Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርን ጨምሮ አራት የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ረቡዕ ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

0 709

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከአቶ አብዲ ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የክልሉ ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ራህማ መሐመድ፣ የክልሉ የዳያስፖራ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱረዛቅ አሚንና የክልሉ መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን መሐመድ ናቸው፡፡

በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ በኩል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ፣ ወደ ምርመራ ቢሮው የመጡት ከነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ መሆኑ ታውቋል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ‹‹መንግሥት ለክልሉ ልማት የሚመድበውን በጀት ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል፣ ወጣቶችን በማደራጀት ተከባብሮ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የክልሉን ሕዝብ በዘርና በሃይማኖት በመከፋፈል እንዲፈናቀሉ በማድረግ፣ የእምነት ተቋማትን በማቃጠልና በርካታ ሰዎች እንዲገደሉ አድርገዋል፤›› በሚሉ ወንጀሎች ተጠርጥረው ነው፡፡

ፖሊስ በክልሉ ሌላ መርማሪ ቡድን ልኮ ተጨማሪ የጥፋት ድርጊቶችን እየመረመረ በመሆኑ፣ ለምርመራው ሒደት የፀረ ሽብር ሕጉ 652/2001 አንቀጽ 3 የሚያመላክት በመሆኑ ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው እንዳይከበር ጠይቋል፡፡ በሌላ በኩል ተጠርጣሪዎቹ የደም ግፊትና የጨጓራ በሽታ አለብን በማለት፣ በተለይ አቶ አብዲ፣ ‹‹በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋልኩበት ከነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በቀን አንድ ዳቦና ሻይ ነው የሚሰጠኝ፣ ሕክምና እያገኘሁም አይደለም፣ ላለፉት 20 ቀናት በታሰርኩት በጣም ቆንጆ ቤት የምፈልገው ሁሉ እየቀረበልኝ ከቤት እንዳልወጣ ብቻ ነበር ገደብ የተጣለብኝ፡፡ ነገር ግን አሁን ያለሁበት እስር ቤት ምግብ በአግባቡ እየቀረበልኝ አይደለም፡፡ በጣም በከፍተኛ ችግር ውስጥ ስላለሁ ፍርድ ቤቱ ይህንን ይገንዘብልኝ፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በሽታ እንዳለባቸውና አየር በማይገባበት ክፍል ውስጥ እንደታሰሩና ምግብ እንደማይቀርብላቸው የገለጹ ሲሆን፣ ፖሊስ ከነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለሌላው እስረኛ የሚያቀርበውን ምግብ እንደሚሰጣቸው አስታውቆ በምግብ አስተዳደር ክፍል የሚደረግ ተጨማሪ ነገር ካለ እንደሚመለከት አስታውቋል፡፡

ምርመራውን ለማድረግ ፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን፣ በተጠርጣሪዎቹ የተጠየቀውን የዋስትና መብት ሙሉ በሙሉ ተቃውሟል፡፡ ፍድር ቤቱም፣ የዋስትናውን ጉዳይና የጊዜ ቀጠሮውን መርምሮ ለመወሰን ለሐሙስ ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ስምንት ሰዓት ቀጥሯል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy