Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአፍሪካ ቀንድን ጆኦፖለቲካ የቀየረው ጉብኝት

0 514

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአፍሪካ ቀንድን ጆኦፖለቲካ የቀየረው ጉብኝት

በክቡር የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጉብኝት ማጠቃለያ ላይ ኢትጵያና ኤርትራ የተለያዩ ስምምነቶችን መፈራረማቸውን የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለፁ፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ክቡር ዶ/ር አብይ በኤርትራ ባደረጉት ጉብኝት ላይ ያለ ሶስተኛ አካል ጣልቃ ገብነት የተደረሰው መግባባት እና ስምምነት የአፍሪካ ቀንድን ጂኦፖለቲካ የቀየረ ነው ብለዋል፡፡

መሪዎቹ የጥላቻ የፖለቲካና አሉታዊ የዲፕሎማሲ ቅስቀሳ ላለማድረግ፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመቀጠል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ እንዲጀምርና በወደብ አጠቃቀም ላይ በጋር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ለ20 ዓመታት አይደለም ለአንድ ቀን ሰላም ማጣት ከባድ ነው ያሉት ዶ/ር ወርቅነህ ሰላም እንዲሆን የሁለቱ አገሮች ህዝቦች፣ የሃይማኖት መሪዎችና የአገር ሽማግሌዎች ትልቅ ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የውዝግቡ መፍታት ፋይዳው ከሁለቱ አገሮች አልፎ ለቀጠናው ሰላም ወሳኝ ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተለይም ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኤርትራው መሪ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የድንበር ውዝግቡ በፍቅር እንዲፈታ ላደረጉት ጥረት ዕውቅና እና የዓለም አቀፍ የሰላም ሽልማት ሊሰጣቸው ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አስመራ በገቡበት ወቅት በኤርትራውያን ዘንድ ያለምንም ቀስቃሽ የነበረውን ከልብ የመነጨ አቀባበል እና የመናፈቅ ስሜት ልብ የሚነካ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ በአፍሪካ ቀንድ ልማት እና መረጋጋት ከሌሎች የአከባቢው አገሮች ጋር ተቀናጅተው ለመስራት እንዲሁም፣ ኢጋድን ለማጠናከር መሪዎቹ ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቶቹን ወደ ዝርዝር ተግባር ለማድረግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ የሚመራ ኮምሽን ለማቋቋምም ከመግባባት ተደርሷል፡፡

በክብር ዶ/ር አብይ የተመራ ልዑካን በአስመራ ያደረገውን ታሪካዊ ጉብኝት አጠናቆ ዛሬ እኩለቀን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy