Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ይቅርታው

0 312

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ይቅርታው…!

                                                         ሶሪ ገመዳ

መንግስት የህግ ታራሚዎችን በይቅርታና በምህረት ከእስር እየለቀቀ ነው። ይህም የዜጎችን መብት ለመጠበቅና የተጀመረውን አገራዊ መግባባት ይበልጥ ለማጠናከር ታስቦ የሚደረግ ይመስለኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ይቅርታን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ይቅርታ አድራጊው ህዝብ ነው ብለዋል። መንግስት በፀረ ሽብሩና በሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ኢ ህገ መንግስታዊ በመሆነ መንገድ ጨላ ቤት ሲያስቀምጥ፣ ሲገርፍና ሲያሰቃይ እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም ሳቢያ ኢህአዴግ በጠየቀው ይቅርታ መሰረት ህዝቡ ይቅርታን ማሳየቱን አስረድተዋል። ሌላው ቀርቶ የደርግ ባለስልጣናት መለቀቃቸውን ያሰታወሱት ዶክተር አብይ፤ መንግስትን ይቅር ያለ ህዝብ ለታራሚዎችም ይቅር ማለቱን ገልፀዋል።

ይህም ይቅርታ ገደብ ስለሌለው ነው።ይሁንና በይቅርታ የተለቀቁት ሁሉም ግለሰቦች በሙሉ ህግንና አሰራርን መሰረት ባደረገ ሁኔታ ነው። የህግ መዛነፍ የለውም። የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ የሰው ልጅ ሲለቀቅ መደሰትን እንጂ መከፋት እንደማይኖርበት ያምናል።

መንግስት በይቅርታው ማስረጃና መረጃ ያላገኘባቸውን፣ ነገር ግን አስሮ ያስቀመጣቸውን ግለሰቦች ለቋል። ይቅርታ ማለት ተጠያቂነት እነዚህ ግለሰቦች በማንኛውም ወቅት መረጃና ማስረጃ ሲገኝንና መንግስት ሲፈልጋቸው በቁጥጥር ስር የሚውሉ ናቸው። የይቅርታ ህጉ ምህረት ማድረግን አይከለክልም።

አገሪቱ እስካሁን ድረስ በምህረት ታራሚዎችን ለመልቀቅ የሚያስችል አዋጅ የላትም። በአሁኑ ወቅት አዋጁን ለማጽደቅ በሂደት ላይ ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት መንግስት ይህም ሆኖ እስረኞችን የሚለቀው በተቀመጠው የይቅርታ አዋጅ አግባብ ብቻ ነው።

አንድም እስረኛ ከህግ አግባብ ውጪ የተለቀቀ የለም። ሶስተኛ አካልን ወይም ሶስተኛ ወገንን  ጎድተዋል ለሚባሉ ታራሚዎች ይቅርታ አልተሰጠም። በመሆኑም በይቅርታ የተፈቱ አካላት ሁሉ መንግስት ተገቢ መረጃ ካገኘ ወይም ይቅርታ የተደረገለት አካል ከጥፋቱ ካልተማረበት የተሰጠው ይቅርታ በፈለገው ጊዜ ሊነሳ እንደሚችል ይሆናል።

በዚህም መንግስት ይቅርታ እያደረገ ያለው በአገር ውስጥ የነበረውን የፖለቲካ ውጥረት እልባት እንዲያገኝ ከማሰብ እንዲሁም በህዝቦች መካከል የነበረውን ቂምና ቁርሾ በማስወገድ የተሻለ አገራዊ መገባባት ለመፍጠር መሆን መገንዘብ ይገባል።

አሁን ባለው ሁኔታ ሁሉ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ የህግ የበላይነት ሊሸራረፍና ህገ-ወጦች እንዳሻቸው የሚሆኑበት አውድ የለም። ይህ የህግን የበላይነት የማረጋገጥ ጉዳይ በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሰረተውን ፌዴራላዊ ሥርዓቱ የመሰረቱት የሀገራችን ህዝቦች የሚያምኑበት ነው። የአገራችን ህዝብ የህግ የበላይነትን ፅንሰ-ሓሳብ የሚያውቅና የሚያጋጥሙ ነባራዊ ችግሮችን በህግ ማዕቀፍ እየፈታ የመጣ ነው።

የህግ የበላይነት ከሌለ መብት ሰጪና ነሺ በጉልበታቸው የሚተማመኑ ኃይሎች ይሆናሉ። ጉልበተኞቹም ልክ እንደ ሁሉም እስረኞች ይፈቱ እንደሚሉት ወገኖች ሌሎች ዜጎችን እንዳሻቸው ለማድረግ መሻታቸው አይቀርም።

በተለያዩ ወቅቶች እንደተመለከትነው እንኳንስ ዜጎችን ቀርቶ፣ ህዝቡ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ለማድረግ የሚተጉ የፖሊስና የፀጥታ ኃይሎችን ጭምር በአጉራ ዘለለልነት እስከመግደል ሊደርሱ ይችላሉ።

ይህን ሁኔታ ለመከላከልና በየትኛውም የአገሪቱ ክፍሎች ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የህግ የበላይነት መኖር የግድ ይላል። መንግስት ባለበት ሀገር ውስጥ ማንም ሰው ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም። መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እየደረጋቸው ከመጣው መንገድ ፈቀቅ የሚል አይመስለኝም።

ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ በንጹሃን ዜጎች ላይ ለተፈጸመው ጅምላ ግድያ ተጠርጣሪ የሆኑ ዜጎች ወዲያውኑ በህግ ፊት እንዲቀርቡ አድርጓል። ይህም በሚያደርጋቸው የተለያዩ ጉዳዩች ህግና ስርዓትን ተከትሎ የሚሰራ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

በይቅርታ የተለቀቁት ግለሰቦች ጉዳይም ይህን የህግ የበላይነት ከማስጠበቅ አኳያ መታየት ይኖርበታል። መንግስት መብትም፣ ኃላፊነትም ሆነ ግዴታ ያለበት አካል በመሆኑ በህጉ አግባብ መሰረት እስረኞችን ሊፈታና ሊያስር ይችላል። ይህን በማድረግም ህዝቡንም ይሁን በህዝቡ የተመሰረተውን ስርዓት በአግባቡ እንዳይጠብቅ ያደርገዋል።

እንደሚታወቀው ሁሉ ህገ መንግስቱ የህጎች ሁሉ የበላይ መሆኑ፤ ማንኛውም ህግ፣ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈፃሚነት አይረውም።

ማንኛውም ዜጋ፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እንዲሁም ባለስልጣኖቻቸው ህገ መንግስቱን የማክበርና ለህገ መንግስቱ ተገዥ የመሆን ኃላፊነት አለባቸው። የዶክተር አብይ መንግስት በጥቂት ወራት ውስጥ ያደረጋቸው ተግባሮች ይህን መሰረት ያደረጉ ናቸው።

ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን የምታከብረው የምትከተለው ፌዴራላዊ ስርዓት ስለሚያዛት ብቻ ነው። ስርዓቱ ደግሞ ህዝቦች በበርካታ መስዕዋትነት ያመጡት ነው። ራሳቸው ይሁንታ እነዚህ አገር ውስጥ እውን እንዲሆን የፈቀዱት ነው። በመሆኑም ዶክተር አብይና መንግስታቸው ሰብዓዊ መብቶችን በማይነካና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ የህግ የበላይነትን የማስከር ስራ ለማከናወን ጥረት እያደረጉ ነው።

ይቅርታም ይሁን ይሁን ምህረት ሲሰጥ በአገሪቱ ውስጥ በተቀመጠው የህግ አሰራር እንጂ ሁሉንም ታሳሪዎች በጅምላ በመፍታት ሊሆን አይችልም። ታራሚዎች እየተለቀቁ ያሉት በተቀመጠው መስፈርትና በህጉ መሰረት ይቅርታና ምህረት በመስጠት መሆኑን ግንዛቤ መያዝ ይገባል።

በማንኛውም አገር ውስጥ ዴሞክራሲ በማህበረሰቡ ዕይታ የተቃኘ በመሆኑ “ለሰናይ” ምግባሮች ቅድሚያ ይሰጣል—ተከታዩ ማህበረሰብ የሚፈልገውን የሞራል ፈርጅ ካልወገነ ሊከተለው የሚችለው ሊቅም ይሁን ደቂቅ የለምና። በመሆኑም ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ‘ሰናይ’ መንገድ መከተል ብቻ ሳይሆን መንገዱንም ለህብረተሰቡ በማሳየት ፋና ወጊነት ነው።

ህዝብ ሁሉንም ነገር የሚያይ፣ ሚዛናዊና ለየትኛውም ወገን የማይወግን በመሆኑ፤ ማን ምን እንደሚሰራ፣ የትኛው ወገን ሀገሩንና እርሱን ማዕከል አድርጎ እንደተንቀሳቀሰ፣ የትኛውስ ከዚህ ውጭ ሆኖ ራሱን ብቻ በማዳመጥ እንደተንቀሳቀሰ ያውቃል። ዶክተር አብይ እያደረጉ ያሉት ህዝቡ የሚፈልገውን ሰናዩን ይቅርታ ነው። ይቅርታው ግን የህግ የበላይነትን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑን መረጋት ተገቢ ነው።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy