Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ያለፈው ስህተት እንዳይደገም።

0 633

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አዘጋጅ፣  ልኡል ገበረመድህን (ከአገረ-አሜሪካ)
ወረሐ ሰኔ 2018.
ግላዊ እይታ ፣
(1) መግቢያ ፣

በአንድ አገር በህዝብ የተሰየመ  የመንግስት አስተዳደር ይኖር ዘንድ የግድ ነው። የመንግስት ሐላፊነት ደግሞ የአገሩን ህገ- መንግስት መሠረት አድርጎ የአገሩን ጥቅም መቃኘት፣የህዝቡን ደህነት ማስጠበቅ ፣የአገር ለአላዊነት ማስከበር  ፣የዜጎች መብት ሳይሽራረፍ ማክበር፣ መሰረተ ልማቶች ማስፋፋት፣ የዜጎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቅሞች ማሳደግ ፣ የአገር ሀብት ብክነት መቆጣጠር እንዲሁም የስልጣን ብልሹነት ማስወገድ (check & balance) ፣ሁለንተናዊ አህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ  ግንኙነቶች ማጠናከር፣ የመንግስት ግልፅነትና ተጠያቂነት ማስፈን ፣ ለህግና ለህገ- መንግስቱ ተገዢ መሆን ከበርካታዎቹ ከፊሎቹ ናቸው። ከላይ በከፊል የተጠቀሱት የመንግስት ተግባሮች ለመከወን ሰብዕና እና ፍትሃዊነት መስረት ያደረገ መንግስት መሆን አለበት። በኢትዮጵያ የመንግስትነት ታሪክ የህዝብን አወንታ አግኝቶ፣ ህግን አክብሮ ፣ የዜጎች መበት ተቀብሎ፣ አክብሮ ፣አስከብሮ፣ የአገሩን ለአላዊነት አስጠብቆ ስልጣን ከህዝብ ወደ ህዝብ በስላማዊ ሁናቴ ያሽጋገረ መሪ ወይም መንግስት የለም ወይም የተለመደ አይደለም። ያለመሆኑ ደግሞ እጅግ ያስቆጫል፣ያሳዝናልም። መንግስት የህዝብ ልሳን የማይሆንበት አብይ ምክንያት ደግሞ ወደ መንበረ ስልጣን የሚወጣበት ሂደት ኢዲምክራስያዊ በመሆኑ ነው።ላለፉት ብዙ ዘመናት በኢትዮጵያ የመንግስትነት ስልጣን ይገኝ የነበረው  በግጭት አልያም በዘውዳዊ ውርርስ ነበር።በዚህ ሁኔታ አገርና ህዝብ ለማስተዳደር ስልጣን ያገኘ መሪ በምንም መስፈርት የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት አይችልም።ሰብዓዊ መብት አያከብርም።ብልሹ መንግስታዊ አሰራር ይስፍናል።የሀሳብ ልዩነት አያስተናግድም። ይልቁንም ለስልጣኑ ማስቀጠያ ይረዳ ዘንድ ለስርዓቱ ታማኝ የሆኑ ሰዎች ሞያን መሰረተ ያላደረገ  ስልጣን  ይስጣሉ ፣ ይሾማሉ፣ያወርዳሉ። ከግል ክብር ይልቅ የመንበረ ስልጣን ክብር ያገዝፋል ።ህግ ተላልፎ ህዝብ ከመበደል አልፎ አገርን አደጋ ላይ የሚዘፍቅ ተግባራት ይፈፅማል። በአንድ ወቅት ጅቡቲ የኢትዮጵያ መሬት ነበረች።በቂ መረጀ እንካን ባይኖር ቀደምት  መሪዎቻችን  ከህዝብ ፍላጎት ውጭ ጅቡቲ በክራይ መልክ በ1894 አከባቢ ለፈረንሳይ ተስጠች ።እስከ 1977 አጋማሽ ድረስ በፈረንሳይ ስር ነበረች።አሁን ላይ ሆነን ያለፈው ስናስታውስ በሁኔታዎች እንቆጫለን። የውጭ ንግዳችን ማሳለጫ ወደብ አልባ መሆናችን ደግሞ የበለጠ ያመናል።ዛሬ ላይ ሆነን መጪው መገንዘብ ፣መተንበይና መተንተን  ካልቻልን ጉዛችን የኋልዮሽ ይሆናል።

እኔ የምኖርበት አገር (አሜሪካ) የአምስት መቶ አመት ዕድሜ ያለው አገር ነው። ከእጅ አዙር አገዘዝ ነፃ ከወጣ ሶስት መቶ አመት እንኳን አላስቆጠረም።ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ግን የአለማችን ጫፍ ላይ ነው። ከ1605 እስክ 1770 ዎቹ ድረስ እንግሊዞች በቅኝ ያስተዳድሩት አገር ነበር።
የአሜሪካ አስራ ሶስት ቅኝ ግዛቶች(colonial States)  ጥምረት በመፍጠር እንግሊዝን በ1770 ዎቹ ከአገራቸው ጠራርጎ በማስወጣት በቀጥታ የግዛት ማስፋፋት እቅድ ነደፉ። በሃይልም ሆነ በግዢ ሰፋፊ ቦታዎች ያዙ ። አላማቸው ግልፅ ነበር።ይህውም ለመጪው ትውልድ ጥቅም ተኮር መደላድሎች ለማመቻቸት ነበር። ትላንት የሰሩት መልካም ስራ ዛሬ ጠቅሟቸዋል።ዛሬ የአለም ህዝብ መሰደጃ አገር ሆነዋል።ዛሬ አሜሪካ ከሶስት መቶ ሚልየን በላይ ህዝብ ያለው አገር ነው። በህጋዊ መዝገብ በየአመቱ በአማካይ እስከ ሀምሳ ሸህ የአለም ህዝብ ወደ አሜሪካ  ይተማል።ሰፊ ህዝብ የሚያኖር ሰፊ አገርና መሬት አላት። ህዝቡ ለአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ነው። የጦር መሳሪያ ሽያጭም ትልቁ የገቢ ምንጯ ነው። አሜሪካ ኃላ ተፈጥራ ግንባር ቀደም የበለፀገች ሀያል አገር ለመሆን ያበቃት አንዱ ምክንያት የህግ በላይነት ማስፈፀም የሚያስችል ተቋማዊ አቅሟ ነው። ማንም ሰው ርዕስ ብሄሩ ጭምር ከህግ በታች ነው። መንግስት ይከሳሳል፣ ይቀጣል፣ ከስልጣኑ ይወገዳል። ሌላው የዲሞክራሲ ባህል ማበልፀጔ እንዲሁም የግለሰብ መብት ማክበርና  ማስከበር መቻሏ ነው።

(2)  ** ኢትዮጵያ **

ኢትዮጵያ በአፈጣጠር እንዲሁም በስልጣኔ ከአሜሪካ በብዙ ዘመናት ትቀድማለች። ያለፈው አሁን ላይ ሆነን ስናየው የእድገታችን ፍጥነት ቁልቁል ነበር ማለት ነው።ሌላው ትተን አሁን ላይ ሆነንም ስለ ዘርና ብሄር እናወራለን፣ እንተቻለን፣ እንከፋፍላለን፣ እንስብካለን። የምናደርገው በስክነት ብናስተውለው  አሁንም እናሳዝናለን። ዘርና ብሄር እንደሀረግ እየመዘዝን እንዴት ሰላምና እድገት ይሳካልናል ? ። የዛ ጎሳ ስው ስልጣን ያዘ ብለን ስንናገር በራሱ ያሳፍራል። መነሻ ሀሳብና ትንታኔ ካለውም ስህተት ነው። የወደቀ አስተሳስብ ይዘን እንደ አገር መቀጠሉ ከምንም በላይ አስቸጋሪ ነው። የውስጥ አንድነትና ህብረት ከሌለን ስለ ለአላዊነትም ሆነ በአጠቃላይ ስለ አገር መፃኢ እድሎች መተንበይ አይቻልም ። የራሳችን የመለወጥና የመልማት እድል በሮች የመዝጋት እንጂ የመክፈት ባህላችን ደካማ ነው። አንደ አገር አንዱና ዋናው መነሻ ችግራችን  ጤናማ የፓለቲካ ስርአት ያለመኖር ነው። ሌላው ደግሞ የህዝባችን የፓለቲካ ተሳትፎ ማነስ ነው።መንግስት የሚቆጣጣሪና የሚጠይቅ ማህበረሰብ እና ህብረተሰብ ከሌለ መሪዎች ወደ አምባገነናዊ ባህሪ ይቀየራሉ። አሳሪና ቀፋዲ ህጎችና መመሪያዎች ያወጣሉ።ሰብአዊ መብቶች አያከብሩም። ሙስና ይስፋፋል።

ፓለቲካ ለአንድ አገር የሰላም፣ የልማት ፣ የአንድነት ፣ የመቻቻል፣ መገልገያ መሳሪያ ነው። ፓለቲካ የማይነካካው የህይወት መስመር የለም። የኢኮኖሚ እድገት ካለ የፓለቲካ እድገት መኖሩን ያመላክታል።በተቃወሰ ፓለቲካ ስላም የለም።የሰላም መረጋጋት የሌለው አገር ደግሞ ልማትና እድገት የለውም ። ልማትና እድገት ከሌለ ደግሞ ስራ አጥነትና ስደት መኖሩ የግድ ነው። የፓለቲካ መረጋጋት ለአንድ አገር የህልውና ጉዳይ ነው።የዜጎች የህልውና ጉዳዩ ነው።የፓለቲካ ቀውስ አገር ያፈርሳል። በፈረስ አገር ደግሞ ዜጋ አይኖርም ።በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የፓለቲካ መፍትሔ ያስፈልጋታል። የዜጎቿ መቀራረብ ትሻለች ። በዘርና በብሔር ህዝቧ እንዲከፋፈል አትሻም። በህብረትና አንድነት መንፈስ (spirit of unity) የአገር ልማት ለመተግበር የሚያዳግት የአቅም ውስንነት አይኖርም ።ህዝቦች የአንድነት መንፈስ እንዲያዳብሩ የማያወላዳ ቀጥተኛ የህገ-መንግስት ከለላና ዋስትና ይሻሉ። በየትኛውም የአገቷ  ክልል ሰርቶ ፣ሀብት አፍርቶ የመኖር መበት በማያሻማ ሁናቴ መረጋገጥ አለበት። ዘር ቆጠራ ሳይውል ሳያድር መቆም ይኖርበታል ። ከስፈለገም መጠየቅ  ያለበት ዘርና ብሄር  ሳይሆን ዜግነት ነው። ዘርና ብሔር የአንድ ግለስብ ወይም ህብረተስብ ምንነትና ማንነት ጉዳይ ነው። ምን ግዜም ቢሆን አብሮህ የሚኖር ስብዕና ነው። ማንነት የሚጠፋ፣የሚስረዝ፣የሚደለዝ አይደለም። አንድ ግለስብም ሆነ ህብረተስብ በማንነቱ መኩራት ይኖርበታል ።ለብሄር ብሄረሰቦች ዘርና ማንነት ክብር ካልስጠን አገር የሚባል ጉዳይ አይኖርም። ለምን ቢባል ብሄረሰቦች የአንድ አገር መተኪያ የሌላቸው ፀጋዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ ዘርና ብሄር መነሻ ያደረገ ፓለቲካ መቆም አለበት። የፓለቲካ ድርጅቶች አነሳሳቸው ዘርና ብሔር (Ethnic centered) መዕከል ያደረገ ነው። ይህ አይነቱ የፓለቲካ እንቅስቃሴ መዘዙ ብዙ ነው። በተግባር ተፈትኖም ውጤቱ አስደሳች አይደለም ። ኢትዮጵያ የተፋጠነ ልማት፣ስላምና የተሟላ ዲሞክራሲ እንዲኖራት ከተፈለገ  ብሄራዊ የፓለቲካ አደረጃጀት ያስፈልጋታል ። ለምሳሌ ፣ በአሁኑ ግዜ በኢትዮጵያ ያለው የፓለቲካ ስርአት ብሔር ተኮር በመሆኑ ለዲሞክራሲ ግንባታ ፣ ሰላምና መረጋጋት እንቅፋት ነው። የኢህአዴግ ስርአት ፈርሶም ቢሆን  ወደ ብሔራዊ ስርአት መቀየር አለበት።በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስርአት  ብዙ ርቀት መጔዝ የሚቻል አይመስለኝም ። አብዮታዊ ዲሞክራሲ አፋኝ ስርአት ነው። ከፊላዊ እንጂ የተሟላ ስርአት አይደለም ። በአብዮታዊ ዲሞክራሲ መነሻ ስነ ሀሳብ የዲሞክራሲ መርሆዎች በአግባቡ አይተገበሩም። የልማት እንቅስቃሴውም ቢሆን ለብልሹ አስራር የተጋለጠ ነው። በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስርአት  የህግ በላይነት ሳይሆን ግለስቦች ከህግ በላይ ናቸዉ ። በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስርአት ውስጥ ግለስቦች ህግ ይጥሳሉ፣ መብት ይደፈጥጣሉ፣ ያስራሉ፣ ይሞስናሉ።በአጠቃላይ በስራአቱ ስር ያሉ ግለስቦች፣ ባለሥልጣኖች የአምባገንነት ስርአት ባህሪዎች አሏቸው ።

(3) **  የኢትዮጵያ ህዝብ ወካዮች ምክር ቤት **
(   Ethiopian Parliament)

በኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ የስልጣን መቀመጫ ወንበር ያገኙ የህዝብ ውክልና የተቀበሉ ሰዎች ተግባራቸው ሆነ ቋንቋቸው ከስራ አስፈፃሚው (executive branch) የተለየ አይደለም ። ሌላ ቀርቶ ለተለያዩ መሰረተ ልማት የሚውሉ የውጭ ብድሮችና እገዛዎች ሲገኙ አይመረምሩም፣ አይጠይቁም፣ በግልፅነት ጉዳዮች ዙርያ በተገቢው መንገድ አይከራከሩም፣ አይሞጉቱም። No seen effective debates & Discussions on the floor of the Ethiopian Parliament on issues that matter to the Country.የህዝብ ተወካዮች ምንም እንኳን በአብላጫ  የኢህአዴግ ስርዓት ወክሎ መቀመጫ ያገኙ ቢሆኑም የህዝብ ወኪሎች ናቸው ። ውግንናቸው ለህዝብ መሆን ነበረበት።ህግ አውጪ እንደመሆናቸው ተፈፃሚነቱም መከታተል ነበረባቸው ። የወከሉትን ህዝብ ከኖረበት ሰፍራ ሲፈናቀል ማወገዝና ህዝቡ ፍትህ እንዲያገኝ ማድረግ ነበረባቸው ። የአገር ሀብት በመንግስት ሙስኞች ብክነት ሲደርስበት መቆጣጠርና ክትትል ማደረግ ነበረባቸው ። የለአላዊነት ጉዳይ ሥራ አስፈፃሚ ክፍል (መንግስት) ስህተት ሲፈፅም የአገሪቷ ፓርላማ ሥራ አስፈፅሚ ክፍል ማስቆም ነበረበት ። የአገር ለአላዊነት ጉዳይና ህገ- ውሳኔ የህዝብ ተወካዮች እንጂ የሥራ አስፈጻሚ ክፍል (Executive branch) አይደለም። አሁንም ሆነ ነገ የድንበር ነክ ውሳኔዎች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በውይይት ዳብሮ መፅደቅ ይኖርባቸዋል።
የፓርላማ እንደራሴዎች የአገርና የህዝብ ኅላፊነትና እምነት አለባቸው ።በመሆኑም ድምፅ ለመስጠት ብቻ ፓርላማ መቀመጥ የለባቸውም ።አብዛኛዎቹ የፓርላማ አባላት የአንድ ፓለቲካ ስርአት ወኪሎች ቢሆኑም የሀሳብ ልዩነት አንዳያደርጉ አጋጅ ህግ የለም። በህዝብ ሀብት ብክነት ላይ ከፍትኛ በቁጥጥርና ክትትል ማድረግ ብዙ ይቀራቸዋል።

(4)   **  የባድሜ ድንበር ጉዳይ **

ድንበር ነክ ጉዳዮች ውሳኔ የመስጠት ሐላፊነት የማን ነው?ምንም ባልጠበቀው ሁኔታ የአስብን ወደብ ለኢትዮጵያ አይጠቅም በማለት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ነበር ያለምንም ድርድር ለኤርትራ አስረካቧት። ረዘም ላለ ግዜ አንድ ላይ የነበር ህዝብ በምክንያት ሲለያዩ ግምት ውስጥ የሚገቡ ብዙ አገራዊ ጥቅሞች ይኖራሉ። ኤርትራ በምዕራውያን ዘመን ቀመር 1993 ከኢትዮጵያ ስትለይ ለኤርትራውያን ደስታ ለኢትዮጵያውያን ሀዘን ነበር። በ1991 የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር(EPLF) አስመራ ለመቆጣጠር ቻለ ። ቀጥሎም በኢትዮጵያ ሰፋ ያሉ ጣልቃ ገብ እንቅስቃሴዎች ጀመረ። ለምሳሌ ፣ የኢኮኖሚና ንግድ ጣልቃ ገብነት ፣ ህገ ውጥ የፋይናንስ ዝውውር፣ ወታደራዊ ስለላና ስውር ግድያዎች። ሜጀር ጄኔራል ሐየሎም አርአያ የተገደለው ጀማል ያሲን የተባለ የኤርትራ መንግስት ሰላይ ነበር። የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ጣልቃ ገብቶ ያሻው ሲፈፅም የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ መንግስት አሽከር (ከዳሚ) ነበር። ኤርትራ ባድሜ በሀይል ለኢትዮጵያውያን መነሻ ምክንያት ግልፅ አልነበረም። የኢትዮጵያ መንግስት የአልጀርስ ስምምነት ከመቀበሉ በፊት የባድሜ ችግር ለመፍታት ብዙ አጋጣሚዎች ነበሩት። ከስምምነቱ በኃላም በርካታ ጥሩ አጋጣሚዎች የኢትዮጵያ መንግስት ሳይጠቀምባቸው ቀርተዋል።ለምሳሌ ፣ ኤርትራ የኢትዮጵያ ደህንነትና ብሄራዊ ጥቅም ለመጉዳት አሽባሪዎች አስልጥና ወደ ኢትዮጵያ በስርጎ ገብ መልክ ተግባራዊ ሽበራዎች ፈፅማለች። ኢትዮጵያ የአገሯን ጥቅም ለማስጠበቅ ይህ የኤርትራ ሴራ ከበቂ በላይ ምክንያት ነበር። ተመጣጣኝ ሳይሆን ስር ነቀል እርምጃዎች መውሰድ ነበረባት። መንግስት በኤርትራ ላይ ስር ነቀል እርምጃ ለመውሰድ ፍቃደኝነቱ አልነበረውም.። የባድሜ እና ሌሎች አወዛጋቢ ቦታዎች ችግር ለመፍታት በአካባቢው የሚኖሩ የሁለቱም አገራት ህዝቦች ድምፀ ውሳኔ መከበር አለበት። የባድሜ ችግር ለመፍታት በህዝቦች ፍቃደኝነት እንዲሁም የመንግስት ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል።

(5) ** የኤርትራ መንግስት **

ከምንም ግዜ በበለጠ በአሁኑ ወቅት የኤርትራ መንግስት በባድሜ ጉዳይ ላይ አጣብቂኝ ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል ።በተግባር የድንበር ማካለል ስራ ሂደት ለመጀመር የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ የሚሆን አይመስለኝም ። የኤርትራ መንግስት ፍቃደኛ ያለመሆን ደግሞ ለኢትዮጵያ  ብሔራዊ ድህንነቷ ለማስከበር መልካም አጋጣሚ ይሆናል።
በቀጣይ ከኤርትራ መንግስት የሚስነዘሩ ትንኮሳዎች ኢትዮጵያ ተመጣጣኝ በሚል መርህ የምታልፋቸው አይመስለኝም ። ኢትዮጵያ ለአካባቢው ህዝብና ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ሲባል በኤርትራ መንግስት ላይ ከባድ እርምጃዎች ለመውሰድ ትገደዳለች። የአልጀርስ ስምምነት ተግባራዊነት ከሁሉም በላይ ለኤርትራ ህዝብ ጠቀሜታ አለው ።በመሆኑም የኤርትራ ህዝብ ከፍተኛ የሰላም ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅበታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy