Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በመቀሌው አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ የተያዙት የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲመለሱ ተደረገ

0 529

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከሁለት ሳምንት በፊት ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፍቃድ ውጭ ገብተዋል ያላቸው አርባ አምስት የፌደራል ፖሊስ ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል አባላት ከመቀሌ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

አባላቱ በአሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የመጡበት አላማም እስኪታወቅ ድረስ እንቅስቃሴቸው ተገድቦበ በፌደራል ካምፕ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎ እንደነበር ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ባለመኖሩ የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል አስፈላጊ አለመሆኑን ተናግረዋል። ጨምረውም ክልሉ ድጋፍ የሚጠይቀው ከክልሉ አቅም በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥም ወይም በልዩ ሁኔታ ከተወሰነ መሆኑን ጠቅሰው “ሁለቱም ጉዳዮች እኛ ጋር የሉም” ብለዋል።

 

“ለተወሰኑ ቀናት የፌደራል ፖሊስ አባላት በካምፑ ውስጥ ቆይተዋል። ወደ ክልሉ የገቡበት መንገድ ችግር ነበረው። እኛ ባልጠየቅንበት እና በማናውቀው ጉዳይ ነው የመጡት” በማለት የፀረ-ሽብር ግብረ ኃይሉ ለምን መቀሌ እንደተገኘም ግልፅ እንዳልሆነም ተናግረዋል።

“ለምን እንደመጡ ከፌደራል መንግሥት ጋር መነጋገር ያስፈልግ ስለነበር ፤ ከፌደራል መንግሥት ጋር እስክንግባባ በቦታው እንዲቆዩ ተደርጓል። አሁን ደግሞ እዚህ መቆየታቸው የሚጨምረው ነገር ስለሌለ ወደመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ አድርገናል። “ብለዋል

ልዩ ፖሊስን ማን መሰረተው?

በወቅቱ የፌደራል ፖሊስና የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ረዳኢ ጉዳዩን መካዳቸው የሚታወስ ነው። የዚያ አይነት ምላሽ የተሰጠበት ምክንያት እንደነበረው አቶ ረዳኢ ይናገራሉ ።

“እውነት ነው ለተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተራ ወሬ ነው የሚል መልስ ስንሰጥ ቆይተናል። ምክንያቱም በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከእውነት የራቀ መረጃ እየተሰራጨ ስለነበርና፤ ለትግራይ ህዝብ እና ለትግራይ መንግስት ብሎም ለስርአቱ ስለማይጠቅም የሚሰሩ ስራዎች ተሰርተው ወቅቱን ጠብቆ በትክክለኛ ጊዜ መነገር ስለነበረበት ነው” ብለዋል።

የፌደራል ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል ከክልሉ መንግሥት ፍቃድ ውጭ መግባቱን አስመልክቶ ከፌደራል መንግሥት ጋር ቅራኔ ተፈጥሮ እንደሆነ አቶ ረዳኢን ቢቢሲ ጠይቋቸዋል።

“ከፌደራል መንግሥት ጋር የሚያቃቅር ነገር የለም። ለተልእኮ መጥተው ከሆነ ለዚያ የሚሆን ነገር የለም። አንድ ሃገር ከመሆናችን አንፃር ከመረዳዳት ውጭ ምንም ነገር የለም” ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ግብረ ኃይሉ እንዲወጣ ባዘዛው መሰረት ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ተገልጿል።

https://www.bbc.com/amharic

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy