Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ያለግንባሩ እውቅና በኦነግ ስም ዝርፊያና መሰል ህገ ወጥ ድርጊት እየተፈጸመ መሆኑ ተረጋግጧል- የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት

0 633

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ያለ ግንባሩ እውቅና በኦሮሞ ነጻነት ስም ዘርፊያና መሰል ህገ ወጥ ድርጊት እየተፈጸመ መሆኑ መረጋገጡን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ አስታወቁ፡፡

በአቶ ዳውድ ኢብሳ ከሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋር በአስመራ የተደረሰው እርቅ ውጤታማ እንደነበር ገልጸው ህገ ወጥ ተግባራቱ ከእውቅናቸው ውጪ መሆናቸውን የግንባሩ አመራሮች እንዳረጋገጡላቸው ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

አቶ ለማ ለመገናኛ ብዙኃን እንዳሉት ከኦነግ አመራሮች ጋር የተደረገው ውይይት የኦሮሞን ህዝብ በሚመለከቱ ታላላቅ አጀንዳዎች ላይ ተባብሮ በመስራት የህዝቡን አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡

ለዚህም በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ መደረሱን ነው ፕሬዝዳንቱ ያብራሩት፡፡

በኦሮሞ ስም መደራጀት እንጂ ስምምነቱን አስታኮ ሰላምን ማደፍረስ እንደማይቻል አስገንዝበው በዚህ መሰሉ ድርጊት የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል፡፡

ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የተደረሰው ስምምነት በዚህ መሰሉ ችግር እንዳይደናቀፍ መንግሥት የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ህብረተሰቡም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚሰራው ስራ አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy