Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

…ምን ማለት ነው?

0 2,110

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

…ምን ማለት ነው?

                                                             ታዬ ከበደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ስለ ምርትና ምርታማነት እድገት አስመልክቶ በቅርቡ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ፤ መንግስት በአገራችን የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ የመንግስት ጥረት ችግሩን ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

በአሁኑ ወቅት በጥቁር ገበያ የዶላር ምንዛሬ ላይ የታየው ለውጥ የችግሩ መፍቻ አንዱ እርምጃ ነው። ይሁን እንጂ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ምርትና ማርታማነትን ማሳደግ ሲባል ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ ማንሳት ያስፈልጋል። ምክንያቱም ችግሩን ለዘለቄታው መፍታት የሚቻለው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ነው።

በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ምርትንና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ችግር መፍቻ ዋነኛው ቁልፍ ነው። መንግስት ግብርናውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ተገንዝቦ እየሰራ ነው። በያዝነው ሁለተኛው የልማት ዕቅድ ላይም በመጀመሪያው የዕቅድ ዓመት ላይ የተገኘውን አመርቂ ውጤት ይበልጥ አጎልብቶ ለመቀጠል ብርቱ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

በአገራችን መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በግብርናው ዘርፍ ነው። ግብርናው ለውጥ ማምጣት ይችል ዘንድ በበሁለተኛው አምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትኩረት ተሰጥቶታል።

ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ እየተሰራ ነው። የምርትና ምርታማነት ማደግ ማለት አርሶ አደሩ ባለችው መሬት ላይ ከፍተኛ ምርት ሲታገኝ ነው። በአነስተኛ መሬት ላይ ከፍተኛ ምርት ሲያመርት ነው። በተለይ በአሁኑ ወቅት ይህ ሁኔታ እንዲሳካ ጥረት እየተደረገ ነው። መንግስት አርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

መንግስት ለዘመናዊ ግብርና ያልተደፈረውን የአገሪቱን አርሶ አደር የአስተራረስ ዘይቤ የመለወጥን አስፈላጊነት ተገንዝቦ በቀየሰው መስመር እነሆ የሚታየ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው። አርሶ አደሩ በድርቅ በቀላሉ መጠቃት ምክንያቱም ደግሞ የዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ አለመኖር እንደሆነ ግልፅ ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ኑሮው እንዲሻሻል ተገቢ ትኩረት አግኝቷል። ለዚህም በቂ ማሳያዎችንም ማቅረብ ይቻላል። መንግሥት የዘመናት ቁጭቱን አገራዊ መሠረት ባላቸው አቅጣጫዎች የመፍታት ትግሉን እያካሄደ ነው።

አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና ላይ እንዱገኝ እየተደረገ ነው። በቀጣዩ የመኸር ምርት 370 ሚሊዩን ኩንታል እንዲያመርት የግብዓት አቅርቦቶች እየተደረጉለት ነው።

በዚህም በአሁኑ ወቅት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ለውጥ ማምጣት ችለዋል።  አርሶ አደሩ ባለው መሬት ላይ የሚታይና አሳማኝ ውጤት እያመጣ ነው። ይህም መንግስት እየተከተለ ካለው የማስፋት ስትራቴጂ የሚመነጭ ነው። ይህም በየዓመቱ ምርትና ምርታማነት እየጨመረ እንዲሄድ አድርጓል።

አገራችን የአርሶ አደሩን ምርታማነት በማሳደግ፣ ለምርቱ ገበያ በማመቻቸትና ከግሉ ዘርፍ ጋር ትስስር በመፍጠር ምርትና ምርታማነትን አሳድጋ ተጠቃሚ በመሆን ላይ ትገኛለች። አርሶ አደሩም የለውጥ መስመሩን ተረድቶ በእምነት ወደ ስራው በመግባቱ የሚያመርተው ምርት እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል። በተለይም መንግስት በሚያደርገው ድጋፍ በከርሰ ምድርና በገፀ ምድር እንዲሁም ውሃን እያቆረ በመጠቀም እስከ ሁለቴ ድረስ ማምረት እየቻለ ነው። ይህ ትልቅ ለውጥ ነው።

ጄኔሬተሮን በመጠቀምም የወንዝ ውሃን ጠልፎ ጥቅም ላይ በማዋል እየሰራ ነው። ይህምከራሱ ፍጆታ አልፎ ለከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ ፍላጎት የሆኑትን ምርቶች እንዲያቀርብ አስችሎታል።

መንግስት ባመቻቻው ልዩ ሁኔታ ከዝናብ ጥገኝነት በተላቀቁ አመራረት የተገኙትን ምርቶች ለራሱም እየተጠቀመ ነው። ይህም የመስኖ ልማት ስራን በመገንዘብ ለበጋ የሚሆኑ ምርቶችን እንዲያቀርብ አድርጎታል። የግብርና ምርቱም እጅግ እንዲያድግ አድርጓል።

ከገበያ አኳያም አርሶ አደሩ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለታል። በራሱ በራሱ ካቋቋማቸው የህብረት ስራ ማህበራት በኩል ምርቱን ለገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እያቀረበ ነው። የለፋበትን ዋጋም እያገኘ ነው።  

የግብርናው ዘርፍም በአስተማማኝ ሁኔታ ገበያው ሳያሳስበው ምርትና ምርታማነቱን በማሳደግ ላይ ብቻ አተኩሮ ለልማት ለውጥ ሽግግሩ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥርበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ጥረት እየተደረገ ነው።

በተናጠል ሊፈቱ ያልቻሉ ችግሮች ራሱ ባቋቋማቸው ማህበራት አማካኝነት እየፈታቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ያቋቋመው የምርት ገበያ በኩልም የየዕለት ዋጋዎችን እየተመለከተ ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል።

ምርት ገበያው የሚያገበያያቸው እንደ ሰሊጥና ቦሎቄን የመሳሰሉ ምርቶችን በገበያው ዋጋ መሰረት እንዲገበያይ እየተደረገ ነው። እንዲሁም አርሶ አደሩ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የማድረግ ጥረት ለምርታማነቱ የጎላ ሚና እየተጫወተ ነው።

በአሁኑ ሰዓት አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና እንዲፈጠር አድርጓል።

ምርትና ምርታማነት በማደረጉ ምክንያት አርሶ አደሩ ከተጠበቀው በላይ ምርት እያመረተ ነው። ይህ ሁኔታ ትርፍ አምራች አርሶ አደሮች በድርቅ የሚጎዱ አካባቢዎችን የምግብ ፍጆታ እንዲሸፍኑ አድርጓቸዋል። ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

እነዚህ ሁኔታዎች በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ምርትና ምርታማነት እንዲያድግ ያደረጉ ናቸው። ይህ እንዲሆን መንግስት ከፍተኛውን እገዛ አድርጓል። የምርታማነት ማደግ የአምራቹን አርሶ አደር ተጠቃሚነት እያረጋገጠ የአገርን ኢኮኖሚ የሚያሳድግ ነው። ምክንያቱም እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የያዘው የግብርናው ዘርፍ አሁን ባለንበት ደረጃ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመለወጥ የሚያስችል ስለሆነ ነው።  

 

    

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy