Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የፖለቲካ ምህዳሩ…

0 350

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የፖለቲካ ምህዳሩ…

                                                        ሶሪ ገመዳ

በአሁኑ ሰዓት የፓርቲዎች እየተወያዩ ነው። የውይይታቸው አጀንዳ የፖለቲካ ምህዳሩን በሚያሰፉ በማንኛውም ጉዳዩች ላይ የሚያጠነጥን ነው። በአሁኑ ሰዓት 15 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፀረ ሽብር ህጉ እንዲሁም በብሄራዊ መግባባት ላይ እየተወያዩ ይገኛሉ። ቀደም ሲልም ከውይይቱ ወጥቶ የነበረው መድረክ ከኢህአዴግ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል። ይህም ምህዳሩን ከማስፋት አኳያ የመጣ ለውጥ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ገዥው ፓርቲ ከውጭ ከመጡ የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ጭምር ያለ ምንም ገደብ ውይይቶችን እያካሄደ ነው። ይህም የአገራችንን የፖለቲካ ምህዳር የትኛውንም ዓይነት ሃሳብ በማስተናገድ እየሰፋ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ “ለትግል ውጪ መዞር አያስፈልገንም” ያሉትም ይህን በመስፋት ላይ የሚገኘውን የፖለቲካ ምህዳር ስለተመለከቱ ይመስለኛል።

መንግስት እዚህ ሀገር ውስጥ የዴሞክራሲውን ምህዳር ይበልጥ በማስፋት የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ አሁን ካለው በላይ እንዲጎለብት ያላቸውን ፍላጎት የሚያረጋግጥ ነው። ሆኖም ገዥው ፓርቲም ይሁን ተፎካካሪዎች ድርድራቸው አገራዊ ዓላማን የህዝብን መብት ያከበረ መሆን አለበት።

ይሁንና የፖለቲካ ፓርቲዎች የድርድር መድረክ የሀገራችንን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያጎለብትና የፖለቲካ ምህዳሩን ይበልጥ የሚያሰፋ ነው። ድርድሩ እዚህ ሀገር ውስጥ በመገንባት ላይ ያለውን የዴሞክራሲ ስርዓት እንዲሁም የሁሉንም ህዝቦች ውክልና የሚያጠናክር ነው። ስለሆነም ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍተቶችን የማጥበብና በሚያግባቡ ጉዳዩች ላይ ለአገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል አንድ ላይ መስራት ያስፈልጋል።

በአሁኑ ወቅት በመደራደር ላይ የሚገኙት 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ዓላማዎቻቸው ዴሞክራሲን በማስፋት ለመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ መጎልበት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ነው።   በመሆኑም በቀጣይ ድርድሮች ወቅት ሁሉም ወገኖች ማሰብ ያለባቸው የሀገራችን ዴሞክራሲ በበለጠ ሁኔታ እንዴት መስፋት እንዳለበት ነው።

እንደ ኢትዮጵያ ያሉና ባለፉት ፊውዳላዊና አምባገነናዊ ስርዓቶች በህዝቦች መካከል ፈጥረውት ያለፉት ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦች በቀላሉ የሚሽሩ አይደሉም። ፀረ ዴሞክራሲያዊ እሳቤዎችን በዴሞክራሲያዊነት ለመቀየርም አስተሳሰብንና ተግባርን በአዲስ መልክ ማዋሃድ ይጠይቃል።

ታዲያ እዚህ ላይ በህዝቦች ውስጥ ለዘመናት ሲፈጠሩ የነበሩትን የተዛቡ ግንኙነቶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ ማስተካከል እንደማይቻል መገንዘብ ያስፈልጋል። ሆኖም መንግስት በተቻለ መጠን የፖለቲካ ምህዳሩን በማስፋት ሁሉም ሃሳቦች እንዲንሸራሸሩ እያደረገ ነው።

ሁሉም ፓርቲዎቹ በክርክሩና በድርድሩ ሂደት ውስጥ ‘እነዚህን የዴሞክራሲ ተግዳሮቶች ለመፍታት ከእኔ ምን ይጠበቃል?’ ብለው ራሳቸውን መጠየቅ የሚገባቸው ይመስለኛል። በዚህም ለአገራቸው ዴሞክራሲ የበለጠ መስፋት የበኩላቸውን ሚና ይጫወታሉ።

ፓርቲዎቹ ሌላው ሊያነሱት የሚገባው ጉዳይ ድርድሩ በአሁን ወቅት የተገኘውን ሰላም ይበልጥ ለማጠናከር አኳያ ሊኖረው ስለሚገባው ፋይዳ ነው። እንደሚታወቀው ሁሉ የዛሬ ሶስት ዓመት ገደማ በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ሁከት ተፈጥሮ ነበር።

የሁከቱ አነሳሽ ምክንያት ምንም ይሁን ምን፤ ፓርቲዎች እንዲያ ያለው ሁከት ዳግም እንዳይፈጠር ሲባል በሰፋው ምህር ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸው መስራት።

እርግጥ ማንኛውም ዴሞክራሲያዊ ድርድር መቋጫው ጥርጣሬንና ግጭትን በማስወገድ ሰላምን ማምጣት ነው። ሰላም ካለ ሁሉም ነገር አለ። ያለ ሰላም ልማትን ማሰብ አይቻልም። ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱንም ስር እንዲሰድ ማሰብ ትርጉም አይኖረውም።

ዴሞክራሲ ስር ባልሰደደበት ሀገር ውስጥ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ልባቸው ሃሳባቸውን ለህዝባቸው ሊያስተዋውቁና በህዝቡ ይሁንታ በሚካሄድ ምርጫ አገር ሊመሩ አይችሉም። በመሆኑም አዋጆችን ይሁን ህጎችን ለመቀየር ሲደራደሩ የሰላማችን ሁኔታ ይበልጥ የሚጠናከርበትን መንገድ ማሰብ ይኖርባቸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ልማትንም ይሁን ዴሞክራሲን ለማሳለጥ የሚከናወኑ ማናቸውም ሁነቶች ማንንም ለማስደሰት አሊያም ለማስከፋት ሳይሆን፤ የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የታገሉላቸውን መብቶች በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም ታስቦ ነው።

በመሆኑም በገዥው ፓርቲም ይሁን በተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የሚከናወኑ ጉዳዩች ለሀገርና ለህዝብ ጠቀሜታ ሲባል እንጂ፣ ለታይታ አሊያም ለሌላ ጉዳይ የሚከናወኑ አይደሉም፤ ሊሆኑም አይችሉም። ስለሆነም እንዲህ ዓይነቱ ደዴሞክራሲን የማስለጥ ተግባር የዴሞክራሲ መለያ ስለሆነ ነው።

ዴሞክራሲን ከማስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው ከማድረግ አኳያ ይህ በገዥው ፓርቲ አማካኝነት የተጠራው የድርድር መድረክ ሊመሰገን የሚገባው ተግባር ነው። እንዲህ ዓይነት መድረኮች በበዙና በተበራከቱ ቁጥር የሀገራችን ዴሞክራሲ ይበልጥ አሳታፊ፣ ግልፅነት የተሞላበትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በበቂ ሁኔታ ሊያሳትፍ የሚችል ይሆናል። እናም በገዥው ፓርቲና በተቃዋሚዎች መካከል የሚካሄደው ክርክርና ድርድር ከዚህ ዴሞክራሲያዊ አውድ ብቻ መታየት ያለበት ይመስለኛል።

ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚደረገው ውይይትና ድርድር፤ ፓርቲዎቹ ከመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታው ጋር ተያይዞ መንግስት ያለበትን ችግሮች ነቅሶ በማውጣት ህፀፆቹን በግልፅ እንዲያይ ያደርጉታል።

መንግስትም አግባብና ትክክለኛነት ያላቸውን አስተያየቶች በመቀበል ለስራው እንደ አንድ ድጋፍ እንዲጠቀምባቸው የመነሻ ሃሳቦች ሊሆኑት ይችላሉ። ይህ ሁኔታም በአንድ በኩል ዴሞክራሲውን ለማስፋትና የህዝቦችን ተደማጭነት ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሰሚነት ድምፅ እንዲጨምር ዕድል ይሰጣል።

ዴሞክራሲን ከማስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው ከማድረግ አኳያ ይህ በገዥው ፓርቲ አማካኝነት የተጠራው የድርድር መድረክ ሊመሰገን የሚገባው ተግባር ነው። እንዲህ ዓይነት መድረኮች በበዙና በተበራከቱ ቁጥር የሀገራችን ዴሞክራሲ ይበልጥ አሳታፊ፣ ግልፅነት የተሞላበትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በበቂ ሁኔታ ሊያሳትፍ የሚችል ይሆናል።

እናም በገዥው ፓርቲና በተፎካካሪዎች መካከል የሚካሄደው ክርክርና ድርድር ከዚህ የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት አኳያ መታየት ይኖርበታል። በመሆኑም ሁሉም ለፖለቲካ ምህዳሩ መጎልበት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy