Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አንድ መቶ የዲፕሎማሲና የስኬት ንጋቶች

0 402

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አንድ መቶ የዲፕሎማሲና የስኬት ንጋቶች

እቴጌ ዳጊ

በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር እየተከወነ ያለው ሁሉ ከቃል አቅምና ተሰጥኦ በላይ ነው፡፡  ሕዝብን እንደ ሂሳብ ስሌት ደምረው… ደምረው በደስታ እምባ ያራጩት ሰው፣ ብሔር የሚለው ቃል ሊመጣ የሚገባው “ኢትዮጵያ” ከሚለው ቃል በኋላ ነው፤ “ኢትዮጵያ” የምትባለውን አገር ከፍ ማድረግ የሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው፤ ብለው የነገሩን ሰው ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብለው ከተሾሙ መቶ ቀናት ሞላቸው::

በጣም የሚገርመው ነገር  ደግሞ “መደመር” የሚለውን ቃል ጭርሱን ልክ እንደ መፅሃፍ ቅዱስ ቃል ሁሉም ሰው በልቡ ማንገሱ ነበር:: ይባስ ብሎም የውስጥ ጥያቄው ምላሽ ያለው በኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንደሆነ ተረድቷል:: የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ እንደ ብሄራዊ መዝሙር ሲዘመር ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች መካከል ዘላቂ  ሠላም እንዲሰፍን አገሮች በምጣኔ ሀብታዊ ጥቅም እንዲተሳሰሩ ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን አከናውነዋል።  የኢትዮጵያን የወደብ አገልግሎት ለማስፋትና የወደብ አማራጮች ለማብዛት ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

ምን ይህ ብቻ! “ሞት አልባ ጦርነት” የነበረው የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ወደ መቀራረብና መደጋገፍ  የሚያሸጋግር ግንኙነት ለመፍጠር ጉዞ ተጀምሯል። ከሁለቱ ህዝቦችም እጅግ የላቀ ተቀባይነት በማግኘቱ ሌላው ለመንግስታቱ ተጨማሪ የብርታት ስንቅና የቤት ሥራ የሰጠ ነው፡፡ የደቡብ ሱዳን መንግሥትና የተቀናቃኙ ቡድን ድርድርም ፈር ይዟል። በህዳሴው ግድብ ግንባታ ዙሪያ ከግብፅ ጋር የነበረውን ፍጥጫ ወደ መተማመን እንዲሸጋገር የተደረገው ጥረት የሚያበረታታ ሆኗል።   

ከነዚህ ዲፕሎማሲያዊ ድሎችም ባሻገር የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት የገጠመውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እፎይታ እንዲያገኝ እስካሁን ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቀጥታ ወደ ብሔራዊ ባንክ ማስገባት ተችሏል።

እነዚህ መቶ ቀናት የመቶ አመታት ያህል የተለጠቱ ይመስል ህስቡ በየንጋቱ አዳዲስ ተስፋ ሰጪ ተግባራትን እየተመለከተ የሄው ባለፉት መቶ ቀናት ውስጥ በርካታ የፖለቲካ እሥረኞች ነፃ ወጥተዋል። በውጭ አገራት በእሥር ይማቅቁ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተፈትተዋል።_በሽብርተኝነት የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶችና አመራሮች ከሽብርተኝነት መዝገብ በመሰረዛቸውና የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት መንግስተ ባሳየው ፍላጎት መሰረት በውጭ አገር ሆነው ይንቀሳቀሱ የነበሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና መሪዎቻቸው ወደአገር ቤት እንዲገቡ ተፈቅዷ፤ በርካቶችም ገብተዋል፡፡ አፋኝ አዋጆች ናቸው እየተባሉ መንግሥትን ሲያስተቹ የነበሩ ህጎችን ለመሻሻል የሚሰራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት እያደረገ ይገኛል፡፡

ሚዲያዎች አንፃራዊ ነፃነት አግኝተዋል፡፡ በውጭ ሀገር ተወስነው የነበሩ የሚዲያ ተቋማት ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ ተፈቅዷል፡፡ ተዘግተው የነበሩ ዌብሳይቶች ተከፍተዋል፡፡
የምህረት አዋጅ መውጣቱና ተግበራዊ እየተደረገ መሆኑበሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ በርካታ ዜጎችን እፎይታ የሰጠ ጉዳይ ነው፡፡

ህዝብን ያሳድዱ የነበሩ የደህንነትና የመከላከያ አዛዦች ከስልጣን ተነስተዋል፡፡
የሀገር አንድነትን የሚመለከቱ፣ ኢትዮጵያዊነትን ከፍ የሚያደርጉ ንግግሮች በሀገር መሪ ደረጃ ከዓመታት በኋላ በተደጋጋሚ አድምጠናል፡፡ የፍቅር እና የሰላም አስፈላጊነት በሰፊው ተሰብኳል፡፡

ለስድስት ወር ተጥሎ የነበረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከማብቂያ ጊዜው ቀድሞ ከመነሳቱ ማግስት ጀምሮ ህዝቡ አስተሳሰቡን ያለምንም ገደብ እንዲያንፀባርቅ እድሎች ተፈጥረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የተፈፀመው በአንድ መቶ ቀናት ውስጥ ነው፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy