Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የተከበራችሁ በተባበሩት አሜሪካ ግዛቶች የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን

0 301

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የተከበራችሁ በተባበሩት አሜሪካ ግዛቶች የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንዲሁም ለሚዲያው ማህበረሰብ “ግንቡን በማፍረስ ድልድዩን እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በሃምሌ 19፤20ና 21 (እ.ኤ.አ ጁላይ 26 27፤ 28 እና 29)በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር አብይ አህመድ በሚመራ ከፍተኛ ልኡክ ቡድንና በኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መካከል ለሚደረገው ታሪካዊ ግንኙነት በተዘጋጀው የጋዜጣዊ መግለጫ ስለተገኛችሁ በራሴና በመላው የኮሚቴ አባላት ሥም  ምሥጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

ክቡር ዶ/ር አብይ ያሉትን በመጥቀስ መልእክቱን ልጀምር

“በውጭ አገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለስራም ሆነ ለትምህርት በሄደበት ሁሉ ኢትዮጵያን ተሸክማት ይዞራል፡፡ ኢትዮጵያዊ ከኢትዮጵያ ታወጡት እንደሆነ ነው እንጂ ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ አታወጧትም የሚባለው ለዚህ ነው፡፡ ሁላችሁም በታታሪነታችሁ፤ በእውቀታችሁ እና የትም በሚከተላችሁ የአገራችሁ የጨዋነት ባህሪ የኢትዮጵያ የእሴቶቿ እንደራሴዎች ናችሁ፡፡” ብለዋል፤

የጠቅላይ ሚኒስትራችን ልባዊ እምነት የሆነው ይህ ጥሪ በአገራችን ታሪክ በመጭው ሐምሌ መጨረሻ ይካሄዳል ተብሎ የሚታሰበው ታላቅ ሕዝባዊ ጉባኤና ልዩልዩ የውይይት መርሃ ግብሮች በአገራችን የ50 አመት ታሪክ ውስጥ በይዘቱም ሆነ በመጠኑ የተለየ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡ ልባዊ ይቅርታ እንዲጀመር ብሩህ ተስፋ የተሰነቀ ሲሆን ፍቅርና አንድነት  በአገራችን ኢትዮጵያ እንዲሰፍን በሕዝቦቿ መተማመንና መቀራረብ እንዲጐለብት ወደፊት አርቆ የማየት የአስተሳሰብና የሃሣብ ልእልና ባህል ማምጣት እንድንጀምር የመጀመሪያውን ምእራፍ የሚከፍት ነው፡፡

 

  • ይቅርታ ከመንግሥት ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን
  • ይቅርታ ከሃይማኖት አባቶች ለምእመናን እንዲሁም  እርስ በእርሳቸው
  • ይቅርታ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ለተከታያቸውና ለሚያገለግሉትና ለሚወክሉት ሕዝብ ያስፈልጋል፡፡
  • የጉባኤያችን ቀጣይ መልእክት በየዘመኑ የነበረውን የመጀመርና የማቋረጥ ሂደት በመወለጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ የአገራችን ብልጽግና እንዲጐለበት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ በዚህም አገራችንና ሕዝቦቻችን ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

 

በአጠቃላይ ይቅርታ የተሳካ የሚሆነው ሁሉም ወገኖች ከልብ ሲፈጽሙት ችግሩ ዳግም እንዳይመለስ፤ እየቀነሰ ሄዶ እንዲጠፋ ከማድረጉም በላይ  በሰበብ አስባብ የማይናድና አብሮነቱ እየተገነባ የሚሄድ ሲሆን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለበሰለና ለሰከነ የሃሣብ ነጻነትና ትግል በር ይከፍትና ግለሰቦችና ቤተሰብና ማህበረሰብ በአጠቃላይ በአገር ደረጃ በማያቋርጥ ሁኔታ እያደገ እንዲሄድ ያስችለዋል፡፡ የዚህ የፍቅርና ይቅርታ እርቅና ከልብ መወዳጀት ውጤቱ ሁሉም ወገኖች  አሸናፊ ሲሆኑ ነው፡፡

 

 

  • ይቅር ባይነት ፍቅር ኢትዮጵያዊ አንድነትና መተሳሰብ ምን እንደሚመስል  ዛሬ መግለጫ እየሰጠንበት ባለበት ኤምባሲያችን በግልጽ ባለፉት ሁለት ወራት መታየት ጀምሯል፡፡

 

 

 

  • ወደ ኤምባሲያችን መጥተው የማያውቁ ወገኖቻችን መምጣት ጀምረዋል፤ በጋራ ተሰባስበን እየመከርን ቆይተናል፡፡

 

 

 

  • በተለያዩ ምክንያት ርቀው የቆዩ ወገኖችን፤ በልዩ ልዩ መንገዶች ተቃውሞ ያሰሙ የነበሩ፤ ይደግፉ የነበሩ፤ ገለልተኛ ሆነው ይመለከቱ የነበሩ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ከልብ ሲወዱ ማሳየት የሚችሉትን ልዩ አክብሮትና ፍቅር የሚገልጹበት መድረክ በመፍጠር ግንቡን አፍርሰን ድልድዩን መገንባት እንደምንችል በተግባር አሳይተናል፡፡ ያልመጡትም በያሉበት ከልባቸው ድጋፋቸውን ገልፀዋል፡፡ ሰልፍ በመውጣት በመጻፍ በልዩ ልዩ መገናኛ መንገዶች ይህንን ታሪካዊ ክስተት መጠቀም አለበን ብለው መክረውበታል፡፡ ከልብ በመፍቀዳቸውም የተነሳ አስተዋጸኦ እናበረክታለን ባሉት ሁሉም ያለምንም ጐትጓች ተሳትፈውበታል እየተሳተፉበት ነው፡፡ በዚህም ውድ የሆነውን የሰው ሃብታችንን በማሰባሰብ የአገራችን ልማት እውን ማድረግ ያስችለናል፡፡

 

 

 

  • ኤምባሲያችን ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ቤታቸው መሆኑን፤ ሁላችሁም ባለቤቶች መሆናችሁን ከገለጽን ጊዜ ጀምሮና ክቡር ጠቅላይ ማኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ላደረጉት ጥሪ የተሰጠን ምላሽ እጅግ የሚያረካ ስለሆነ በራሴና በኤምባሲያችን ስም አመሰግናለሁ፡፡ እስከሁን ለደረሰው ችግርና ለተፈጠረው ሁሉ ጥፋት በዚህ አጋጣሚ ይቅርታ እየጠየቅን አብሮ ለመሥራትና እናንተን ለማገልገል ያለንን ልባዊ ዝግጅት በእኔና በመላው የሥራ ባልደረቦቼ ሥም በአክብሮት እገልጻለሁ፡፡

 

 

 

  • በሁሉም ቦታ ሆናችሁ የክቡር ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይን መምጣት በጉጉት ለጠበቃችሁ፤ ኃላፊነቱንም ወስዳችሁ ለተረባረባችሁ፡ በርካታ ገንዘብና ጊዜያችሁን አጥፍታችሁ ሰልፍ የወጣችሁ ውይይት ያደረጋችሁ በርቱ ላላችሁንና በማንኛውም መስክ ለተሳተፋችሁ ሁሉ በኮሚቴያችንና በኤምባሲያችን ሥም እያመሰገንኩ የተጀመረው በጥራት፤ በብቃትና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ውጤቱን እስክናይ ድረስ ጥረታችን ተጠናክሮ እንዲቀጥል በትህትና እጠይቃለሁ፡፡

 

አመሰግናለሁ!

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy