NEWS

በ630 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው አባይ ህትመትና ወረቀት ፋብሪካ ተመረቀ

By Eden TG

August 06, 2018

በ630 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው አባይ ህትመትና ወረቀት ፓኬጂንግ ፋብሪካ በዛሬው እለት ተመረቀ።

ፋብሪካው በአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ) እና በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ አማካኝነት በጋራ የተገነባ ነው።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፋብሪካውን ተገኝተው መርቀዋል።

ፋብሪካው ለህትመትና ወረቀት ስራው ጥሬ እቃዎቹን በሀገር ውስጥ የሚጠቀም መሆኑም በዚህ ወቅት ተገልጿል።

የፋብሪካው መገንባትም በሀገሪቱ ያለውን የህትመትና የወረቀት ዋጋ ማሻቀብ ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ባህር ዳር ከተማ አባይ ማዶ አካባቢ የተገነባው ፋብሪካ ግንባታ በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ነው።

መረጃው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ነው።