Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በጀትና የሀገር ልማት

0 666

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በጀትና የሀገር ልማት

                                                           ሞገስ ፀ

በጀት ለአንድ ሀገር የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ መንግስት ደግሞ በጀት የሚበጅተው ንቁና ቀልጣፋ ግብር ከፋይ ዜጎች ሲኖሩት ነው፡፡ ሀገርም የምታድገው ከዜጎቿ በሚሰበሰበው ገቢ ነው፣ ጥሩ የግብር አሰባሰብ ባህል ካለ መንግስት በቂ  የሆነ በጀት ይበጅታል፡፡ ይህ በየአመቱ ሀምሌ 1ቀን የሚበጀት በጀት በአግባቡ ለታቀደለትና ለታለመለት አላማ በማዋል የሀገሪቱን እድገት ማፋጠን ይኖርታል፡፡ በጀትን ለታለመለት አላማና በግዜው መጠቀም ካልቻልን የህዝቦችን ችግር መፍታ አይቻልም፣ ይህ ደግሞ ህዝብን በመንግስት ላይ ቅሬታና ሮሮ እንዲያነሱ ምክንያት ይሆናል፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ ዉሃ፣ መብራት፣ መንገድ፣ ያለ መሰረታዊ የህዝቦች ፍጆታ የተመደበላቸውን በጀት ተጠቅመው በውቅቱ የህዝብ አገልግሎት መስጠት ካልቻሉ ለኢኮኖሚው እንቅስቃሴ እንቅፋት ከመሆን አልፈው ህዝብን ከመንግስት ያጋጫሉ፡፡ ነገር ግን በእኛ ሀገር ሁኔታ እየተስተዋለ ያለው ሁኔታ በበጀት ዓመት መጨረሻ ለመስራት የታቀዱ ስራዎች ሳይሰሩ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ተመላሽ ሲሆን ማየት ተለመደ ነው፡፡ ይህ አይነት ተግባር ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች ስላሉት መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አለበት፡፡

የዘንድሮው የ2010/2011 በጀት ዓመት 346 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀድቋል፡፡ ይህ በጀት ቀላል የሚባል አይደለም፣ ደግሞም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች ከፍተኛ ገንዘብ ነው፡፡ መንግስት በ2011ዓ.ም  ከያዘው በጀት ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው ድህነት ቅነሳ ላይ ለሚያተኩር ፕሮግራሞች እንደሚውል ታውቋል ፡፡ እንዲሁም ከጠቅላላው በጀት 55 በመቶ የካፒታል በጀት 45 በመቶ ደግሞ መደበኛ ወጭ ላይ እንደሚውል ታውቋል ፣ ይህም ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች አንፃር ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በቀጣዩ አመት ኢኮኖሚው ከማሳደግ አነፃር በተለይ በማዕድን ልማት፣ አበባ ልማት፣ በቱሪዝም እና በውጭ ንግድና ሌሎችም ዘርፎች ትኩረት ይደረጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኮንትሮባንድ ንግድን መቆጣጠር እና የገቢ አሰባሰብን ማስተካከሉም ትኩረት እንደሚደረግበት ተገልጧል ፡፡ በተለይ ደግሞ ግብር መክፈል ለሀገር ጥቅም መሆኑን አውቆ ያለማንም አስገዳጅነት ሁሉም ዜጋ መክፈል ይኖርበታል፣ መንግስትም ህብረተሰቡ በማስተማር ግብር አሰባሰቡን ቀልጣፋና ዘመናዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በቀጣይ ኣመት አዲስ የሚጀመር የልማት ፕሮጀክት የለም ያሉት ዶክተር አብይ አሁን የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን  ዶላር ይስፈልጋል ብለዋል፡፡ የታክስ ስርአቱን ማሻሻል እና ማዘመን፣ ወጪ መቀነስ፣ የመንግስት ተቀማጭ ገንዘብን ማሳደግ እንዲሁም ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጉዳይ ውስጥ ስራዎች ናቸው ብለዋል፡፡

የሀገር እድገትና ግብር ከፋይ ዜጎች ማለት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ዜጎች ይህንን በመረዳት በግዜውና ተገቢውን ግብር ለመንግስት በማስገባት ለሀገራቸው እድገት የበኩላቸውን ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል፡፡ ግብር ከፋይ ዜጎች ያሉባት ሀገር ቀጣይነት ያለውና ጠንካራ ኢኮኖሚ ይኖራታል፣ በአጭር ግዜ ውስጥ ፈጣን የሆነ ዕድገት ማስመዝገብ ትችላለችል፡፡ መንግስትም ግብር መሰብስብ ብቻ ሳይሆን የተሰበሰበውን ግብር ከሙስና በፀዳ መልኩ ለታሰበለት አላማ እንዲውል ማድረግ አለበት፡፡ ለሀገር እድገት ተብሎ የተበጀተ በጀት የት እንደደረሰ ህብረተሰቡም መንግስትን መጠየቅ ይኖርበታል፣ መንግስትም ለህብረተሰቡ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች በጀት የሚበጀተው ከውጭ ሀገርና ከሀገር ውስጥ በሚገኝ ብድርና ከዜጎች በሚሰበሰብ ግብር ነው፣ ስለሆነም ይህንን በመገንዘብ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግብር በግዜው ለመንግስት መክፈል ይኖርበታል፡፡ ግብር ሳይከፍሉ መንግስትን መሰረተ ልማት እንዲያሟላ መጠየቅም ሆነ ሀገር እንድታድግ መፈለግ ፈጽሞ ተገቢና ሊሆን ይማይችል ጉዳይ ነው፡፡ የበጀት አላማ የህዝቡን ገንዘብ ባግባቡ ከውጭና ከውስጥ የሚገኘውን እርዳና ብድር በአግባቡ በማስተዳደር ለህዝብ ጥቅም የሚውል የእድገት መሰረት የሆኑ ልማቶችን ሰርቶ ማቅረብ ነው፡፡ የግብርና፣ መብራ፣ ጤና፣ የኢነዱስትሪ፣ የአውራ መንገዶች ባቡር፣ ትምህርት፣ መገናኛ ስልክ የሚስፋፋው በበጀት ነው፡፡ ለበጀት ክብር እንስጥ፣ በጀት መንግስት ለህዝብ ጥቅም የሚሰራበት እንጅ ለራሱ የሚጠቀምበት ወይም ለግሉ የሚወስደው ገንዘብ አይደለም፡፡ ‹‹የመንግስት ነው ምን አባቱ›› በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በትን በየሰበቡ አስባቡ ማባከን የዜግነት መገለጫ አይደለም፣ ለሀገርም ጉዳት ነው፡፡

የዘንድሮ አመት በጀት የሚያተኩረው በደህንነት ቅነሳ ላይ ነው፣ ማለትም ትምህርት፣ ጤና፣ መንገድ በመሳሰሉት የሚያተኩር ነው የሚሆነው፡፡ የበጀቱ አብዛኛው ድርሻ ደህንነት ቅነሳ ላይ ማተኮሩ ያለው ጠቀሜታ ዜጎች ካጠቃላይ ከሀገር ሀብት የመጠቀም መብታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል አንድ መንገድ ነው፡፡ ትኩረቱ አብዛኛው ህዝብ የሚገለገልባቸውና የሚጠቀምባቸው ሴክተሮች ላይ ያተኮረ የበጀት ድልድል ነው፡፡ ይህንን ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ሰናመዛዝነው ከፍተኛ ለደህንነት ቅነሳ ተብሎ የተበጀተ በጀት 40% ነው፣  ሰብሰሀራ 35% አካባቢ ይጠጋል፡፡ በዘንድሮው የበጀት አመት ኢትዮጵያ ለደህንነት ቅነሳ ተብሎ የጠበጀተው በጅት እጥፍ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ደግሞ የሀገሪቱን እድገት ለማረጋገጥና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳለጥ እድል ይሰጣል፡፡ ይህ 55% ማለት አዳዲስ ስራዎች ወይም ተጀምረው ያላለቁ ስራዎችን ለመጨረስ የምነጠቀምበትና ሙሉ በሙሉ መንግስት ስራውን ለማስኬድ የሚውል ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ፍትሀዊ የሆነ የበጀት ድልድል የተደረገ መሆኑንና ከደህንነት አዘቅት ለመውጣት የሚደረገውን ጉዞ የሚያፋጥን ነው፣ እንዲሁም  የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ከፍ ለማደረግ የሚያግዝ የበጀት ድልድል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ዘንድሮ ለማደግ ከ9%-10% የታቀደውን እቅድ ከግቡ ለማድረስ ይጠቅማል፡፡ የተሟላ ለውጥና መሻሻል ለማንጣት ግዜ የሚዎስድ ቢሆንም በነበረው ግዜ ውስጥ ትኩረት ሰጥቶ በወቅቱ መጠቀምና በጀቱንም በአግባ መጠቀም ተከታታይ ለውጥ ይመጣል፣ የበጀት ብክነትም አይኖርም፡፡

ነገር ግን ትኩረት ሊባል የሚገባው ይህ የተበጀተው በጀት የመንግስትን ፍላጎት ሚያሳይ ነው፡፡ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድርግ በየደረጃው ያሉ ሃላፊወች ግዴታና ሀላፊነት ነው፡፡ ይህ በጀት በተበጀተው መሰረት ያልዋለ እንደሆነ ያሰብነውን የደህንነት ቅነሳ በተሟላ መንገድ ላይሳካ ይችላል፡፡ እንዲሁም የአሰራርና አስተሳሰብ ለውጦች ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ የ2011 አመት በጀት ከ2010 ዓመት በጀት ጋር ሲነፃጸር 3.6 በሞቶ ብቻ እድገት አሳይቷ፡፡ ይህ የሆነበት  ምክንያት ደግሞ መንግስት በተሻለ መልኩ የግብር አሰባሰብ ስርአትን ባለማሳደጉ ነው፣ በ2010 የበጀት ዓመት መንግስት ለማግኘት ካቀደው የግብር ገቢ ወደ 50 ቢሊዮን ብር በላይ ሳይሰበሰብ ቀርቷል፡፡ ይህም ሁኔታ በመንግስት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ በማድረግ የልማት ፕሮጀክት ስራዎች ወደ ቀጣይ በጀት ዓመት እነዲሸጋገሩ በማድረግ የበጀት ጫና መፍጠር ከመሆኑም በላይ ለህብረተሰቡ መድረስ ያለባቸው የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልገሎቶች እየተጓተተ እነዲሄድ ምክንያት ሁኗል፡፡ በተለይ ደግሞ ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ የምታደርገውን ግስጋሴ አጠናክሮ ለማስቀጠል ታማኝና ቀልጣፋ ግብር ከፋይ ዜጋ ያስፈልጋታል፡፡ በመሆኑም የታክስ አሰባሰቡ በመንግስትና በህብረተሰቡ ከፍተኛ ትኩረት ማግኘት ያለበት አጀንዳ ነው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy