Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የክብር ዶክትሬት ሊሰጣቸው ነው፡፡

0 415

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሀረማያ ዪኒቨርሲቲ ለሁለት ታዋቂ ሰዎች የክብር ዶክትሬት ሊሰጥ መሆኑን ገለጸ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለመሃመድ አህመድ ቆጴ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት መረጃ ሰጥቷል፡፡
መሃመድ አህመድ ቆጴ የመጀመሪያው የኦሮምኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ ሆነው በሃረር ከተማ ይሰሩ እንደነበረም ከዩኒቨርሲቲው ካገኘነው መረጃ አረጋግጠናል፡፡

ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት ለሁለት ሰዎች ብቻ ነው የክብር ዶክትሬት የሰጠዉ፡፡ በማሽላ ላይ ታዋቂ ተመራማሪ እና የምግብ እና የእርሻ ድርጅት/FAO/ አማካሪው ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጄታ እና የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ናቸዉ በዩኒቨርሲቲው የእስካሁን ታሪክ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸዉ፡፡

ሀረማያ ዪኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ከ 7900 በላይ ተማሪዎች ሐምሌ 07/2010 ዓ.ም እንደሚያስመርቅ ታዉቋል፡፡ በዕለቱም ለርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው እና ለመሃመድ አህመድ ቆጴ የክብር ዶክትሬት ይሰጣቸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አስማማዉ በቀለ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy