Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሪፎርም ውጤትና ሪፎርም የሚሹ ነጥቦች

0 1,059

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሪፎርም ውጤትና ሪፎርም የሚሹ ነጥቦች

ሞገስ ፀ

ኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀዉሶችን ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ በ2010 ዓ.ም የከፋ መልክ እየያዘ መጥቶ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጉዳት ተከስል፡፡  የነበሩ ግጭቶችም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፈው አልፈዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የኢኮኖሚው እድገት ወደ 1አሀዝ የወረደ ሲሆን ፈጣን እድገቱ ግን አሁንም ቀጥሏል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ 863 የአሜሪካ ዶላር ደርሷል፡፡ በ2010 ዓ.ም የዋጋ ንረቱ ወደ ሁለት አሀዝ ከፍ ብሏል፡፡

የግብርና ሴክተሩ በትምህርት እምብዛም ያልተደገፈ ስለሆነ ከአየር ንበረቱ ጋር እነዲዋዥቅ አድርጎታል፡፡ ይህ ዘርፍ በባህሪው ብዙ የሰው ጉልበት ይጠቀማል፡፡  ሰፊ የሰው ጉልበት የሚጠቀም የአጨዳ ስራዎች በሰው ጉልበት ታግዘው ሚካሄዱበት አሰራር የምርት ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ሴከተሩ ከዝናብ ጥገኘነት ተላቆ ወደ መስኖ እንዲዘም ለማድረግ በ2010 ዓ.ም በጀት አመት መልካም ሰራዎች ተሰርተዉ አልፈዋል፡፡ አሁን የሚሰተዋለውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትም ከኤክስፖርት አፈፃፀማችን ጋር የተያያዘ ስለሆነ መገምገም ይኖርበታል። ዋነኛ መፍትሄውም ኤክስፖርት የሚያደርጉ ነጋዴዎችን ማበረታታት ነው፡፡ እንዲሁም በዚህ በጀት አመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ስድስት መቶ ስማኒያ ስምንት ነጥብ ስድስት የአሜሪካን ዶላር እዳ ክፍያ ተፈፅሟል፡፡

የፌደራል መንግስት 2011ዓ.ም በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀድቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የሰጡት ማብራሪያም  መንግስታቸው በ2011ዓ.ም ከያዘው በጀት ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው ድህነት ቅነሳ ላይ ለሚያተኩር ፕሮግራሞች እንደሚውል ጠቅሰዋል፡፡ ከጠቅላላው በጀትት 55 በመቶ የካፒታል በጀት 45 በመቶ ደግሞ መደበኛ ወጭ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች አንፃር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ አመት ኢኮኖሚው ከማሳደግ አንፃር በተለይ በማዕድን ልማት፣ አበባ ልማት፣ በቱሪዝም እና በውጭ ንግድና ሌሎችም ዘርፎች ትኩረት ይደረጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮንትሮባንድ ንግድን መቆጣጠር እና የገቢ አሰባሰብን ማስተካከሉም ትኩረት እንደሚደረግበት አስገንዝበዋል፡፡

በተለይ ግብር መክፈል ለሀገር ጥቅም መሆኑን አውቆ ያለማንም አስገዳጅነት ሁሉም ዜጋ መክፈል ይኖርበታል። መንግስትም ህብረተሰቡን በማስተማር ግብር አሰባሰቡን ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ ይጠበቅበታል። በቀጣይ ኣመት አዲስ የሚጀመር የልማት ፕሮጀክት የለም ያሉት ዶክተር አብይ አሁን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን  ዶላር ይስፈልጋል ብለዋል፡፡ የታክስ ስርአቱን ማሻሻል እና ማዘመን፣ ወጪ መቀነስ፣ የመንግስት ተቀማጭ ገንዘብን ማሳደግ እንዲሁም ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጉዳይ ውስጥ ስራዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት አመታት በከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞና አመፅ ስትታመስ ቆይታለች እንዲሁም ሰላምና መረጋጋት ከዜጎች ርቆ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማለትም በሶስት ወር ውስጥ መንግስት ተስተውሎ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ቀላል በማይባሉ ተቋማት ላይ ሪፎርም አካሄዷል በፖለቲካውም በኢኮኖሚውም ዘርፍ ፣ይህ ሪፎርምም ቀጣይነ ያለው ነው፡፡ ይህ ሪፎርም ተስተውሎ የነበረውን ችግር ከመፍታት አንፃር በሁሉም የመንግስት ተቋማት ለውጥ እያመጣና ሀገሪቱን ወደ ተሻለ መረጋጋት እያሸጋገራት ይገኛል፡፡

ጥቂት በሚባል ጊዜ ውስጥ ጥሩ የሆነ የኢኮኖሚ መረጋጋትና የፖለቲካ ለውጥ የተስተዋለ ይገኛል፡፡ እንዲሁም ለዘመናት  በቀጠናው ሲስተዋል የነበረውን የፖለቲካ አለመረጋጋት ወደ ተሸለ ምቹ ሁኔታ ለመለውጥ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ቀጠናውን የተረጋጋ ለማድረግ እየሰራች ትገኛለች፡፡ ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው ከኤርትራ ጋር ያለውን አለመግባባት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍታት መቻሉ ነው፡፡ በትጥቅ ትግል የሚያምኑ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ይህንን የፖሊሲ ለውጥ እና የሰላም ጥሪን በመከተል ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ችግሮቻቸውን በመፍታት ላይ ይገኛሉ፡፡

በአሸባሪነት ተፈረጀው የነበሩ የትጥቅ ትግሎችም  ማለትም እንደ ግንቦት ሰባት፣ ኦብነግና ኦነግ ያሉ የትጥቅ ትግሎች፣ በተጨማሪም በወንጅል ሚፈለጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ምህረት ተደርጎላቸዋል፡፡ እንዲህ አይነት ዕርምጃዎች የሰላም ጥሪውን የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርጉ ብዙዎችን እያስማማ ነው፡፡ የታራሚዎችን አያያዝ በተመለከተም ኢ-ስብዊ በሆነ መንገድ ታራሚዎችን ሲያሰቃዩ የነበሩ የመንግስት አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብም ተፈጥሯል፡፡

ብዙ ሊባል በሚችል ሁኔታ የፖለቲካ እስረኞችም ምህረት ተደርጎላቸዋል ፡፡ ብዙዎቹ ደግሞ ያለወንጀላቸው ፍርድ ተፍረዶባቸው ታስረው የነበሩ ታራሚዎች ናቸው፡፡ ለታራሚዎች ምቹ አይደሉም ተብለው ቅሬታ ከቀረበባቸው ማረሚያ ቤቶች ውስጥ  ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት እነዲዘጋ ተደርጓል፡፡ በተለይ ደግሞ በሃቅም ውስንነት እና በችልተኛነት ምክንያት የህዝብን ቅሬታ መፍታት ባልቻሉ የመንግስት አካላት ከፌደራል እስከ ቀበሌ አዲስ ሹም ሽር እና ሪፎርም በማካሄድ አዲስ ለውጥ እንዲመጣ ተደርጓል፡፡ ህዝብን ሲበድሉ በነበሩ አመራሮች ላይም እርምጃ ተወስዷል፡፡

የኢኮኖሚውን ዘርፍ ለማነቃቃት ሲባል በመንግስት ቁጥጥር ስር የነበሩ የመንግስት ተቋማት ሙሉ በሙሉና በከፊል ወደ ግል እንደሚዛወሩ ይፋ ካደረጋቸው የልማት ድርጅቶች መካከል ውስጥ ኢትዮ ቴሌኮም፣ መብራት ሀይል፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የባቡር ትራንስፖርትና ውሀ ናቸው፡፡ ይህም ነፃ የሆነ ገበያን ከማረጋገጥ አነፃር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ እንዲሁም የግል ባለሀብቶች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ባለሀብቶችን በማወዳደር  ለተጠቃሚው ጥሩ የሆነ አማራጭና ዘመናዊ የሆነ አገልግሎት ከማግኘት አንፃር የሚበረታታና የተከሰተውንም የምንዛሬ እጥረቱን ሚቀርፍ ይሆናል፡፡

የመንግስት የፋይናንስ ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግ እየተደረገ ባለው ለውጥና ሽግግር ውስጥ ብዙ እመርታዎች እይታዩ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሪፎርሞች አገሪቱ ከገጠማት የፖለቲካና የኢኪኖሚ ችግር ለማውጣት ታሳቢ ያደረገ ስለሆነ ዜጎች ህይንን በመረዳት ለሀገራቸው እድገት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

መንግስትም ለዜጎች ምቹ ሁኔታን መፍጠር ይኖርበታል፡፡ ስለሆነም አንድ ሀገር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሰላም ከሌላት ዜጎቿ ይሰደዳሉ፡፡ ሀገሪቱም ከዜጎቿ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ሳታገኝ ትቀራለች፡፡ ኢትዮጵያም በርካታ ዜጎቿ በሰው ሀገር ይገኛሉ፣ ለዚህም በዋናነት ጥሩ የሆነ የፖለቲካ ምህዳርና አቅም ያለው ኢኮኖሚ አለመኖሩ በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ አሁን የተካሄደ ያለው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም በመከተል ዜጎች ከስደት መታቀብ ይኖርባቸዋል፡፡ በስደት ላይ የነበሩ ዜጎችም ወደ ሀገር ቤት በመግባት በሀገራቸው ሰርተው እንደሚለወጡ ማመን ይኖርባቸዋል፡፡

የሀገርን አዉንታዊ ገፅታ ከሚያበላሹ ነገሮች ውስጥ ቀዳሚው ስደት ነው፣ ሰለዚህም የፖለቲካ መግባባቱን ተከትሎ መንግስት እያመቻቸ ያለውን የስራ ዕድል በመጠቀም ሳይሰደዱ በሃገር ውስት ሰርቶ መለውጥ እንደሚቻል በማወቅ በአገር ውስጥ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል፡፡ አሁን ለኛ ገነት መስለው የሚታዩን ሀገሮች ከ30 እና ከ40 አመት በፊት ከኛ የባሱ ደሀ ነበሩ፣ ነገር ግን ወደ ሰዉ አገር ሳያማትሩ ጠንክረው በመስራታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ አሁን ያሉበት ደረጃ ለመድረስ ችለዋል፡፡ እኛንም እነሱን ተመልካች ማድረግ ችለዋል፡፡ በሀገር ውስጥ መስራታችን ከስደት ይታደገናል፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ካደጉ አገራት ተርታ ለመሰለፍ ያስችለናል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ እንዳለው በመረዳት በአዲስ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ መሰረተ ድንጋዩ ከተጣለ ሰባት አመታት ተቆጥረዋል። ባሁኑ ጊዜ ግንባታውም ከ63% በላይ ሆኗል፡፡ የሁሉም አሻራ ያረፈበት ይህ ታሪካዊ ግድብ ሲጠናቀቅ ብዙ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡፡ ለአብነትም ለመስኖ፣ ለቱሪዝም መስህብነት፣ ለአሳ እርባታነት፣ ለመዝናኛነትና ለኤሌክትሪክ አገልግሎት ይውላል፡፡ በተለይ ደግሞ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘት አንፃር ቀላል የማይባል ጥቅም ይኖረዋል፡፡

የፖለቲካ አለመግባባት በነበረበት ጊዜ ለአፍታም ሳይቋረጥ ሲገሰግስ የነበረው ይህ ግድብ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ብዙዎች ሲገምቱት የነበረው ግድቡ በውሰጣዊና በውጫዊ ሀይሎች ግቡን አይመታም ብለው ሲያስቡ ነበር፣ ነገር ግን ጊዜአዊ አለመግባባቶች ሳያግዱት ይሄው አሁን ላለበት ውጤት መብቃት ችሏል፡፡ ከጎረቤት ሀገሮች ጋርም የነበረውን አለመግባባት በላቀ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ከስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡ ከሚካሄደው የመንግስት ለመንግስት ዲፐሎማሲ ጥረቶች ጎን ለጎንም በፐፕሊክ ዲፐሎማሲ ቡድን በፐፕሊክ ዲፐሎማሲ መስክም በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ይህ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው የሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለሆነ በጋራ ከግቡ ማድረስ የሁሉም ዜጋ ላፊነት ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy