አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው ታገዱ፡፡
ባሕር ዳር፡ነሀሴ 18/2010 ዓ.ም(አብመድ)የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታግደዋል፡፡
ነባር አመራሮች በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እንዲሳተፉ የሚፈቅደው መመሪያም ተሸሯል፡፡በመሆኑም ከዚህ በኋላ በሚኖረው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አባል ያልሆነ አመራር አይሳተፍም፡፡ማዕከላዊ ኮሚቴው የሁለት ቀን ስብሰባውን ዛሬ አጠናቋል፡፡