የዐቢይ ጥሪ ለሌሎች የማሰብ ጥሪ ነው
ሰዒድ ከሊፋ
ታዋቂው የፈረንሳይ ምሁር አሌክስ ቶኮቪሌ፤ ‹‹አሜሪካውያን እያንዳንዱን የህይወት እንቅስቃሴአቸውን ከግል ፍላጎት መርህ አንጻር መተርጎምን ይመርጣሉ›› ይላል፡፡ በመሆኑም፤ በዚህ ዓይነት ህብረተሰብ ውስጥ ለሌሎች ሰዎች ጥቅም መስራት፣ የራስን ፍላጎት መስዋዕት ማድረግ ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር ‹‹አልቱሪዝም›› (altruism) ቦታ የለውም፡፡ ይህ አስተሳሰብ በርካታ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል ቢሆንም፤ ነገር ግን እንዲህ ያለ አስተሳሰብ ጠንክሮ የሚታይባቸው ምዕራባውያን ሐገራት፤ ይህ አስተሳሰብ የሚፈጥረው ችግር ተባብሶ የስርዓት ቀውስ ከሚጎትትበት ነጥብ እንዳይደርስ ለማድረግ የሚያግዝ መላ አላቸው፡፡
ቶኮቪሌ እንዳለው ‹‹የግል ፍላጎትን በመርህ መተርጎም›› አንድ ነገር ነው፡፡ ይህ መርህ ግለኝነት ወደ ስርዓት ቀውስ እንዳይጥላቸው ጠብቋቸዋል፡፡ የግል ፍላጎት በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆሙ መኪኖች ናቸው፡፡ እነዚህ መኪኖች እንዳሻቸው ቢሄዱ መጋጨት እንጂ መተላለፍ አይቻልም፡፡ ዝንተ ዓለም ተገትሮ ከመቅረት በቀር ወደፊት መሄድ አይታሰብም፡፡ እነዚህን መኪኖች እንዲተላለፉ ለማድረግ የሚቻለው በአንድ የጋራ ህግ ነው፡፡ ህጉን ለማስከበር በሚችለው ትራፊክ አገልግሎት ነው፡፡
እንደ ምራባውያን የግል ፍላጎትን በመርህ ለመግራት የማይችሉ ህዝቦች ደግሞ የባሰ መከራ ይገጥማቸዋል፡፡ በመስቀለኛ መንገድ ላይ ቆሞ መቅረትን ብቻ ሳይሆን፤ ከመኪና እየወረዱ መደባደብ ይመጣል፡፡ በአውሮፓ ግለኝነት ሥር የሰደደ አስተሳሰብ ሆኗል፡፡ በመሆኑም፤ ለሰዎች ጥቅም የመስራት (altruism) አስተሳሰብ ገዢ ያጣ አስተሳሰብ ከመሆን ደርሷል፡፡ እንደ አንዳንድ ምሁራን አስተሳሰብ ለሰዎች ጥቅም የመስራት (altruism) አስተሳሰብ በሁለት የሚከፈል ነው፡፡
የመጀመሪያው፤ የግል ጥቅምን በማስከበር ፍላጎት የተነሳሳ ለሰዎች ጥቅም የመስራት (altruism) አስተሳሰብ utilitarian ወይም mutual altruism ነው፡፡ ይህም ከግል ጥቅም ጋር የተሳሰረ ለሌሎች ሰዎች የመጨነቅ አመለካከትን የሚገልጽ ጽንሰ ሐሳብ ሲሆን፤ ሁለተኛው ልባዊ ወይም ሞራላዊ አልቱሪዝም (genuine or moral altruism) የሚሉት ነው፡፡ ይህም አስተሳሰብ የሚፈጠረው፤ ሰዎችን የመርዳት ፍላጎት ራስን መስዋዕት ከማድረግ ወይም ምንም ዓይነት የግል ፍላጎት በሌለበት ሁኔታ ሰዎችን የመርዳት እንቅስቃሴ ሲታይ ነው፡፡
ለምሣሌ፤ የንግድ ድርጅትን መልካም ገጽታ ለመገንባት የሚደረግ የገንዘብ ልገሳ የመጀመሪያውን ዓይነት አልቱሪዝም ሲያመለክት፤ ሠራተኞች ከፍ ያለ የውሳኔ አቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ የአመራር ዘይቤ መከተል ለሁለተኛው ዓይነት አልቱሪዝም አብነት ይሆናል፡፡
የአልቱሪዝም ዘይቤ ያለው አመራር በመከተል አብነት የሚሆኑ በርካታ ሰዎች በታሪክ መዝገብ ስማቸውን አስፍረዋል፡፡ ማሀትማ ጋንዲ፣ እማሆይ ቴሬዛ፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ (ታናሹ) ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ጓዶቻቸውን ለማትረፍ የእጅ ቦንብን ታቅፈው በመፈንዳት ከእነርሱ ጋር የነበሩ የሌሎች ሰዎችን ህይወት የሚያተረፉ ወታደሮችም ስማቸው እንደ ተጠቀሱት ሰዎች ባይጠራም ምድባቸው ከነዚህ ወገን ነው፡፡
የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ ‹‹አሁን በሐገራችን ትልቅ ችግር የፈጠረው ስግብግብነት ነው›› በማለት እኔ ብቻ በሚል አስተሳሰብ መታጠር ያስከተለውን ችግር በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ፤ ሐገር እንደዚህ ዓይነት ‹‹የስግብግብነት›› ችግር ውስጥ ሲገባ፤ እንዲሁም እንደኛ ለ50 ዓመታት በ‹‹ገሎ ማለፍ›› የፖለቲካ ባህል የተጎዳ ህብረተሰብ ሲኖር አልቱሪስቲካዊ አመራር ፈውስ ይሆናል፡፡ ዶ/ር ዐቢይ እንዲህ ዓይነት አመራር በሚያስፈልግበት አጋጣሚ የመጡ መሪ ናቸው፡፡ ለብዙሃኑ በጎ ዕድል ሲባል፤ አፈር የላሰ የሞራል መርህን ከወደቀበት ለማንሳት ሲባል፤ ወደፊት ብሩህ ዘመን እውን ለማድረግ ሲባል፤ አንድ ታላቅ ራዕይን ለማስፈጸም ሲባል መሪዎች አንዳንድ ጥቅሞችን ቸል በማለት ለዘላቂው እና ለትልቁ ነገር ለመስራት ይገደዳሉ፡፡ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድም የመደመር፣ የፍቅር እና የይቅርታ መንገድን ለመምረጥ የሚገደዱበት ሁኔታ አጋጥሞአቸዋል፡፡ ይህም ትራንስፎርሜሽናል አመራር የሚጠይቅ ሐገራዊ ሁኔታ መኖሩን ተረድተዋል፡፡ ስለዚህ ማንዴላን በልብሳቸው እና በልብቸው አንጸባርቀዋል፡፡ ጋንዲን በንግግራቸው ደጋግመው ጠቅሰዋል፡፡ የአመራር ዘይቤአቸውንም ከተጠቀሱት የህዝብ መሪዎች ጋር በማነፃጸር ማየት ይቻላል፡፡
ራስን ለሌሎች መስዋዕት የማድረግ ነገር ከአልቱሪዝም ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ልዩነቱ የትኩረት ጉዳይ ነው፡፡ ራስን ለሌሎች መስዋዕት የማድረግን ነገር ስናነሳ፤ ትኩረታችንን ጠበብ አድርገን ሰውዬው ለሌሎች ሲል በሚከፍለው ዋጋ ላይ ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ፤ ራስን ለሌሎች መስዋዕት የማድረግ አልቱሪስቲክ ባህርይ የሚያንጸባርቁ መሪዎች በተከታዮቻቸው ዘንድ ተመሳሳይ ስሜት ይፈጥራሉ፡፡ ራሳቸውን ለሌሎች መስዋዕት የማድረግ ባህርይ የሚያንጸባርቁ መሪዎች በፍጥነት ቅቡል ይሆናሉ፡፡ ሌሎች ለእርሱ እንዲታመኑላቸው እና እንዲሞቱላቸው የሚያደርግ ጠንካራ ስሜትን የሚቀሰቅሱ (charismatic) መሪዎች ይሆናሉ፡፡
ራሱን ለሌሎች መስዋዕት የማድረግ ባህርይ የሚያንጸባርቅ መሪ ሲነሳ፤ ተመሪዎችም ለመሪው አጸፋውን ለመመለስ ይጣጣራሉ፡፡ በተለይ ሐገር ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ስትገባ እንዲህ ዓይነት የአመራር ዘይቤ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ አነቃቂ እና ምሁራዊ ቀስቃሽነት ያለው የአመራር ዘይቤ እንደ ትራንስፎርሜሽናል አመራር ሊወሰድ ይችላል፡፡ ምነው ቢሉ፤ ተመሪዎች ከራሳቸው ጠባብ ፍላጎት ተሻግረው እንዲያስቡ የሚያስገድድ በመሆኑ ነው፡፡ ታዲያ አልቱሪዝም አንዳንድ አሉታዊ ገጽታዎች አሉት፡፡ አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ውጤት ሊያስከትልም ይችላል፡፡ እኩልነት እና ፍትህን የመሳሰሉ የሞራል መርሆዎችን የመጣስ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡
ለተቸገሩ ሰዎች ገንዘብ እና አገልግሎት ለማቅረብ በአልቱሪዝም ስሜት የተገፋፋ ሰው ሥራውን በፍትሕ መርህ ላይ ተመስርቶ የመስራት ዝንባሌ ይኖረዋል፡፡ ገንዘብ እና አገልግሎትን ለተጎችዎች እኩል ያከፋፍላል፡፡ በተቃራኒው፤ የሐዘኔታ ስሜት ለፈጠረበት አንድ የተለየ ወገን ወይም ሰው ልዩ ድጋፍ የሚያደርግበት ሁኔታም ሊፈጠር ይችላል፡፡ ለምሣሌ፤ አንዳንድ ተጎጅዎች በተጨባጭ ከፍ ያለ ጉዳት ደርሶባቸው (ከሌሎች ረዘም ያለ ጊዜ ሲጠብቁ የቆዩ ሆነው) ሳለ፤ የተለየ የሐዘኔታ ስሜት ለፈጠረብን ሰው በት ቅድሚያ ድጋፍ ልናደርግ እንችላለን፡፡ አልቱሪዝም እንዲህ ያለ ወገንተኝነት ሊያስከትል ይችላል፡፡ እንደውም አንዳንዴ፤ አልቱሪስቲካዊ ተግባር ሥነ ምግባራዊ የማይሆንበትም አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስለዚህ ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ሚዛን ለመጠበቅ ደግሞ፤ አልቱሪስቲክ እንቅስቃሰአችን የሞራል መርሆችን እንዳይጥስ ለማድረግ መጣጣር እና ፍትሕ ያጡ ሰዎችን እንዲመለከት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በተረፈ አልቱሪዝም ፍትሐዊነትን፣ ለሌሎች ጥንቃቄ ማድረግን እና አኩልነትን የሚያበረታታ በመሆኑ፤ እንደ ኢትዮጵያ ሐይማኖታዊ እና ብዙ በደሎች ለሚታዩበት ሐገር እና በአንዳንድ ታሪካዊ አጋጣሚዎች ተመራጭ ሞራላዊ መርህ ወይም የአመራር ዘይቤ ነው፡፡
አመራር ከኃይል የራቀ እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ ተጽዕኖ ነው፡፡አዎ፤ አመራር በአንድ ሁኔታ ውስጥ አንድን ዓላማ ወይም ግብ ለማስፈጸም ሲባል በሰዎች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ መሪም አንድን ትልቅ ዓላማ ለማስፈጸም በአደጋዎች መካከል ጭምር እያለፈ አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር ወይም አዲስ ጎዳናን ለመክፈት የሚሞክር ሰው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ነባሩን ወይም ተቀባይነት አግኝቶ የቆየውን ድርጅታዊ አሰራር ይገዳደራል፡፡ አንድ መሪ መጪውን ጊዜ ብሩህ የሚያደርግ አዲስ ራዕይ እያለመ፤ አጋሮችን በማሰባሰብ እና ትብብርን በማጠናከር፤ ሰዎች ለአንድ ዓላማ በቁርጠኝነት እንዲሰለፉ የሚያደርግ የጋራ ራዕይ መቀስቀስ የሚችል ሰው ነው፡፡ እንዲሁም ጥሩ አመራር፤ ለሌሎች ጥሩ አብነት ማስቀመጥ፤ አበረታች የሆነ ስሜት የሚፈጠሩ ትናንሽ ድሎችን ማቀድ እና ለዜጎች አስተዋጽዖ እውቅና በመስጠት፣ ማበረታታት እና ስኬቶችን ማክበር ይኖርበታል፡፡
ጥበባዊ አመራር የሰዎችን አሰተሳሰብ በማረም ወይም በማረቅ ከነባሩ በተለየ መንገድ የማየት ዕድል በመፍጠር የትራንስፎሜሽን ኃይል ለመሆን ይችላል፡፡ በዚህ ረገድ የኪነ ጥበብ እና ጥበባዊ አመራር ቁርኝት በደንብ ሊታሰብበት የሚገባ አጀንዳ ነው፡፡
በእንግሊዝኛ ቋንቋ ‹‹creativity›› የሚለው ቃል ምንጩ ከኢንዶ -ዩሮፒያን የቋንቋ ሲሆን ሥርወ ቃሉ ‹‹kere›› ነው፡፡ ‹‹kere›› የሚለው ቃል ፍቺም ‹‹አዲስ ነገር እንዲበቅል ማድረግ›› (to make something grow) የሚል ነው፡፡ መሪዎች የጥበብ አሳላጨች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ጥበባዊ መሪዎች በጥበብ አዝመራ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡ ጥበባዊ ማንነታቸውንም ያሳያሉ፡፡ የመሪዎች አንዱ እና ዋነኛ ሥራቸው ራዕይ መቅረጽ እና በህዝብ ህሊና ውስጥ ማስረጽ፣ በአነቃቂ ምስል ሐሳቦችን እና ጽንሰ ሐሳቦችን መግለጽ ነው፡፡ ስለዚህ በጨለማ ውስጥ አማራጮችን የማሳየት አቅም እና ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ መሪዎች ምናብን ያለቃቃሉ፡፡ ትኩረትን ይስባሉ፡፡ በዚህም አዲስ እና አወንታዊ አደረጃጀትን የሚፈጥሩ ጎዳናዎችን ይከፍታሉ፡፡ ማህበራዊ ህይትን በአዲስ ዓይን በማየት አዲስ ትንታኔ ለማቅረብም ይችላሉ፡፡
ፍኖተ መጸብሃን የሚጣላህን መጥላት፤ የሚወደንን መውደድ ነው፡፡ ፍኖተ አማጺያን፤ የሚጠላንንም ሆነ የሚወደንን መጥላት ነው፡፡ ፍኖተ ክርስቶስ፤ የሚወደንን ብቻ ሣይሆን የሚጠላህን ሰው ጭምር መውደድ ነው፡፡ ጠላቶቻችንን መውደድን የሚያዝ ነው፡፡
የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ ስግብግብነት እና እኔ ብቻ የሚል አስተሳሰብ በገነገነበት፤ የ‹‹ገሎ ማለፍ›› የፖለቲካ ባህል በተንሰራፋበት ህብረተሰብ ውስጥ ለትውልድ ፈውስ የሚሆን እና ከነማንዴላ፣ ጋንዲ እና ኪንግ (ታናሹ) የሚነፃጸር አልቱሪስቲካዊ የአመራር ዘይቤ ይዘው የመጡ መሪ ናቸው፡፡ ዶ/ር ዐቢይ በጊዜአዊ ነገር ከማትኮር ይልቅ፤ ወደፊት የሚታያቸውን ብሩህ ዘመን እውን ለማድረግ በሚያግዝ ዘላቂ አጀንዳ ላይ አትኩረው የሚሰሩ እና የኢትዮጵያዊት አጀንዳን ማቀንቀን በሚያስፈራበት አካባቢ እና ወቅት ከነለማ መገርሳ ጋር ብቅ ያሉ መሪ ናቸው፡፡ እንዲህ ያለ አመራር በሚያስፈልግበት የታሪክ አጋጣሚ የመጡ መሪ ናቸው፡፡