Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ በዝምቧብዌ ምርጫ የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን እንዲመሩ ተመረጡ

0 503

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርም ደሳለኝ በዝምቧብዌ በሚካሄደው ምርጫ የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን እንዲመሩ ተመረጡ።

የዝንቧብዌ መንግስት ከጥቂት ወራት በፊት ዘንድሮ የሚካሔደውን ምርጫ እንዲታዘቡ የአውሮፓና የአፍሪካ ሕህረትን ጨምሮ የመንግስታቱ ድርጅትን የልኡካን ቡድን እንዲታዘቡ ጋብዘው ነበር።

በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ሁለት ቡድን ያለው የታዛቢዎች አካላት የአገሪቱን ምርጫ እንዲታዘብ የወሰነ ሲሆን፥ አንዱን ቡድን የመምራት ስራ ለቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ ሕብረቱ መመረጣቸው ተገልጿል።

ህብረቱ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ምርጫውን የሚታዘበውን የልዑካን ቡድን እንዲመሩ ያደረጉት በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በነበራቸው ተሳትፎ ነው።

አቶ ኃይለማርያም በዚሁ መሰረትም ከ10 ቀን በኋላ ወደ ሀረሬ እንደሚያመሩም ተጠቁሟል።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በሀገራታቸው ብሎም በአህጉሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የዴሞክራሲ ስርአትን ለመገንባትና በተለያዩ አለማቀፍና አሕጉር አቀፍ መስሪያ ቤቶች ውስጥ ባደረጉት ተሳትፎ እንደተመረጡ ተጠቁሟል።

ከዚህ ውስጥም አቶ ኃለማርያም ደሳለኝ የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና ፀጥታ፣የኔፓድና የሕብረቱ ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy