ከሲኮ መንዶው ልጃችን ላይ አይናቹሁን አንሱ
ወራቅሳው
የባረንቱማው አርሲ ሲኮና መንዶ ቤተሰብ በተለይም ከአንገፋው ልጅ ከመንዶ ዘረ ሃረግ የሚመዘዝ አንድን ኢትዩጵያዊ ኦሮሞ ይህ ከማንነትን ነጠቃ አንስቶ እስከ የኃሰት ነብያት ሽኩሽኩታ ለምን ተተኮረበት? ይህ ሰው በርግጥስ ማነው? እነማንስ ይህን ይሰራሉ? እውን ይህ የትኩረታቸው መንስኤ ድብቅ እውነትን ከመግለጽ ወይስ በኦሮሞ ህዝብ በከፋፋይ ፖለቲካ እስትራቴጂ የአይችሉም ቀጣይ ሴራ ለማሳካት ይሆን?
የኦሮሞ ህዝብ አንድነት በአለት መካከል እንደፈለቀ ምንጭ ውሃ በአንድ አቅጣጫ እንዲፈስ ካረጉት አንጋፋ የያኔው ወጣት የፖሊቲካ ሳይንስ ጎበዝ ተማሪ የዛሬው ጎልማሳና ብስል ሙሁር ታጋይ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ሚና አይተኬ ነው። በተለይም በኦሮሞ ህዝብ ትግል በረጅም የትግል ልምዱ፣ በንጹህ ልቡ፣ የፖርቲ ስልጣን ሽግሽግ ሀሳብ ከማመንጨት የራስን ስልጣን እስከመልቀቅ የደረሰ የቁርጥ ቀን የህዝብ ልጅ ነው።
እንደ ኦሮሞ ህዝብ መሪያችንን ጠንቅቀን ብናውቅም ዘርን መፈልቀቆ ማየት ባህላችን አይደለም በስርነ ገዳ ስርአታችን ከተጎናጸፍናቸው የስነ ማህበረሰብ ባህሪያት መካከል ትውልድን የመቁጠርና የመነጠል ሳይሆን ትውልድን የመተንተንና የማውረስ ነው።
#አልገባህም!
በስነ ህዝብ ታሪካችን ከተነሳንበት የኢትዩጵያ መንደር ዛሬ እስከደረስንበት የጂኦግራፊዊ ስፋትና የስነ ህዝብ ምህዳር የጉዲፈቻ(የሙሉ ልጅነት ማእረግ) ፤ሞጋሳ(የሙሉ ኦሮሞነት የመጎናጸፍ ) ፤አመቺሳ(የሙሉ የኦሮሞ የማንነት ስያሜ) አቃፊና አካታች ማንነት የያዝን ህዝብ ነን። በአጭር ቃል የደም ዘረ ሃረግን ሳይሆን ሙሉ ማንነትን በፍቃደህ የሚያጎናጽፍ ብቸኛ ማህበረሰብ ኦሮሞ ነው… ማንም ቢሄር ከኦሮሞ ባይወለድ ከወደደ ባህልና ማንነቱን ከተቀበለ ኦሮሞ የመሆን መብት አለው። በኦሮሞ ስነ ማህበረሰብ አስተሳሰብና እምነት በJus sanguinis(በደም ሀረግ) አልያም በjus soil (በትውልድ ቦታ) ብሎም የnaturalisation(በህጋዊ የማንነት ለውጥ) አያምንም። የራሱን እምነትና ማንነት ያከበረ መሆን የወደደ እራሱ ኦሮሞ ነው። በቋንቋህ ሁነህ ብቻ ሳይሆን በፍቃድህም መሆነ የምትችለው ኦሮሙማ ባለቤት የኦሮሜሱ ድንቅ አቃፊ ስርአት ባለቤት ነው።
ከዚህ የኮራ የደራ በሁሉም ሰብአዊ ስርአት በጊዜ ሂደት የተፈጠሩ የሴራ ፖለቲካ ስነ ባሀሪያት ዛሬ ላይ በለመዱት በትላንት ቀመር እገሌ ኦሮሞ አይደለም እናቱ ፤አያቱ፤አባትና አማቹ ትግሬ አማራ ኤርትራዊ ናቸው ቢባል አያስገርምም። የስልብ ስነልቦና እስትራቴጂ ትናንት በኦሮሞ ትግል አበይ ሚና የነበራቸውን ኦሮሞዎች በጥላቻ ፖሊቲካ ማንነት የመንጠቅ ግብግብ ተይዞው ሰንብተዎል። ዛሬ ለላ ቀን ነው። ያ ሁሉ ከሸፏል። በስም ብቻ የሚገለጽ ማንነት የለም በተግባር ለኦሮሞ ህዝብ ትግልና ለውጥ ጠብ የሚል የማያበረክት በድንቅ ብሄርተኛ አቀንቃኝነቱ የሚወደስበት ጊዜ አክትሟል። ዛሬ ከስም በዘለለ የማንነት መለኪያ ብስለት ላይ ደርሰናል። …
ይሁን እንጂ የህዝባችን ዲና በለውጣችን ውስጥ የቻሉትን ስንጥር ከመሠግሰግ አይታረሙም። በተለይም በምንወዳቸው መሪዎች የመዘንጠል ሙከራው ይቀጥላል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የቱክረታቸው ትኩረት በሲኮ መንዶው የሻሼ ልጅ ላይ ለምን በሚል የወርቅነህን ማንነት ርእስ ማሳጣት ተገቢ እንደሆነ በማሰብ ከቅርብ ቤተሰብ አዎቂ በዚህ መልኩ አጀንዳውን መቋጨት እንደሚያስፈልግ ከመገንዘብ አንጻር ጥቂት ማለት ወደድን። ለዛሬው እንደ አንድ ግለሰብ ስለዚህ የዘመን የጥምረትና የአንድነታችን ሞገስና ተመሳሌት ሰው እንድጽፍ ግድ ያለኝ የአሻጥርና ደባ አካሄድ ነው።
የዶ/ር ወርቅነህ እውነታዎች መካከል ሁሉም ሊያውቀውና ሊረዳው የሚገባ ሀቅ የ17 ቤት ቆጥሮ በመንዶ ሃረግ ስለመመዘዝ ትንተና አይደለም ቢሆን እንኳን ከጊፍቲ ዎዩ እቅፍ እስከ ገደሞጂ ያለውን እድሜያቸውን ያሳለፉ የእያንዳንዱ ትውልድ በስርአት ዘርዝሮ ማንነታቸውን ለሚውቅ ኦሮሞ የሌሎች ምስክርነት አልያም ጠቋሚነት አያሻም ጠንቅቆ ያውቃልም። ከዚህ አንጻር በተለየ የሚነዛው የአያት ስም ለውጥ ከየት መጣ? ለምንስ ሆነ?… ስም ለውጥ የማንነት ለውጥ መሠረት ሊሆንይችላልን? የሚለውን እንመልከት። በርግጥም ዶ/ር መረራ ጉዲና በ1980ቹ መጀመሪያ በፖሊቲካ ሳይንስ ዲግሪ ሲያስተምሩትና ከኢህአፖው አቀንቃኝ ክንፈ አሰፈ ጋር ቅርርብ በኖራቸው -በዚያ ጊዜ የዶር ወርቅነህ የአያት ስም ወ/ማርያም አልያም ወ/እግዚያቤሄር መባሉ ትክክል ነው። እውነታው ግን ትክክለኛው የእናት አባት ዎቄፈና ስማቸው ነገዎ መባሉና በዘመኑ በተቀበሉበት የክርስትና እምነት ተከታይነት ከጊፍቲ ሀመቺሳ ስማቸው ወደ ክርስትና ስም መቀየሩን መረዳት ተገቢ ነው። ታዲያ በዘመኑ መጀመሪያ 1980 አጋማሽ የብዝሃነትና እኩልነት ማቆጥቆጥ የግለሰብ ስም ብቻ ሳይሆ የከተሞች ስምም ከክርስትና አብዬት ስም ወደ ቀድሞ የማንነት ስም መመለስ የወቅቱ እውነታና መብት ነበር። በአጋመጣሚ ሳይሆን አስበውበት እጅግ ብዙ ኦሮሞ ወጣቶች የግልና የቤተሰብ ስማቸው ወደ ቀድሞ የማንነት ስያሜ ቢቀይሩ ለምን ማለት ማንነት አለመረዳት ነው። እውቅ የኦሮሞ አቀንቃኞች መካከል በተመሳሳይ ስያሜ በክርስትና ስም አባትና አያታቸው መነሳቱ ማንነታቸውን አልቀየረም። ጌታቸው ወልደ ማሪያም፣ ጸጋዬ ዳንደና እና ሀጫሉ ሁንዴሳ ቦንሳ የመሥሠሉ በጣም ተወዳጅ የኦሮሞ አቀንቃኞች እንደ ዶ/ር ወርቅነህ አያት አልያም አባት በክርስትና ስም የሚጠሩ ወይም የቀየሩ ናቸው።
ይህ እንዳለ የሻሸመኔው ዶ/ር ወርቅነት ለምን የሚድያ ማዳመቂያ መደረግ ተመረጡ የሚለውን ስንመልከት
የዶር ወርቅነህ የፀና ፖለቲካዊ አቋምና ባህሪ አንዱ ተጋላጭነትን ፈጥሮባቸዎል። ዶ/ር ወርቅነህ ከልጅነት የሚታወቅበት የአካዳሚክስ አለም ባሻገር በአመራር ባህሪው ኮስታራ፤ ብዙ ከመናገር ያመኑበትን የመተግበር አቅም ያላቸው ቅንና ቆራጥ ፖለቲከኛ ናቸው። በቱኩረት የፖሊቲካ ደሊበራንስ የሚታወቁት ዶክተሩ ከተሰጣቸው ሀላፊነት በብቃት ከመወጣት ያለፈ የጣልቃ ገብነት አመራር ባህሪ የላቸውም። ይህ ባህሪ ከውስጥም ከውጭም አካላት በተየይም በወቅቱ የነበራቸውን ወሳኝነት ያልወደዱ የስም ማጠልሼት ዘመቻ ቢከፍቱ አይገርምም። በወቅቱ ፖለቲካዊ ተቃውሞ የትም ፍጭምና ገልብጭው ትግል የነዚህን ሰው ወሳኝነት ማን ይወደዎል? ታዲያ ይህን በተለይም ከልጅነታቸው ጀምሮ ኢህአፖ የፖሊቲካ አማራጭ የማይዎጥላቸው ዶ/ር ወርቅነህ እንደ #ክንንፈ_አሰፋ አይነት የክፍል ጓደኛ በጫፍ የረገጠ የዘር ምንዘራ ፖለቲካ አልያም በደርግ ተደፍጥጦ በከተማ ለታፈነ ኢህፖ አለመወገናቸው እንደ ክህደትና ስህተት በማንሳት የጠላትነት ፍረጃው ለመሰሎቹ በሰበር ዜና ቢያስኮመኩም አይደንቅም። በወቅቱ ይህን ሰምቶ አሉታዊ ተጽኖ ውስጥ ያልወደቀስ ማን ነበረ? ይሁንና ያም አልተሳካም።
የለያይቶ የመግዛት ምቹ አማራጭ፡- ዶር ወርቅነህ በተለያዩ ጊዚያት ከሚነዛባቸው ወሬ መካከል በቅርብ በ#ዘ_ሀበሻና_ሹክሹክታ በሚባሉ የድህረ ገፅና የዩቲቭ ገጾች የሚነሱ የሀሰት ሹክሹክታ ዎነኛ አላማ በኦሮሞ ህዝብ ብሎም በኢትዮጵያውያን ፖለቲካ ውስጥ እየመጣ ያለው ፍጹም ሰላምና አንድነት ለህልውናቸው አስጊ መሆኑ በፖለቲካ የተቃውሞ አባዜ የተከተቡ አልፎም በዶ/ር አብይና ዶ/ር ወርቅነህ እረፍት የለሽ ድሎች የተለየ ርእስ ያጡ ሚዲያዎች ዶክተሩን ለከፋፍለህ ሞክር እስትራቴጂ ቢጠቀሙበት የተሻለ ይሆናል ከማለት ነው። የሚገርመው ግን በኦሮሞ በተለይም ከእጅግ ተወዳጅ መሪያችን ኦቦ ለማ ቲም (ኦህዴድ) ማግስት እየታየው ያለው ለውጥ ኦሮሞን ችግርና ሀሰተኛ ውጅምብር ከማፍረክረክ ይልቅ አንድነቱን እያጸናው ወሳኝነቱን እያጠነከረ መምጣቱ ነው። በዶ/ር ከስራ ተነሰረተዎል፣ መለሠቀቂያ አስገቡ ጫወታ የኦሮሞ አክቲቪስቶች በጠላቶቻቸው በአንድነት የመዝመት አንቲ ቦዲ እንዲያበለጽጉ አርጓቸዎል። ስለዚህ ኦሮሞ ህዝብ ካገኜው ህብረት አንድነት አንጻር፡ የእንዲች አይነት ሹክሹክታ ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣል-ይበልጥ ታጣምረወረለች። ኦሮሞ እንደሚስማር ባልከው በሰነዘርክ ቁጥር የሚጠብቅ የሚያጣብቅ ዘንግ እየሆነ መጥቷል። ስለዚህ የፈጣራ ማንነትና ሹም ሽረት ዲናችንን እንድንለይ እየጠቀመን ይበልጥ እያጠነከረን ነው።
በሌላም በኩል መገንዘብ ያለብን በዲጅታል አለም አሁን አሁን ሥስት ዲጅታል ቢዝነስ ጡፎል: የYoutube የምስል ተመልካች ማግኜት እሽቅድምድሞሽ፤ የFacebook ተከታይ የማሴታወቂያ ኢንስታንት መልእክት ገቢ እና የGoogle ድህረገጽ የማስታወቂያ ስራዎች ገቢ ማመንጨት ናቸው። በቀጣይ ለአገራችን አደገኛና ጥንቃቄ ከሚሹ አብይ ጉዳዩች ዶላር አደር የድህረገጽ ጥገኛ መረጃና ፖለቲካ አጀብ ናቸው/ይሆናሉ። ህዝብ መንቃት ካልቻለ ለውጣችንን ሊጎዱት ይችላሉ።
#ማጠቃለያ
እንግዲህ ለአንድ ሹክሹክታ ብዙም እሩምታ ባያስፈልግም በዚች በተነዛችው አናሳ ውሸት ላየ ተመርኩዘን የተሻለ ግንዛቤን ለመፍጠረረ ትሆን ዘንድ ነው። ዛሬ ላይ የኦሮሞ ፖለቲካ በአዳዲስ ወጣት ትውልድ የሚመራ የተራራ ላይ ጫፍ እየደረሰ ነው። ማንም ወደኃላ ሊመልሰው አይቻለውም በአዲሲቷ ኢትዮጵያውያ አብዬት እንደ ትኩስ እሳተ ጎመራ አለትና ጠላት እያቀለጠ ዛሬን ደርሷል በቀጣይም ከፊት ያሉትን ጉቶ እየነቀለ ጉድጓድ ጎሮጎዴ እየሞላ ከወንድም ህዝቦች ጋር ይጓዛል። በሁሉ የተደላደለች ኢትዩጵያንም ለቀጣይ ትውልድ አውርሶ ይኖራል በዚህ ሂደት ገና ብዙ መልካም ተአምር ከምናይባቸው አመራር የዶር ወርቅነህ ቆራጥና ቀጣይ ሚና ይቀጥላል።
“ዛሬ ላይ ከዶ/ር ወርቅነህ ማንነትና ስጋት ይልቅ በአገሬ ላይ ያለውን በጎ የፍትህና ለውጥ ማየት ነው የምፈልገው መመዘኛየም ይህ ነው…ጎበዝ በትላንት ቦታ ለይ የለንም”
#መልካም ቀን