Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአደናቃፊዎች ዓላማ…

0 322

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአደናቃፊዎች ዓላማ…

                                                        ደስታ ኃይሉ

ኢትዮጵያ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ባለቤት ናት። ወጣቶች የአገራቸው የነገ ተስፋ ናቸው። ስለሆነም ለሰላም ዘብ በመቆም አገራዊ ለውጡን ከዳር የማድረስ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። በየትኛውም የአገራችን ክፍል የሚታይ የስርዓት አልበኝነት ተግባር ለውጥ አደናቃፊ ነው። ስርዓት አልበኝነት ለውጥን ያኮላሻል እንጂ አይደግፍም።

ለውጡን ያመጡት ወጣቶች ናቸው። በለውጡ ያላቸውን ዕድልና ተስፋ እንዲሁም ያገኟቸውን ድሎች ከእጃቸው እንዳያመልጡ ሊጠነቀቁ ይገባል። ስለሆነም ለሚያከናውኗቸው ማንኛውም ድርጊቶች ምክንያታዊ አስተሳሰብን ማጎልበት አለባቸው። በምክንያታዊነት የሚመራና የሚጓዝ ወጣት የየትኛውም ወገን ፍላጎት ማስፈጸሚያ አይሆንም። ስለሆነም ስርዓት በኝነትን በመኮነን ፍላጎትን በህግና በህግ ብቻ የመጠየቅ ጉዳይ የወጣቱ ተግባር መሆን ይኖርበታል።

እንደሚታወቀው ሁሉ አገራችን ውስጥ የህግ የበላይነት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። የህግ የበላይነት የሚጠቅመው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ነው። የህግ የበላይነትን ማክበር የስልጣኔ ምልክት ነው።

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የህግ የበላይነት መኖር የግድ ይላል። መንግስት ባለበት አገር ውስጥ ማንም ሰው ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም። በመሆኑም መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር እያደረጋቸው ከመጣው መንገድ መውጣት የለበትም።

የኢትዮጵያ መንግስት መብትም፣ ኃላፊነትም ሆነ ግዴታ ያለበት አካል በመሆኑ በህጉ አግባብ መሰረት ተጠርጣሪዎችን ህግ ፊት በማቅረብ ተገቢውን ትምህርት የሚያገኙበትን ሁኔታ በመፍጠር የተጎጂዎችን እምባ ይጠርጋል።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ ህዝቦች መቻቻልን መፍጠር የቻሉ እንዲሁም ዴሞክራሲያቸውን ስር እንዲሰድ ለማድረግ የህግ የበላይነትን የሚያፀና ለውጥን ዕውን በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ህዝቦች ለውጥ አደናቃፊዎችን አይሹም።

እርግጥ ኢትዮጵያ የጀመረችው የለውጥ ሂደት ስኬታማ ሆኖ እንዲቀጥል፤ አስተማማኝ ሠላም የሰፈነበት ምህዳርን መፍጠር የግድ ነው። ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት ውስጥ ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት የሆኑ እንቅስቃሴዎችን መከላከልና መቆጣጠር ይገባታል። ለዚህም የህግ የበላይነትን ማስፈን አለባት።

የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ሰላምን እንጎናፀፋለን። ሰላምን ስንጎናፀፍ ደግሞ ያመጣነውን ለውጥ እናስቀጥላለን። ለውጡ እንዲቀጥልም የህግ የበላይነት ነከበር አለበት። በህግ የበላይነት ውስጥ ህጎች ለአንዱ የሚሰሩ ለሌላው ደግሞ የማይሰሩ ለሆኑ አይችሉም።

በህግ ፊት የሚያንስም ይሁን የሚበልጥ ወገን አይኖርም። የህግ የበላይነት ሲኖር ሁላችንም ከሚገኘው ሀገራዊ ጥቅም እንካፈላለን። ጥቅማችንን እናረጋግጣለን። የማንኛውም ዜጋ ጥቅም የሚረጋገጠው በህግ የበላይነት የዳበረ ሰላም ማምጣት ሲቻል ነው።

ስርዓት አልበኝነት ከህግ የበላይነት ጋር ምንም ዓይነት ዝምድና የለውም። ስርዓት አልበኝነት የህግ የበላይነትን በመፃረር ጥቂቶች እንደልባቸው የሚሆኑበት መንገድ ነው። ይህ ተገቢ ያልሆነና ለውጥ አደናቃፊ መንገድ መዘጋት አለበት። መንገዱን በመዝጋት በኩል ወጣቶች የበኩላቸውን ድርሻ ማበርከት ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ተግባሩ ዋጋ ከፍለው ያመጡትን ለውጥ የሚያደናቅፍ ስለሆነ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም በስርዓት አልበኝነት የለውጥ አደናቃፊዎች ዓላማ ማስፈፀሚያ መሆን የለባቸውም። ዛሬም አንፃራዊ ሰላማችንን የለውጡ አደናቃፊዎች እንዳያደፈርሱበት መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

በአሁኑ ሰዓት አገራችን ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚዋ እየሆነች ነው። ለዚህም ምስክሮቹ የቀጠናው አገራትና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው። ይህን ቀዳሚነታችንን የህበረተሰቡን ሰላም በማወክ ለማደናቀፍ የሚሹ ጥቅማቸው የተነካባቸው ሃይሎች እየተንቀሳቀሱ ነው።

ይሁን እንጂ ከህዝብ የለውጥ ፍላጎት ፊት ሊቆም የሚችል አንዳችም ሃይል አይኖርም። ለአገሩ ሰላምና ዕድገት ዋነኛው ሃይል ህዝብ እንጂ ‘እኔ ብቻ ልብላ’ የሚሉ ስግብግቦች ስላልሆኑ ነው። እናም ህብረተሰቡ ለሰላሙ ቅድሚያ መስጠት አለበት።

እርግጥ ሰላም ከሌለ ህግን ማስከበር አይቻልም። መብትም አይከበርም። መብትን በፈቃዳችን ሳይሆን በህገ ወጦች ችሮታ ብቻ ለማግኘት እንገደዳለን። ህገ ወጦች ህዝቡ በትግሉ ያገኘውን መብት ሲሻቸው ይነፍጉታል። የህግ አስፈፃሚም ይሆናሉ። ሌላው ቀርቶ የህዝቡ በሰላም ወጥቶ የመግባት ጉዳይም አሳሳቢ ይሆናል።

የሰላም እጦት ፈተናን እንኳንስ በተግባር የተፈተነው የአገራችን ህዝብ ቀርቶ ሌላውም ቢሆን ያውቀዋል። ያለ ሰላም አንዳችም ነገር መፈፀም እንደማይቻል የሁሉም አገር ህዝብ ይገነዘባል። በመሆኑም ለሰላሙ ዘብ በመቆም የለውጡን አደናቃፊዎች አምርሮ ሊታገላቸው ይገባል። በተለይ

ባለፉት አራት ወራቶች ውስጥ ብቻ የተፈጠረው አስተማማኝ ሰላም ምን ያህል ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ወጣቱ ያውቀዋል። የለውጡ ባለቤትም እርሱ ነው። እርግጥም የህዝብን የለውጥ ፍላጎትን ማንም ሊያቆመው አይችልም። አገራችን የህዝብን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የጀመረችው ፈጣን የለውጥ ጉዞ ተጨባጭ ስኬቶችን እያስመዘገበ ነው።

ወጣቶች መስዋዕት ጭምር የሆኑለት ይህ ለውጥ በአሁኑ ሰዓት ማንም ሊያቆመው የማይችልት ደረጃ ደርሷል። የለውጥ አደናቃዎች ግን ወጣቱን የዓላማቸው ማስፈጸሚያ ለማድረግ እየሞከሩ ነው።

እነዚህ አደናቃፊዎች ፈጣኑ ለውጥ ከስጋት ላይ የጣላቸው ናቸው። የለውጡን ሂደት ለማደናቀፍ በርካታ እንቅፋቶችን አዘጋጅተዋል። ወጣቱን በመጠቀሚያነት ለመጠቀምም እየሰሩ ነው። ወጣቱ ሴራቸውን ማምከን የሚችለው ህዝብን ከህዝብ ጋር ለማባላት ያላቸውን ዓላማ ሲገነዘብ ነው።  

የአደናቃፊዎችን ዓላማ መገንዘብ ተባባሪ ባለመሆን በለውጥ ስራው ላይ ብቻ እንድናተኩር ያደርገናል። ወጣቶችን በገንዘብ ለመደለል የሚደረጉ ጥረቶችን በመከላከል ድርጊታቸውን ማጋለጥ ያስፈልጋል።

ስለሆነም ወጣቱ አደናቃፊዎች ምን እንደሚፈልጉ ከተገነዘበ ሴራቸውን በቀላሉ ሊያከሽፈው ይችላል። እናም በያለበት ቦታ ሁሉ የአደናቃፊዎች ዓላማ አስፈፃሚ ላለመሆን በማንኛውም ስርዓት አልበኝነት ጉዳይ ውስጥ መሳተፍ አይኖርበትም።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy