Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሕግን የማስከበር ኃላፊነት…!

0 467

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሕግን የማስከበር ኃላፊነት…!

 

በነጻነት አምሃ

 

በኢትዮጵያ  ዘመን የማይሽራቸው እሴቶች እንዳሉ ያደባባይ  ምስጢር ነው። ከእነዚህ እሴቶች መካከልም በዋናነት የሚጠቀሰው የሃይማኖቶች መቻቻልና አብሮነት ነው፡፡ የሁሉም ሃይማኖቶች ምእመናን ልዩነት ሳይፈጥሩ በመዋደድ፤ በመከባበርና በአብሮነት ለዘመናት ዘልቀዋል፡፡ ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ መሸራረፍ ያልታየበት አኩሪ ታሪክ ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል በዋናነት የሚጠቀስ ነው።

 

ይህ ደግሞ እኛ ኢትዮጵያዊያን በራሳችን የሚንናገረው ብቻ ሳይሆን የዓለም ሕዝብ የመሰከረው እንደሆነ  እሙን ነው፡፡ የዓለም ህብረተሰብ ይህንን ከመመስከርም አልፎ በያዝነው የበጀት ዓመት አገራችን ለኃይማኖቶች መቻቻልና መከባበር  እንደዚሁም ለፈጠረችው የሰላምና አብሮ የመኖር እሴት ከአፍሪካ የተባበሩት የኃይማኖት ኢንሼቲቭ ሽልማት እንደተበረከተላት ይታወቃል።

 

ሃይማኖታዊ መተሳሰርና መከባበር በአገሪቱ ሰላምና ፍትህ እንዲሰፍን አንድነት እንዲጠናከር ቁልፍ አስተዋጵኦ አድርጓል አሁንም ይህንኑ አጠናክሮ ቀጥሏል። የሃይማኖት አባቶች ግጭቶችን ለማጥፋትና አገራችን ወደ ሰላምና አንድነት እንድትመጣ የሚያስችል ተግባር በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

 

በአገራችን ለዘመናት ዘለቀውና በመከባበር ላይ የተመሠረተ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያስቻለው የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር አንዱ እሴታችን ሆኖ ቀጥሏለወል። አገራችን  ከጥንት ጀምሮ የኃይማኖት ነፃነትና እኩልነት የሰፈነባት ሃገረ ሰላም ሃገረ ፍቅር በመሆኗ ለልሎች አገራት ህዝቦች አርአያ በመሆን ስትጠቀስ ኖራለች፡፡

 

አሁን ደግሞ የበለጠ መጠናከር ተፈጥሯል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል የነበረውን መከፋፈል እንደዚሁም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማኞች ዘንድ ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባት እንዲፈታ በማድረጋቸው እስካሁን የነበረውን አንድነትና መቻቻል የበለጠ በማጠናከር አገራችንን ለማልማትና ሰላሟን ለማስጠበቅ የህዘቧን ብልጠን ከፍተኛ አስተዋጽ እንዳለው ማንም የማይክደው ሃቅ ነው፡፡

 

የሃይማኖት አንድነትና መቻቻል በአገራችን አብሮ የመኖሩ ባህል የበለጠ እንዲጎለብት አስችሏልሃ,። በአገራችን በየትኛውም የእምነት ተቋም ሰላምና አንድነትን። ምእመናንም ይህንን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ በቅርብ ጊዜ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በቤተክሪስቲያኖች ላይ የተፈጸመው ውድመትና በአማኞች ላይ የደረሰው ጉዳት የሶማሌን ህዝብ የማይወክልና በተወሰኑ የጥፋት ሃይሎች የተቀነባበረ መሆኑን በተለያየ መልክ እየተገለጸ  ይገኛል፡፡

 

ከዚሁ ጋር ተያይዞና በሌሎች አካባቢዎችም ጭምር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያለው ሰዎችን በማንነታቸው የመግደልና የማፈናቀል ተግባራት ሌላ አጀንዳ ባላቸው የአገራችንን ሰላም ማደፍረስ በሚሹ ወገኖች የተቀነባበረ ለመሆኑ አያጠያይቅም፡፡ መንግስት በአሁኑ ወቅት በአገራችን ይቅር ባይ መሆንና መቻቻል ሰላማዊ ግንኙነት እንደሚያሰፍንና አንድነትን  እንደሚያጠናክር በመገንዘብ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ ይገኛል፡፡

 

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በሀገራችን ተቻችሎ ከመኖር ይልቅ የተለያዩ ችግሮችን መፍጠር እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ሰዎችን በኃይማኖታቸው፤ በዘራቸው ወይም በጎሳቸው መጥላት፣ ብሔራዊ ስሜት ማጣት፣ ወገናዊነትና የኃይማኖት ጽንፈኝነት የመሳሰሉ ተግባራት ሲንጸበረቁና ሲተገበሩ ይታያል።

 

ከግጭት የሚገኝ ነገር የለም፡፡ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው እንኳ እርስ በርስ መቻቻልና በነፃ ይቅር መባባል እንዳለበት የክርስትና የእምነት መጽሐፍት አበክረው ያስረዳሉ። በክርስትናም በእስልምና እምነቶች በመቻቻልና በመከባበር ላይ የተመሠረቱ በርካታ አስተምህሮዎች አሉ።

 

በእስልምና ሃይማኖት በተለይ  የነብዩ መሐመድ የጦርነት ጊዜ ትዕዛዞች ተብለው ከተዘረዘሩት መካከል «ሕፃን አትግደሉ፣ አዛውንት አትግደሉ፣ ሴቶችን አትግደሉ፣ የእምነት ቦታዎችን አታፍርሱ፣ እጅ የሰጠን ሰው አትግደሉ፣ የኃይማኖት አባቶችን አትግደሉ፣ ወደ እምነት አታስገድዱ» የሚሉት አስተሳሰቦች ላነሳነው ርእሰ ጉዳይ አብነቶች ናቸው።

 

በሃገራችን ያሉ ሃይማኖቶች ለሠላም፣ ለልማት፣ ለአብሮነት፣ መልካም ዜጋ ለመቅረፅና ለሀገራዊ ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይህ አሁንም የበለጠ ማጠናከርን የተየቃል፡፡ በሀገራችን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥትና ኢትዮጵያ ተቀብላ የፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ መሠረታዊ የሰው ልጆች መብቶችና ነፃነቶችን የሚያስከብሩ ናቸው።

 

አሁን የምናያቸውን ለሕግ ያለመገዛት ዓይነት አፈንጋጭ አስተሳሰቦች መወገዝ አለባቸው፡፡ ኃይማኖትንና ብሔርን ሽፋን ያደረጉ ጥቃቶችን ሊያስተናግድ የሚችል ማህበረሰብ ሊኖረን ፈጽሞ አይገባም። ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ይዛው የዘለቀችውን የኃይማኖት መቻቻል አሁንም ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

 

በግጭትና እርስ በርስ ከመገዳደል የሚገኝ ትርፍ አይኖርም፡፡  በኢኮኖሚ የበለጸጉ አገራትም ሆኑ የዜጎቻቸውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ያልቻሉ ታዳጊ አገራት በግጭት አንዳችም ጠቃሚ ነገር አላገኙም፡ ፡

 

ቀደም ሲል በግጭት ውስጥ ከገቡ አገራት  መማር ይኖርብናል፡፡ አገር ሠላምና መረጋጋት ሲርቃት በስጋትና ጭንቀት ትወጠራለች፡፡ ዕድገትና መለወጥ የተስፋ ራዕይ ብቻ ሆነው ይዘልቃሉ፡፡ ሁሉ ነገር ሠላምና መረጋጋትን ስለሚሻ ልማት ብዙም ትኩረት አያገኝም፡፡ ሠርቼ እለወጣለሁ የሚል ዜጋ በአጭሩ ተስፋ ይቆርጣል፡ ፡

 

ልማትን በማፋጠን የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ዕድገትን ማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት ግጭትን ማስወገድና ሰላምን ማስፈን ተኪ የሌለው ተግባር ነው፡፡ ግጭት የዕድገት መሰናክል በመሆኑ ግጭትን ለማስወገድ መትጋት ይገባል፡፡  በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የታየው ዓይነት ግጭት በሌሎች አካባቢዎች እንዳይከሰት ብርቱ ጥረት ማድረግ ያሻል፡፡

 

በመሆኑም ለህይወትን ንብረት መውደም መጥፋትና አካል ምክንያትየሆኑ የግጭት መንስዔዎችን ማስወገድ ይገባል፡፡ በዚህ በኩል ሕዝቡ  ከፍተኛ ኃላፊነት አለበት፡፡ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው በህዝብ አንድነት ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ የግጭት ምዕራፍ መዘጋት ሲችል ነው፡፡  የግጭትን ምዕራፍ የመቋጨት ተግባር ደግሞ በዋናነት የሚሳካው በህዝብ ትግል ነው፡፡ ሁሉም ዜጋ ለግጭት መንስዔ ከሚሆኑ አካሄዶች፣ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች መታቀብ ይጠበቅበታል፡፡

መንግሥትም  ህግን የማስከበር ሃላፊነቱን በተገቢው መንገድ ሊወጣ ይገባል፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ ያሉ ግጭትን የሚያባበሱ ተግባራትን በመከታተልና ህዝቡን በማስተባበር   ግጭቶች ስር ሳይሰዱ እልባት እንዲያገኙ የማደረግ ተግባሩን በተገቢው መንገድ ሊያከናውን ይገባል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy