በትራፈክ አደጋ ሁለት የፌዴራል ፓሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የዳውሮ ዞን ፓሊስ መምሪያ አስታወቀ።
በዳውሮ ዞን ሎማ ወረዳ ላላ ቀበሌ ከኮይሻ ወደ ጊቤ 3 የኤሌክትሪክ ሀይል ፕሮጀክት ምድብ ቀጠና ለስራ በርካታ የፌዴራል አባላትን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ ፍሬን ተበጥሶ አደጋው የደረሰ ሲሆን፥ አንድ አባል አደጋው በደረሰበት ወቅት ህይወቱ ሲያልፍ ሌላኛው አንድ አባል ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ አልፏል።
የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ጦሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ አሽከርካሪውን ጨምሮ በመኪና አደጋው ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው 23ቱ በወላይታ ሶዶ ኦተና ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ሰባቱ ቀላል ጉዳተ የደረሰባቸወ ደግሞ በተርጫና ገሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል።
እንደ ኮማንደር አለማየሁ ገለፃ ሰባት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምን አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው አስታውቀዋል።
የክልሉ ፓሊስ ህይወታቸው ያለፈው የሁለቱ የፈዴራል ፓሊስ አባላት አስክሬን በክብር ወደ ቤተሰቦቻቸው ተሽኝተዋል።
በታሪክ አዱኛ