Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፍጠር የሀገሪቱን እድገት መግታት አይቻልም!!

0 682

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢኮኖሚያዊ አሻጥር በመፍጠር የሀገሪቱን እድገት መግታት አይቻልም!!

ሞገስ ፀ

ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ በሁሉም የኢኮኖሚ  መስክ ጥሩ የሚባል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች፡፡ ነገር ግን ይህንን እንቅስቃሴ ለመግታት ሳይታክቱ የሚሰሩ ነጋዴዎችና የተወሰኑ የመንግስት አመራሮች አልጠፉም፡፡ ባለፉት ሦስት አመታት ውስጥ ሲስተዋሉ ለነበሩ ችግሮችም እንደምክንያትነት የሚቆጠረው በመሰረታዊ የሸቀጣ ሸቀጥ ፍጆታዎች ላይ ያለአግባብ የዋጋ መናር አንዱ ነው፡፡

ለአብነትም እንደ ስኳር፣ ዘይትና ነዳጅ የመሳሰሉት ፍጆታዎች ላይ ቋሚ የሆነ ተመን አልነበረም፡፡ ነጋዴዎች ከመንግስት አመራሮች ጋር በመመሳጠር ህዝቡን ለከፋ ችግርና ፍዳ ሲዳርጉት ቆይተዋል፡፡ ህዝቦች መንግስትን በቅሬታ አይን እንዲመለከቱትና ህዝብና መንግስት በአይነ ቁራኛ እንዲተያዩ ማድረግ አላማቸው አድርገው ሲነቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡

በአጭር ጊዜ ውስጥ መበልፀግን አላማ አድርገው የተነሱ ህገወጥ ነጋዴዎችና የመንግስት አመራሮች ይህን እኩይ ተግባር የሚፈፅሙት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት በማቀጨጭ ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም በማሰብ ነው፡፡ እንዲሁም ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ ወደ አልተገባ ግጭትና እልቂት ለመውሰድ ያለመ ነው፡፡ ይህንን ተግባራችውን ለማሳካት  እንደ መሳሪያ የተጠቀሙት ደግሞ ሸቀጦችን ደብቆ ህዝቡ በሚፈልገው ጊዜ እንዳያገኝ ማድረግ ነው። ዓላማውም ህዝቡን ላልተፈለገ ወጭ በመዳረግ በመንግስት ላይ ማነሳሳት ነው፡፡ ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎችም ህገወጥ የሆነ የገበያ ስርአትን በመከተል መንግስት ማግኘት ያለበትን ጥቅም በማሳጣት የሃገሪቱን እድገት ወደኋላ የሚጎትቱ ናቸው፡፡

ነገር ግን መንግስት ጥብቅና ጥልቅ ክትትል በማድረግ በህግ ተጠያቂ እያደረገ ይገኛል፤ ህብረተሰቡም እንደዚህ አይነት ነጋዳዴዎችን በአንክሮ በመከታተል ማጋለጥና ፍትሀዊ የሆነ የገበያ ስርአት እንዲኖር የበኩሉን ሚና መጫዎት ይኖርበታል፡፡

ህገወጥ ነጋዴዎችን ለመከላከል መንግስት ብቻውን አመርቂ ውጤት ማምጣት አይችልም፡፡ ሰፊው የህብረተሰብ ክፍል ከመንግስት ጎን በመቆም ከቻለ ግን ህገወጥ ነጋዴዎችን በማጋለጥ ጤናማ የገበያ ስርዓትን መገንባት ይቻላል። በተለይ ደግሞ ህዝቡ መብቱን ከመጠበቅ አንፃር ማንኛውንም አይነት ሸቀጥ ከተተመነበት ዋጋ በላይ መግዛት የለበትም፤ ህገወጥ ነጋዴዎች የራሳቸውን ጥቅም በማሰብ የእቃዎች እጥረት ሊከሰት ይችላል በማለት ህብረተሰቡን በማወዳደር የሸቀጦች ዋጋ እንዲንር ያደርጋሉ፡፡

መንግስት የህብረተሰቡን ችግር በመገንዝብ  በቂ ነው ብሎ ያሰበውን ሸቀጥ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ህብረተሰቡ ስጋት ውስጥ እንደገባ በማድረግ ግጭት ከሚቀሰቅሱ ሃይሎች መጠንቀቅ ኖርበታል፡፡ መንግስትም ህግን ተከትለው በማይሰሩ ነጋዴዎች ላይ ተከታትሎ ቅጣት ሊወስድ የገባል። እነዚህ ሴረኞች ጊዜአዊ የሆነ መደናገጥን ከመፍጠር የዘለለ አቅም የላቸውምና ኢኮኖሚያዊ ሻጥርን በመፍጠር የህዝብን የለውጥ ፍላጎት መግታት አይችሉም።

እድገት የሚመጣው ሁሉም ህብረተሰብ በመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ  በጥብቅ ታሳስሮና ተቆራኘቶ ሲሆን ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የህብረተሰባችን ክፍል ከመንግስት ጎን በመቆም እድገትን ማፋጠን ይኖርበታል፡፡ አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንዲፈጠር እያንዳንዱ ማህበረሰብ በአንድ አይነት ኢኮኖሚ፣ የገንዘብ ፖሊሲ፣ በመሰረታዊ የኢኮኖሚ ህጎችና በመሰረታዊ የልማት ስትራቴጂዎች መመራት አለበት፡፡

ከሸቀጦች ክፍፍል አንፃር በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍል እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መንግስት በመከታተል መፍትሄ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሸቀጦች ከቦታ ቦታ ተደራሽነታቸው ፍትሀዊነት አይታይበትም፡፡ ይህ ደግሞ እኩል ግብር ከሚከፍል የህብረተሰብ ክፍል አንፃር ሲታይ አግባብነት ይጎድለዋል፡፡ ይሸቀጦችን ወደ አንድ አካባቢይ ብቻ በማከማቸት ግማሹ በውድም ቢሆን ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ ሲኖር ሌላው ደግሞ የፈለገውን ሸቀጥ በፈለገው ጊዜ የማያገኝበት ሁኔታዎችም ይታያሉ። ይህ ተግባር ደግሞ ለሀገሪቱ እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል፡፡

የሚፈጠሩ የግል ባለሃብቶቻችንም ጤናማና ህግመንግስቱን ተከትለወ መወዳደርና ተገቢዉን ገቢ ለመንግስት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በአለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ሸቀጦችን እያመረቱ ትርፍ በማግኘት እራሳቸውን ጠቅመው ህዝቡንና አገሪቱን የሚጠቅሙ ልማታዊ ባለሀብቶችን በሰፊው ማንቀሳቀስ መቻል አለብን፡፡ የግል ባለሃብቶችን በአገሪቱ በሰፊው እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ያገራችን አካባቢዎች ሊያስመዘግቡ የሚችሉትን የላቀ ልማት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ አይቻልም፡፡ ሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የግል ባለሀብቱን በብቃት ለማስተናገድ፣ ለመደገፍና በሰፊው በስራ ላይ ለማሰማራት የሚያስችላቸው ሁኔታ መፈጠር አለበት።

በልማት ስራ ላይ የሚሰማራውን ባለሀብት በሰፊው ከማንቀሳቀስ ውጭ ፈጣን ልማት ማረጋገጥና ሁሉም የአገራችን አካባቢዎች ከልማቱ የመጠቀም እኩል እድል እንዲኖራቸው ማድረግ በፍፁም የማይታሰብ መሆኑን ያህል በጥገኝነት የተሰማሩትን መቆጣጠርም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ይሆናል፡፡ በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ሸቀጥ ወይም አገልግሎት ሲያቀርቡ በመንግስትና በህዝብ ጫንቃ ላይ በመታዘል፣ በማጭበርበርና በመሳሰሉት ህገ- ወጥ መንገዶች ለመክበር የሚሹ ወገኖች ከልማት ይልቅ ድህነትና ጥፋትን የሚያስፋፉ በመሆናቸው መገታት ይኖርባቸዋል፡፡ የግል ባለሀብቶች በሰፊው እንዲሰማሩ፣ መደገፍና ማስተናገድ ያስፈልጋል ሲባል ልማታዊ ባለሃቱን እንጂ ጥገኛዉን አይደለም፡፡

ፖሊ-ጂሲኤል  የተባለው የቻይና ኩባንያ ላለፉት ጥቂት አመታት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ላይ በድፍድፍ ጋዝ ላይ የፍለጋ ስራ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፖሊ-ጂሲኤል ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በተለይ ደግሞ የተፈጥሮ ጋዝን በተመለከተ አመርቂ ውጤት አስገኝቷል፡፡ በምስራቅ ኢትዮጵያ የአገሪ ክፍል ተገኘ የተባለው ነዳጅ በቀጥታ ቱቦ ወደ ጅቡቲ በመዘርጋ ወደ ቻይና ለኤክስፖርት  የሚቀርብበት ሁኔታ እንዳለ ተገልጧል፡፡ ይህም እውነት ይሆን ዘንድ ከጅቡቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ወይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም መሰረት ቱቦው በሁለት አመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው የሚሆነው፡፡ ይህ ሁሉ እቅድ እውን ከሆነ በኋላ በአመት ከ1ቢሊዮን ዶላር ብር በላይ የገቢ ምንጭ የምናገኝበት ሁኔታ ነው የሚኖረው፡፡ ይህ ደግሞ ለሀገራችን ከፈተኛ የሆነ የእድገት ምንጭ ነው፡፡

ይህ ሲባል ግን የተፈጥሮ ጋዝና ድፍድፍ ነዳጂ ለሀገራችን አፋጣኘ የሆነ የኢኮኖሚ ችግርን ይፈታል ወይም ባጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ለሀገራችን ያስገኛል ማለት አይደለም፡፡ ይህ የተፈጥሮ ጋዝ በሀገራችን መገኘቱ ምንም እንኳን ከፍተኛ የሆነ እድገት እንደሚያመጣ ቢታመንም፣ በአጭር ጊዜ ግን እውን ይሆናል ብሎ መጠበቅ ተገቢነት አይኖረውም፡፡ እንደሚታወቀው የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መሰረት የግብርናው ዘርፍ ነው፡፡ ከ85% በላይ የሆነው የሀገራችን የህብረተሰብ ክፍል አርሶ አደር በመሆኑ፣ የሀገራችን የኢኮኖሚ ዋልታም ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ የተከተለች ያለችው ግብርና መር ኢኮኖሚ ነው፡፡ የተፈጥሮ ጋዝ መገኘቱ ከረጂም እርቀት አንፃር ከሌሎች ሴክተሮች ጀርባ በመሆን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ነው የሚሆነው፣ ነገረ ግን ገና ብዙ ስራዎችን መስራ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በነዳጅ ተገኘቷ ስም ካሁኑ የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዝ ነዳጁን እንደመሪ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምንጭ አድረገው ማሰብ ጀምረዋል፡፡ የተገኘው ድፍድፍ ነዳጅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጨባጭ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ብዙም ድርሻ አይኖረውም፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች መንግስትንና የህዝብን በጋራ ሰርቶ የመለውጥ ራዕያቸውን ዕውን እንዳይሆንና በጋራ ለሀገራቸው እንዳይቆሙ በማድረግ ሌት ተቀን የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በተለይ ደግሞ ሀገሪቱ የተፈጥሮ ነዳጅ ጋዝ ባለቤት ሁናለች በማለት ህዝብን ከሀገሪቱ አቅም በላይ ተስፋ እንዲሰንቅ እና እንዲጠብቁ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ የኋላ ኋላ ህዝቡን በመንግስት ላይ በማነሳሳት የሀገሪቱን እድገትና በአንድነት የመኖርን ተስፋን የሚያጨልም ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን የተሳሳተ የህልም እንጀራ ከማለም መታቀብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የተፈጥሮ ጋዝ መኖሩ ከመረጋገጡ ዉጭ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የተፈጥሮ ጋዝን ለሀብት ምንጭነት አልተጠቀመችም፡፡

ዜጎች ሁሉም ነገር በመንግስት እንዲደረግላቸው ጠባቂ መሆን የለባቸውም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከዚሁ ጋር የሰጡት ማሳሰቢያ በዚሁ ዙሪያ ሊታዩ የሚችሉ ሥጋቶችን ያመለከተ ነው፡፡ እሳቸው በዚህ ንግግራቸው ነዳጅ ተጨማሪ ሀብት መሆኑን አመልክተው፣ ከዝህ ውጭ ያሉት እንደ ግብርባ፣ ኢነዱሰተሪና ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን ማመልከታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ሀሳብ ያነሱት በሌሎች ሀገራት ከታየው የጠባቂነት አስተሳሰብ በመነሳት ነው፡፡

የተገኘው ድፍድፍ ነዳጅ ከረጂም ጊዜ አኳያ ተስፋ ሰጪ ይሆን እንደሆነ እንጂ አሁን ለሚስተዋለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት መፍትሔ አይሰጥም፡፡ ስለዚህም የግብርናውን፣ የቱሪዝሙንና የኢነዱስትሪውን መስክ በማዘመን ወደ መካከለኛ ገቢ ሀገራት ተርታ ለመሰልፍ የምናደርገውን ግስጋሴ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy