቦታዎች ህዝቡ ለአደጋ እንዳይጋለጥ ጥንቃቄ ያሻል።

3. መፃኢ ቅኝት፣

ኢትዮጵያ የብርሃን መንገድ ለማየት በቅርብ ርቀት ላይ ነች። የብርሃን መንግዱ ደርሶ ለማየት ግን ዛሬ የምንሰራው መልካም ስራ ላይ የተመሰረተ ነው። ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ በቅንነት ፣ በአርቆ አሳቢነት፣ በመልካም ስነምግባር የአዲሱን ጠቅላላ ሚኒስተር የለውጥ ጎደና ውስጥ መግባት ይኖርበታል። የኢትዮጵያ ህዝቦች አንድነት ከምንም ግዜ በላይ አሁን ያስፈልጋል። ሰዎች በአመለካከታቸው የማይታስሩባት አገር መገንባት የሁሉም ድጋፍ ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ሰው ሲፈታ እንጂ ሲታስር የማይታወቅበት አገር ነች። መታስር ለሌቦች፣ ለአጭበርባሪዎች፣ ለህገ ገምዳዮች።የበደለ እያለ ያልበደለ ማስር መቀጠል የለበትም። የሐሳብ ልዩነት ማስተናገድ የሚችል አገርና መሪ መገንባት አለበት። የመንግስት ካድሬዎች ህግና ስርአት መከተልና ማክበር ይኖርባቸዋል። አማራጭ ሀሳብ ያላቸው የፓለቲካ ሰዎች በነፃነት መንቀሳቀስ አለባቸው ። የግለሰብ መብት መከበር ይኖርበታል። የኢትዮጵያ መንግስት የለውጥ ሀወርያ መሆን ይጠበቅበታል።ለለውጥ መታገል እንጂ ለውጥ እንደስጋት መመልከት የለበትም።የአንድ አገር ዕድገት በእውቀት ላይ የተንጠለንጠለ ነው። ድርጊቶች፣ ውሳኔዎች፣ አፈፃፅሞች በእውቀት ላይ መመስረት ይኖርባቸዋል። ማህበረስቡ ምክንያታዊ ውሳኔዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይኖርበታል። የህዝቡ ስሜታዊ ናዳዎች ህዝቡ ራሱ ማጤን አለበት። የዘር ልዩነት ማክበር እንጂ የግጭት መነሻ መሆን የለበትም።በዘር የተከፋፈለ አገር የለም። የኢትዮጽያ ብሔር ብሔረስቦች የኢትዮጵያ ጌጦችና ንጥር ሀብቶች ናቸው።

4.  መዝጊያዊ ቅኝት፣

1. የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች ግንኙነት የሁለቱም አገር ህዝቦች ዝምድና  እንዲሁም ጥቅም ተኮር ህዝባዊ  ተሳትፎ መሠረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል ።
2. ከኤርትራ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ፍይናንስና ቁሳዊ ንብረቶች የኤርትራ መንግስት ከውርስ ነፃ ማደረግና ለባለንብረቶች መመለስ ይኖርበታል።
3. የአልጀርስ ስምምነት ተፈፃሚነት እንዲኖረው ውሳኔ ባረፈባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ድምፅ መስማት ይኖርበታል ።
4. ኢትዮጵያ የውስጥ ስላሟን አሁን በያዘቹ መንገድ መቀጠል አለባት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy